Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የክርስቶስ ሥራ አስቸኩዋይነት

    ወንጌላዊያን የዓለም ኗሪዎች በቅርብ ጊዜ በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት የሚቀርቡ መሆናቸውን ቢገነዘቡ ኖሮ በሥራቸው ላይ ተጨማሪ ጥረት ባደረጉ ነበር:: የመጨረሻው ፈተና ለሰው ሁሉ ሊሰጥ ነው፡፡ ‹ማንም የተጠማ ቢኖር ይምጣና ይጠጣ” የሚለው ግብዣ ብዙ አይቆይም፡፡ ሰዎች ሁሉ በወንጌል ጥሪ ይታደማሉ፡፡ መልዕክትኞቹ ከክርስቶስ ጋር ግንኙነት አንዳላቸው መታወቅ አለበት፡፡ ኢሣይያስ 7:37፡፡GWAmh 20.4

    ስለሐሮን ስለአሥራኤል ሊቀ ካህናት እንዲህ ተብሏል፡፡ «አሮንም ወደ መቅደስ በገባ ጊዜ ለዘለዓለም በእግዚአብሔር ፊት መታሰቢያ የአሥራኤልን ልጆች ስም በፍርዱ በደረት ኪስ በልቡ ላይ ይሸከም፡፡› ይህ ምልክት የክርስቶስን የማይለወጥ ፍቅር በግልጽ ያስረዳል፡፡ ታላቁ ሊቀ ካህናችን ሕዝቡን በልቡ ውስጥ ያኖራቸዋል፡፡ ምድራዊያን አገልጋዮቹ ኃላፊነቱን ሊካፈሉ አይገባቸውም ወይ? የኃጢዓተኛውን ልብ የሚመልስ መለኮታዊ ኃይል ብቻ ነው፡፡ ሉተር፣ መላንክቶን፣ ዋይት ፊልድ ወይም ማንኛውም ታላቅ ወንጌላዊ የሰውን ስሜት ሊሰውጥ ባልቻለም: ግን እግዚአብሔር አንደመሣሪያ አድርጐ ሠራባቸው፡፡GWAmh 21.1

    ሰዎች አንድ የሚገፋፋ ኃይል ይሰማቸውና ሳያውቁት ራሳቸውን ያስገዙለታል፡፡ ዛፊም የራሳቸውን ተፈላጊነት ችላ ብለው በመለኮት ኃይል የሚታመኑ አገልጋዮች ያላሰሉትን ክንውን አግኝተው የነፍሳትን ሰብል በብዙው ያመርታሉ፡፡GWAmh 21.2

    ወንጌላዊያኖችን ኃይል ያንሳቸዋል ልል እደፍራለሁ፡- እግዚአብሔር ፀጋውን ሊያጐናጽፋቸው ዝግጁ ነው ግን ዕምነታቸው አፋዊ አንጅ ከዕውነት ባለመሆኑ ከሰማይ የሚላከው የሰዎችን ልብ የሚያቀልጠው ኃይል ያመልጣቸዋል፡፡ በዙሪያቸው ያሉት ነፍሳት በጥፋት ጐርፍ ሲጥለቀለቁ እነርሱ በእንቅልፍ ሰመመን ተውጠዋል፡፡GWAmh 21.3

    የእግዚአብሔር አገልጋዮች ሆይ! የክርስቶስና የሰዎች ፍቅር ባሞቀው ልብ ተነቃቅታችሁ በመተላሰፍና በኃጢዓት የሚሞቱትን ሰዎች አድኑ:: ማስጠንቀቂያችሁ ወደልባቸው ጠልቆ ይግባ:: ጸሎታችሁ ልባቸውን መልሶ ወደ አዳኛችን ያስጠጋቸው:: የመዳንን አዋጅ ለማዳረስ የክርስቶስ ወኪሎች ናችሁ፡፡ የማስተዋልና ራስን ቀድሶ የማቅረብ ጉድለታችሁ ለሰዎች ጥፋት ምክኒያት መሆኑን አትርሱ:: ዘፀዓት 28:29::GWAmh 21.4

    ወላዋይና ግዴለሽ መሆን የለባችሁም:: ያስፈልጋችሁአል፡፡ ይህንም ኃይል እግዚአብሔር ሳይቆጥብ ሊሰጣችሁ ፈቃደኛ ገው: ተስፋውን ለማመንና ለመቀበል ፈቃደኞች የሆኑ ተሁተ ልብ ብቻ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር የሰጣችሁን በረከት ስትጠቀመብት ተጨማሪ በረከት ታገኛላችሁGWAmh 21.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents