Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የተሰጠንን በሚገባ በሥራ ላይ ማዋል

    እግዚአብሔር ለሰው ልጆች በረክቱን በሰፊ እጁ ለግሦልናል፡፡ እነዚህ የተሰጡን የአምላክን ቸርነት የሚገልጡ ሥጦታዎች በሚገባ ከሥራ ላይ ቢውሉ ኖሮ ድህነት፤ በሽታና ችግር ከምድር ገጽ በጠፋ ነበር፡፡ ነገር ግን አሳዛኙ ነገር በሰዎች ክፋት የእግዚአብሔር በረከት ወደ መርገም ሲለወጥ አንመለከታለን፡፡GWAmh 254.2

    ከመሬት የሚገኘውን የሰብል በረከት ወደ ሚያስክር መጠጥ ከመለወጥ የባሰ ክፉ ሥራ የለም፡፡ አጎልማሸነተ ያላቸው ፍራፍሬዎችና ለጤና ተስማሚ የሆነ ጥራጥሬዎች ሕዋሳትን አደንገዘ፤ አእምሮን ለሚያሳብድ መጠጥ ሥራ ይውላሉ፡፡ እነዚህን መርዞች ከመጠጣት የተነሳ ብዙ ቤተሰቦች ምቾታቸው ተበድሎ የቀን ጉርስ ያመት ልብስ ያጣሉ፤ ወንጀደልና ክፋት ይበረክታል፡፡ ብዙ ሰዎች በሕመም ተጎሳቁለው በሞት ዳኝነተ ተይዘው ወደ ሰካራም መቃብራቸው ይወርዳሉ፡፡GWAmh 254.3

    ይህ የጥፋት ተግባር በመንግሥት ሕግ ተደግፎ ሲሠራበት መታየቱ ያስደንቃል፡፡ ሰዎች ወይም ነጋዴዎች ሌሎችን ሰዎች የዚህ ዓለም ኙሮአቸውን እንዲያስናክሉ፣ የሰማይ በሮቻቸውንም እንዲዘጉባቸው ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡ ሕግ አውጭውም ሆነ የሚያሰክር መጠጥ ሳጩ፡ ጉዳቱን አይስተውም፡፡ በመጠጥ ቤቶች ውስጥ የልማድ ባሪያ የሆነው ሰው ገንዘቡን፤ አስተሳሰቡን ለማበላስት፣ ማስተዋሉን ለመቀነስና ደስታውን ለሚያጠፋ ነገር ያውለዋል፡፡GWAmh 254.4

    መጠጥ ሻጩ ያልታደለው ሰካራም ለቤተሰቡ ቀለብና ልብስ ሊያውለው በሚገባው ገንዘብ ኪሱን ይሞላል፡፡GWAmh 255.1

    ይህ ከቅሚያ ሁሉ የባሰ ቀሚያ ነው። ግን በህብረተሰብና በቤተክርስቲያን ውስጥ ተሰሚነት ያላቸው ሰዎች ለዚህ ጉዳይ ድጋፋቸውን ይሰጣሉ፡፡ ስለዚህ ህብረተሰብ ይበላሳሻል፤ እስር ቤቶች ባጥፊዎችና በወንጀለኞች ይጠበባሉ፡፡ የባሰባቸው ወንጀለኞች በስቅላት ይቀጣሉ፡፡GWAmh 255.2

    ጉዳቱ የሚያበቃው በሰካራሙና ባልታደለው ቤተሰብ ሳይ ብቻ አይደለም፡፡ የግብር አከፋፈል ይጨምራል፤ የወጣቶች ግብረገብ ይበከላል፤ የህብረተ-ሰቡ ሐብትና ሕይወት በአስጊ ሁኔታ ላይ ይወድቃል፡፡ ነገር ግን ችግሩ በግልጽ ሰሰማይታይ እውነቱ ተክከዳድኖ ይቀራል፡፡GWAmh 255.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents