Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ወታደሮችን ማሰልጠን

    በባዜል ሰዊትዘርላንድ በሚገኘው ማተሚያ ቤታችን ፊት ለፊት የመንግሥት ወታደር ማሰልጠኛ ታላቅ መናፈሻ አለ፡፡ አንዳንድ ቀን ወታደሮቹ ልምምድ ሲያደርጉ እናያቸዋለን:: ለጦርነት ጊዜ የሚያስፈልገውን ውጊያ ሥልት ይለማመዳሉ፡፡ ምክኒያቱም ድንገት ጦርነት ቢነሳ ውጊያ ብቁ ሆነው እንዲገኙ ነው፡፡GWAmh 45.3

    አንድ ቀን አንድ ትልቅ ድንኳን ቀረበላቸውና የመትከልና የመንቀል ልምምድ ያደርጉ ነበር፡፡ ለእያንዳንዱ ሰው የሥራ ክፍል ተመደበለትና የመትከልና የመንቀል ትምህርት በጥንቃቄ ይሰጥ ጀመር፡፡ ድንኳኑ ብዙ ጊዜ ተተክሎ ተነቀለ፡፡GWAmh 46.1

    ሌላ ጓድ ደግሞ መድፎችን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ እንዴት ሊያሸሽ እንደሚችል፣ የመድፍ ተኩስ ልምምድና ፤ ከመኪና ላይ የመጫንና የማውረድ ልምምድ ያደርግ ነበር፡፡GWAmh 46.2

    አምቡላንስ (የቁስለኛ መኪናዎች) ቀረቡና የህክምና ጓዱ ለቁስለኞች እንዴት ሊጠነቀቁ አንደሚችሉ ትርኤት ያሳዩ : በቃሬዛ ላይ የተጋደሙ ሰዎች እንደ ቁስለኞች ራሳቸው፣፤እጅና አግራቸው በሻሽ ተጠግኖ ከውጊያ በኋላ በመኪና ተጭነው አንደጦር ሜዳ ከተቆረጡበት ቦታ ያወጡአቸው ነበር፡፡GWAmh 46.3

    ወታደሮቹ ለብዙ ሰዓታት በእንዲህ ያለ ልምምድ ይቆያሉ፡፡ የጦር መሣሪያዎቻቸውን ጥለው እንዴት ባለ ፍጥነት ሊያነሱአቸው እንደሚችሱም ይለማመዱ ነበር፡፡ ለማንኛውም ድንገተኛ አደጋ ብቁ ሆነው አንዲገኙ የሚያስተማምን ሥልጠና ይሰጣቸዋል፡፡GWAmh 46.4

    ታዲያ ለአማኑኤል ተሰልፈው የሚዋጉ አርበኞች የበለጠ ዝግጅት አያስፈልጋቸውምን፤ ለመንፈሣዊ ጦርነት የታጩ ዕጩ ወታደሮች ሁሉ በሚገባ መሠልጠን አለባቸው፡፡ ከማዘዝ በፊት መታዘዝን ማወቅ አለባቸው፡፡GWAmh 46.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents