Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በራስ መመካት

    በወንጌል ሥራ ላይ ያልተስተካከለ የጥቂት ዓመታት ልምድ ያላቸው ወጣት ወንጌላዊያን የብዙ ዓመት ልምድ ካላቸው ዕውነተኛ የወንጌል ገበሬዎች የተለዩ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ያልተስተካከለ አስተያየት ያላቸውንና በራሳቸው ከልክ በላይ የሚተማመኑትን ለሥራው አይመርጥም፡፡ አሁን ሥራውን ከደረሰበት ለማድረስ የወረዱትን ፈተናዎች፤ ሥቃይ፣ ተቃውሞና ችግር ያላዩ ሰዎች፣ ትሁታንና ትህትናንና አክብሮትን መማር : አንዳይወድቁ ራሳቸውን ከፍ ከፍ ማድረግ የለባቸውም፡፡ በራሳቸው ላይ ለሚበራው ብርሃን ተጠያቂዎቹ ራሳቸው ናቸው፡፡GWAmh 207.2

    ከባድ ወጊያ በተዋጉት ላይ የሚያጉረመርሙትን ሰዎች እግዚአብሔር አንዳልተደስተባቸው ነግሮኛል:: ሸክሙን የሚያግዛቸው ሳያገኙ በችግርና በመከራ ጊዜ የተጋደሉጉን ሠራተኞቹን እግዚአብሔር ያከብራቸዋል፡፡ ታማኝ ሆነው የተገኙ ትንም አባታዊ ጥንቃቄ ያደርግላቸዋል፡፡ ከልጅነት እስከ አውቀት ለጌታ ሲሰሩ በኖሩት ሽማግሉች ላይ ስህተትና እንከን ለመፈለግ ዘለዓለም የሚደክሙትን እግዚአብሔር ይነቅፋቸዋል፡፡ ወጣቶች ሆይ ማጉምረማችሁና ነቀፋችሁ ለፍርድ ቀን ይጠብቋችኃል (ይቆያችኃል)፡፡GWAmh 207.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents