Go to full page →

ከአባቶቻችን የላቀ ከእኛ ይጠበቃል ChSAmh 122

በአባቶቻችን ላይ ካንጸባረቀው የበለጠ ብርሃን በእኛ ላይ ያበራል፡፡ አባቶቻችን ከሰጡት አገልግሎት ጋር ተመሳሳይ አገልግሎት በመስጠታችን በእግዚአብሔር ተቀባይነት ወይም ከበሬታ ማግኘት አንችልም፡፡ እነርሱ በእግዚአብሔር ፊት ያኙትን ተቀባይነትና በረከት ማግኘት እንችል ዘንድ ታማኝነታቸውና ቀናኢነታቸው በእኛ ውስጥ ሊኖር የግድ ይሆናል፡፡ እነርሱ የራሳቸውን ብርሃን እንዳጎለበቱ እኛም ብርሃናችን እንዲጨምር በማድረግ-እነርሱ በእኛ ዘመን ቢሆኑ ያደርጉ የነበረውን ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ እያበራልን ባለው ብርሃን መራመድ ይኖርብናል፤ ያለበለዚያ ግን ብርሃኑ ወደ ጨለማ ይቀየራል፡፡--Testimonies, vol. 1, p. 262, ChSAmh 122.1