Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለወንጌላዊያን ተገቢ ዋጋ

    በወንጌል ሥራ የተሰለፉ ሁሉ ለሥራቸው ተገቢ ዋጋ መቀበል አለባቸው፡፡ ሙሉ ጊዜአቸውን፣ ሀሳባቸውን ጥረታቸውን ለጌታ ሥራ ያውላሉ፡፡ የሚከፈላቸው አበል የቤተሰባቸውን ፍላጎት የማያሟላ እንዲሆን እግዚአብሔር አይፈቅድም።፡ ድርሻውን አንደ ችሎታው የሚሠራ ወንጌላዊ የሚገባውን ያግኝ፡፡GWAmh 300.1

    የያንዳንዱን ሠራተኛ አበል የሚወሰኑ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር መማክር አለባቸው፡፡ በገንዘብ ውሳኔ ወይም በደመወዝ ድልደላ የሚሠሩ ሰዎች ማመዛዘን ይጎድላቸዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የኮሚቴው አባሎች የሠራተኛውን የቤተሰብ አቋም ስለማያውቁ በቤተሰቦች ላይ ችግር አንዲመጣ ምክንያት ሆነዋል፡፡ አስተዳደራቸው ሠራተኞቹን ተስፋ ለማስቆረጥ ለሠይጣን አመች ነው፡፡ እንዲያውም ሠራተኞች ሥራውን የተውበት ጌዜ አለ፡፡GWAmh 300.2

    የሠራተኞችን አበል ለመመደብ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ አለበት፡፡ በደመወዝ ድልደላ በኩል የሚሠሩ ሰዎች በሥራው ልምድ ያላቸውና ጠንቅቀው ማሰብ የሚችሉ ይሁኑ፡፡ «አዋቂዎች፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፤ የታመኑ፤ የግፍን ረብ የሚጠሉ» (10. 18:21) ሰዎች መሆን አለባቸው፡፡GWAmh 300.3

    ወንጌላዊ በገንዘቡም ሥራውን እንዲረዳ የሚጠየቅበት ጊዜ ስላለ ይህ ሁሉ ታስቦ የሚበቃውን ያህል ይወስንለት፡፡GWAmh 300.4

    አብዛኛውን ጊዜ በሥራ ላይ መጠለያና የሚበሉት የሚጠጡት ያጡ ድሆችን ያጋጥመዋል፡፡ እርቅናቸውን የሚከድነበትና ራባቸውን የሚያስታግሥበት ሥጦታ መስጠት ግዴታ ይሆንበታል፡፡ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን መሥሪያና ለአዲስ የሥራ ቦታ መቋቋሚያ መዋጮ ሲደረግ ቀዳሚነት አንዲኖረው ይጠበቃል፡፡GWAmh 300.5

    ሚሲዮናዊ የተወሰነ ቦታ ስለሌለው ካገር ወደአገር ቤተሰቡን ማጓጓዝ ይሆንበታል፡፡ የሥራው ዓይነት ይህን አንዲፈጽም ያስገድደዋል፡፡ ይህ የሁል ጊዜ መጓጓዝ፡ በገንዘብ በኩል ይጎዳዋል፡፡ በተጨማሪም ምሣሌ ይሆኑ ዘንድ እርሱ ራሱ ሚስቱና ልጆቹ በንጽህና መልበስ ይኖርባቸዋል፡፡ የሰውነት ይዞታቸው፣ መኖሪያቸው፣፤ አካባቢያቸው፣ ሁሉም ከሚያስተምሩት ዕውነት ጋር ተስማሚ መሆን አለበት፡፡ አርቆ ለሚያያቸው የጸሐይ ብርሃን ይሆኑ ዘንድ ሁል ጌዜ ፈገግታ የማይለያቸውና ደስተኞች መሆን ይገባቸዋል፡፡ ወንድሞችን በየጊዜው ይጋብዛሉ፣፤ ይህም ሌላ ገንዘብ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው፡፡GWAmh 301.1

    ደሞዝ ደልዳይ ኮሚቴ የሚያስፈልገውን በመንሣት ታማኙን ወንጌላዊ ቢያሳዝን ትልቅ ጥፋት ፈጸመ ማለት ነው፡፡ «እኔ እግዚአብሔር ፍርድን የምወድ፤ ስርቆትንና በደልን የምጠላ ነኝ» (ኢሳ. 61:8) ይላል፡፡ ሰዎቹን እርስ በርሳቸው የልግሥና መንፈስ እንዲኖራቸው ይፈልጋል፡፡- ለጥንታዊያን እስራኤሎች የሚከተለውን ሕግ አንደሰጣቸው ሁሉ ይኸው መመሪያ የእግዚአብሔርን ሥራ ለማፋጠን ራሳቸውን ለሰጡ፤ የሰዎችን አስተሳሰብ ከምድራዊነት ወደሰማያዊነት ለመለወጥ በመሉ ኃይላቸው ለደከሙ ሰዎች አበል የሚወሰኑ ሰዎች ችላ ሊሉት አይገባም፡፡» የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሠር፡፡-› ዘ1ኛ. 9፡9፤ ዘዳ. 25፡4)GWAmh 301.2

    በቀን ስምንት የሥራ ሰዓት የሜለው ደንብ በወንጌላዊ ሥራ ቦታ የለውም፡፡ በየትኛውም ሰዓት ራሱን ለሥራ ማዘጋጀት አለበት፡፡ ከሰነፍ መልካም ምሣሌነት ሊሰጥ ስለማይችል ሕይወቱን ብርታቱን ማድከም የለበትም፡ በተለይ የኃላፊነት ሥራ ካለው በልዩ ልዩ ስብሰባዎች እየተገኙ አእምሮ የሚያደክም ሥራ መሥራት ይሆንበታል፡፡ የዚህ ዓይነት ሥራ ላካል ሆነ ለአእምሮ አድካሚ ነው፡፡GWAmh 301.3

    ሥራውን ያስተዋለ ወንጌላዊ የእግዚአብሔር ባሳደራ መሆኑን ያውቃል፡ የእግዚአብሔርን ቃል «ማንን ልላክ ማንስ ይሄድልኛል?» ሲል ሲሰማ አንደ ኢሣይያስ «እኔን ላከኝ›፤ (ኢሳ. 6፡8) ይላል፡፡ እኔ የራሴ ነኝ፣ ደስ ባለኝ ጊዜ የወደድሁትን አሠራለሁ ሲል አይችልም፡፡ ራሱን ለጌታ አገልጋይ አድርጎ ያስረከበ ወንጌላዊ የራሱ አይደለም፡፡ ሥራውን ክርስቶስን መከተል፤ መንፈሱን ቀን በቀን በመቀበል ሳይፈራ ተስፋ ሳይቀርጥ ለርሱ መሥራት ነው፡፡ ወንጌሉን አንዲያዳርስ እግዚአብሔር ስለመረጠው መንገዱን ሳይስት በታማኝነት መሥራት አለበት፡፡GWAmh 302.1

    የዚህን ዓይነት ሥራ ያልሞከሩ፣፤ የእግዚአብሔር ምርጥና ታማኝ ወንጌላዊያንን የማይሠሩ አድርገው የሚገምቱ የእግዚአብሔር ምርጥ ዕቃዎች ሁል ጊዜ ለሥራ ታጥቀው መኖራቸውን አይዘንጉ፡፡ ሥራቸው በሰዓት አይወሰንም፡፡ አበላቸውን ሲደለድሱ ራሳቸውን የሚወዱ ሰዎች በጽሑፍም ሆነ በቃል ያለ አግባብ ቢበድሏቸው ክባድ ስህተት ፈጸመ ማለት ነው፡፡GWAmh 302.2

    በእግዚአብሔር ሥራ ላይ የአስተዳደር ሥልጣን ያላቸው ሰዎች ቅን ትክክለኛ ይሁኑ፡፡ በዕውነተኛ መመሪያ ይመሩ፡፡ የደመወዝ ቅነሳ የሚያስፈልግ ቢታይ የመሥሪያ ቤቱን ሁኔታ የሚገልጽ መግለጫ ታትሞ ይታደል፡፡ በተጨማሪም ሠራተኞቹ በቅናሽ ደሞዝ መተዳደር መቻል አለመቻላቸውን ይጠየቁ፡፡ በአግዚአብኤር ሥራ ውስጥ የሚደረግ ማንኛውም ስምምነት በሰዎች መካከል የተደረገ ቅዱስ ውል ነው፡፡ ሠራተኞችን አንደ ዕቃ ቆጥሮ የፈለገውን ማንም መብት የለውም፡፡ ሰዎች የመናገር የማሰብ ችሎታ ያላቸው ክቡር ፍጥረት ናቸው፡፡GWAmh 302.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents