Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ራሴ አበቃለሁ ማለት

    አንዳንድ በወንጌል ሥራ ሳይ ለብዙ ጊዜ የቆዩ ሰዎች ከእንግዲህ ምንም ዓይነት ትምህርት የሚያስፈልጋቸው መስሎ አይሰማቸወም፡፡ ግን ታላቅ ትምህርት የጐደላቸው እነርሱ ናቸው፡፡ ሰዎች የሥራውን ታላቅነትና የዕውነትን ክቡርነት በበለጠ ሲገነዘቡ አለማወቃቸውን ሊያውቁ ይችላሉ::GWAmh 48.1

    «እነዚህን ነገርች ለማከናወን ማን ብቁ ሆኖ ይገኛል?” የሚሉ ልቦናቸውን በጽሞና ሲመረምሩና ራሳቸውን ከክርስቶስ ሕይወት ጋር ሲያስተያዩ ብቻ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ በትህትና ታርቀው ወደ ክርስቶስ ለመጠጋት የዕለት ትግላቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ራስን መውደድን ካሸነፉ በኋላ የክርስቶስን ዱካ መከተል ይችላሉ፡፡ «የቃልህ ባትሪ ያበራል:: ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል፡፡” (መዝ. 119፡130) የራሳቸውን ችሎታ ከፍተኛ ግምት የሚሰጡ ሰዎች ግን ለእግዚአብሔር ቃል በልባቸው ቦታ ስለማይሰጡት ሊያበራላቸው :GWAmh 48.2

    አንዳንዶች ጠልቀው ለማያውቁት ሥራ ገጣሚ ነን ብለጡ ያስባሉ: በራሳቸው ተማምነው ሥራውን ቢጀደምሩ፣ በክርስቶስ ትምህርት ቤት ውስጥ ሊያገኙት የሚገባቸውን ጠቃሚ ዕውቀት ሳያገኙ ይቀራሉ፡፡ እነዚህ ያሳሰቧቸው ብዙ ችግሮች ያጋጥሟቸዋል፡፡ የራሳቸውን ብቁ አለመሆን እስኪረዱ ድረስ ጥበብና የሥራ ልምድ ይጐድላቸዋል፡፡GWAmh 48.3

    ጥሩ እያላቸው በደንብ ባልሰለጠነ ሰዎች የእግዚአብሔር ሥራ ብዙ ጊዜ ተበድሏል፡፡ ይይዙ ይጨብጡትን በማያውቁት የሥራ መስክ ይሰለፉና ልፋታቸው መና ሆኖ ይቀራል፡፡ ከመጀመሪያው መልካም አመራር አግኝተው ቢሆን ኖሮ ሊፈጽሙ ከሚችሉት አንድ አሥረኛውን ሳይፈጽሙ ይቀራሉ:: ሲጀምሩ የነበራቸው አንዳንድ ሀሳብ ሲያልቅ ሥራቸው እዚያው ላይ ያቆማል፡፡ ስለዕውነት «ሀሁን ሳይጨርሱ ሁሉን ያወቁ ይመስላቸዋል፡፡ መዝሙር 1፲19:130.GWAmh 48.4

    ለሥራው ሆነ ለራሳቸው አንድ ፋይዳ (ጥቅም) ሳይውሉ፣ ሲወድቁ ሲነሱ ይኖራሉ፡፡ የቀዘቀዘውን ኃይላቸውን ለሥራው ለሟሟቅ ወይም ብቁ ሠራተኞች ሆነው ለመኖር በቂ ጥረት አያደርጉም፡፡ ጥሩ ዕቅድ ለማቀድ በነገሩ ስለማይቸገሩበት ሥራቸው በእየአቅጣጫው ጉድለት ሞልቶበታል፡፡GWAmh 48.5

    አንዳንዶቹማ በነገሩ ተስፋ ቀርጠው ወደሌላ የሥራ መስክ ይሰማራሉ፡፡ ከመሰላሉ ሥር ጀምረው ቀስ በቀስ በትዕግሥት ሰመውጣት አቅደው ቢሆን ኖሮ ጠቃሚ ሠራተኞች በመሆን ሰራሳቸው ደስታን፣ ለአምላካቸው ክብርን ባተረፉ ነበር፡፡GWAmh 49.1

    ለመድኃኒታችን ለመሥራት የሚሰለፉ ሰዎች በተወሰነው በራሳቸው ዕውቀት ከተመኩ ደግሞ አይሳካላቸውም።: በዚያ ፋንታ ራሳቸውን ናቅ አድርገው በእግዚአብሔር ተስፋ በሙሉ ቢተማመኑ ፈጽሞ አይተዋቸውም፡፡ «በእግዚአብሔር በፍጹም ልብህ ታመን፤በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፣ በመንገድህ ሁሉ እርሱን ዕወቅ፣እርሱም ጎዳናህን ያቃናልሃል፡፡» (ምሳ.3፡5-6) በጠቢብ መሪ የመመራት መብት አለን::GWAmh 49.2

    እግዚአብሔር ዝቅተኛ ሰዎችን ለሥራው ታላቅ ሊያደርጋቸው ለተጠሩት ግዳጅ በፈቃደኝነት የሚታዘዙና ያላቸውን ችሎታ የሚያሻሽሉ ከሆኑ መለኮታዊ ዕርዳታ መቀበላቸው አያጠራጥርም፡፡ የቻሉትን ያህል ሠርተው የቀረውን ለእግዚአብሔር አደራ ለሚሰጡ ሰዎች፤ መላአክት ይረዱአቸው ዘንድ ይላኩላቸዋል፡፡ ለእግዚአብሔር ሥራ ለመሰለፍ የቆረጡ ሰዎች መጀመሪያ የራሳቸውን አምነት መጽናት በደንብ ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡ የተደላደለ ጨዋ ጠባይ የሌለው ለጌታ ሥራ ክብር ሊሆን አይችልም::GWAmh 49.3

    እያንዳንዱ ሠራተኛ ልቡ ንጹህ፣ ባፉ ጸያፍ ነገር የማይወጣ መሆን ተገቢው ነው፡፡ አንዲሳካለት ከፈለገ ክርስቶስን በጐኑ ማሰለፍ አንዳለበትና ምንም ከሰው ቢሰወር እያንዳንዱ የኃጢዓት ሀሳብ በክርስቶስ ዘንድ ግልጽ መሆነን ማወቅ አለበት፡፡GWAmh 49.4

    ኃጢዓት በሰው የነበረውን መለኮታዊ መልክ አበላሽቶታል፡፡ ነገር ግን በክርስቶስ በኩል፤ የተነጠቅነው መብት ሊመሰስልን ይችላል፡፡ መለኮታዊ ሀይል ለመጐናጸፍ ልባዊ ፀሎት ተፈላጊ ነው፡፡ ዕውነተኛዎቹ የአምላክ የወይን ቦታ ሠራተኞች፣ ጸሎትኛች፣ ራሳቸውን ፣አማኞች ፍቅርና ፍላጐት ያላቸው ናቸው፡፡ እንደነዚህ ያሉ ሰዎች በኑሮአቸው ለክርስቶስ ይሠሰክራሉ፡፡ የሥራቸው ውጤትም ያምርላቸዋል፡፡GWAmh 49.5

    ክርስቶስ «ምንም ልታደርጉ አትችሉም” : መለኮታዊ ፀጋ አስገራሚ የማዳን ኃይል : ያለ እርሱ የሰብዓዊ ጥረት ሁሉ ከንቱ ነው፡፡GWAmh 50.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents