Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የግል አገልግሎት

    በብዙ ወንጌላዊያን እንደሚታየው ከሥራ ይልቅ ንግግር ይበዛል፡፡ ለነፍሳት ብዙ የግል አገልግሎት ያስፈልጋል፡፡ ወንጌላዊው ክርስቶስ እንደሚራራ ለነፍሳት በመራራት የግል የአምነት ዕድገታቸውን ማጎልመስ አለበት፡፡ የዘለዓለም ሕይወት የሚያገኙበትን ሊያበራላቸው ይገባል፡፡ ልባቸው አንደተዳመጠ አውራ ጎዳና ቢጠብቅም ወንጌልን ከማስተማር ተስፋ መቁረጥ አይገባም፡፡ ክርክርና ምርምር ያልመለሰውን ልብ የክርስቶስ ቃል ያላላዋል፡፡ ስለዚህ የእውነት ሥር ይሰዳል፡፡GWAmh 114.6

    ወንጌላዊነት ሥራ ስብከት ብቻ ሳይሆን የልብ አገልግሉት ነው፡፡ ምድራዊ ቤተ ክርስቲያን ትዕግሥት፣ ልግም የሌለበት ሥራ የሚያሻቸው ኃጢዓተኞች የሚሰበሰቡባት ቦታ ናት፡፡ ክርስቲያኖች ከኃጢዓታቸው ተላቀው ሰሰማይ ቤት ገጣሚ (ተስማሚ) ለመሆን መቻል አለባቸው፡፡GWAmh 115.1

    በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ክርክር፣ ቅናት፣ ጥላቻ ሳይገጥመው ስለማይቀር ወንጌላዊው (ምክትል ጠባቂው) ዘዴኛ መሆን አለበት፡፡ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ መስጠት አይዘንጋ፡፡ ኃጢዓትን ይገሥፅ፣፤ ስህተትን ይረም፤ በንግግሩ ወይም በሥራጦ ክፉን መጥላቱንGWAmh 115.2

    አንዳንድ ሰዎች ወንጌላዊውን ያለሥራው ይወነጅሉት ይሆናል፡፡ በዚህ ጊዜ የሚከተለውን ያስታውስ «ላይኛይቱ ጥበብ ግን ንጽህት ናት በኋላም ታራቂ፣፤ ገር፣ እሽ ባይ፣ ምህረተና በጎ ፍሬ የሞላባት፤ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት:: የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉት ሰዎች በሰላም ይዘራል፡፡» (ያዕ. 3፡17-18)GWAmh 115.3

    የወንጌላዊ ዋና ተግባር «የክርስቶስ ባለጠግነት ለሕዝብ ይሰብክ ዘንድ አንደተሰጠው፣፤ ለዘለዓለም የተሰወረውን የክርስቶስ ምስጢር ምን አንደሆነ ለሰዎች ይገልጥ ዘንድ»፤ መታዘዙን ማወቅ ተገቢ ነው፡ (ኤፌሶን 3፡9) በዚህ ሥራ የተሰለፈ ሰው የራሱን ምቾት ቢመለከት የግል አገልግሎቱን ለሌላ እየተወ በስብከት ብቻ ቢወሰን፣ሥራው በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የለውም፡፡ ክርስቶስ የሞተላቸው ብዙ ነፍሳት በቅን ሠራተኞች እጦት ይጠፋሉ፡፡ የወንጌል መምህር ነኝ ብሎ ሕዝቡን ለማገልገል የሚለግም ከሆነ የሥራው ትርጉም አልገባውም፡፡GWAmh 115.4

    አንድ ወንጌላዊ የጌታን ሥራ በየጊዜው ለማስፋፋት ምሣሌ መሆን አለበት፡፡ በየጊዜው ምሳሌ መሆን ማለት ቦታ ሳይመርጡ፤ ጊዜ ሳይወስነው ለሰዎች ቃለ-እግዚአብሔርን ማሰማትና በሕግና በትዕዛዙ አንዲራመዱ መርዳት ነው፡፡ ብዙ ሰዎች አሁን ጊዜው አይደለም በማለት ነፍሳትን ለመመለስ የሚችሉባቸውን ብዙ ምቹ ጊዜዎች አሳልፈዋል፡፡ ነገር ግን ሕሲናን የሚነካ ተማጽዕኖ መቼ አንደሚሰጥ አይታወቅም፡፡GWAmh 115.5

    «ማለዳ ዘርህን ዝራ በማታም አደራህን አትሰብስብ የትኛው እንደሚበቅል አታውቀምና ወይም ሁሉም ያድጉ ይሆናል፡፡ (መክ 11፡6) የወንጌልን ዘር የሚዘራ ሰው በልቡ ሸክም ይሰማዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜም ድካሙ ከንቱ የቀረ እየመሰለው ይደነግጣል፡፡ ግን እምነት ካለው የዘራው ዘር ሲያፈራ ሊመለከት ይችላል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል «የዘራ በደስታ ያጭዳል» (መዝ. 126፡5) ይላል፡፡GWAmh 116.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents