Go to full page →

በራስ መመካት GWAmh 207

በወንጌል ሥራ ላይ ያልተስተካከለ የጥቂት ዓመታት ልምድ ያላቸው ወጣት ወንጌላዊያን የብዙ ዓመት ልምድ ካላቸው ዕውነተኛ የወንጌል ገበሬዎች የተለዩ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ያልተስተካከለ አስተያየት ያላቸውንና በራሳቸው ከልክ በላይ የሚተማመኑትን ለሥራው አይመርጥም፡፡ አሁን ሥራውን ከደረሰበት ለማድረስ የወረዱትን ፈተናዎች፤ ሥቃይ፣ ተቃውሞና ችግር ያላዩ ሰዎች፣ ትሁታንና ትህትናንና አክብሮትን መማር : አንዳይወድቁ ራሳቸውን ከፍ ከፍ ማድረግ የለባቸውም፡፡ በራሳቸው ላይ ለሚበራው ብርሃን ተጠያቂዎቹ ራሳቸው ናቸው፡፡ GWAmh 207.2

ከባድ ወጊያ በተዋጉት ላይ የሚያጉረመርሙትን ሰዎች እግዚአብሔር አንዳልተደስተባቸው ነግሮኛል:: ሸክሙን የሚያግዛቸው ሳያገኙ በችግርና በመከራ ጊዜ የተጋደሉጉን ሠራተኞቹን እግዚአብሔር ያከብራቸዋል፡፡ ታማኝ ሆነው የተገኙ ትንም አባታዊ ጥንቃቄ ያደርግላቸዋል፡፡ ከልጅነት እስከ አውቀት ለጌታ ሲሰሩ በኖሩት ሽማግሉች ላይ ስህተትና እንከን ለመፈለግ ዘለዓለም የሚደክሙትን እግዚአብሔር ይነቅፋቸዋል፡፡ ወጣቶች ሆይ ማጉምረማችሁና ነቀፋችሁ ለፍርድ ቀን ይጠብቋችኃል (ይቆያችኃል)፡፡ GWAmh 207.3