Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ጠለቅ ያለ ቅድስና ያለፈ ልጋል

    ጊዜው ከፍተኛ ብቁነትና ጥልቅ ቅድስና ያስፈልገዋል፡፡ ኃላፊነት የሚሰማቸው፣ ራስን ማምለክ ያስወገዱ፣ ራሳቸውን ለጌታ ቀድሰው የቀረቡ ሕይወታቸው ከሥራቸው ጋር የተያያዘ፤ ለጌታ በግዴለሽነት የማይሠሩ የወንጌል ገበሬዎችን ያስነሳ ዘንድ ጌታን እለምንአለሁ:: የዌልንግተን መስፍን ክርስቲያኖች አሕዛብን መመለስ ይቻላቸው እንደሆን በሚመካከሩበት ስብሰባ ተገኝቶ ነበር፡፡ ነገሩ መቻል አለመቻሉን የግል አስተያየቱን ይሰጥ ዘንድ መስፍኑ ተጠየቀ፡፡ መስፍኑም «ክቡራን ሆይ! የሰልፋችሁ ዓላማ ምንድነው? መቻል አለመቻሉን አይደለም፡፡ ትዕዛዙን አንደማስተውለው ከሆነ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ አስተምሩ የሚል ነው፡፡ አሁንም መሪውን ቃል ተክተሉ» አላቸው::GWAmh 70.4

    ወንድሞች ሆይ፣ የጌታ መምጫ ስለተቃረበ ኃይላችን በሙሉ በፊታችን የተደቀነውን ሥራ ለማፋጠን አናውለው፡፡ ራሳችሁን በሙሉ ለሥራው ታደርጉ ዘንደ ክርስቶስ ለሰዎች ጥቅምና ሙሉ ጊዜውን፤፣ ሕይወቱን፤ ያለ ኃይሉን በሙሉ : ጠላትን ለመቋቋምና ወደ እርሱ የሚመጡትን ለማስጠጋት ቀኑን በሥራ፣ ሌሊቱን በፀሎት ነበር፡፡ የውኃ ምንጭ ባለበት ለምለም ቄጤማ አንደሚታይ ሁሉ ክርስቶስ ባለበት ምህረትና ደግነት አይጠፋም፡፡GWAmh 70.5

    ባለፈበት ሁሉ ጤናን ይሰጥ፣ ደስታ ይከተለው ነበር፡፡ ሕፃን ሳይቀር ሊያስተውለው በሚችል ቀላል አገላለጽ ቃለ-እግዚአብሔርን ለሕዝብ አስተማረ፡፡ ወጣቶች በመምህርነቱ ሙያ ተስበው አንደርሱ ሰዎችን ለመርዳት ይጓጉ ዕውራንና ደናቁርት እርሱን ሲያገኙ ይደሰቱ ነበር፡፡ ቃሉን ለማያውቁትና ለኃጥዓን ሕይወትን አስገኘ፡፡ በረከቱን በገፍ (በብዛት) ያለማቋረጥ ለገሠ፡፡ በክርስቶስ በኩል ዘለዓለማዊ ሐብት ሆኖ የአብ ሥጦታ ለሰዎች ተሰጠ፡፡GWAmh 71.1

    የእግዚአብሔር ሠራተኞች የራሳቸው አለመሆናቸው የመለዮ ማህተም የታተመባቸው ያህል ሲሰማቸው: በክርስቶስ የመሠዋዕትነት ደም ተረጭተው ራሳቸውን ለመሥዋዕትነት ለማቅረብ የቆረጡ መሆን አለባቸው፡፡ ግን የኃጢዓተኛችን መዳን ከዘለዓለም ጀምሮ አምላክ ያቀደው መሆኑን የሚያምኑ ቁጥራቸው ያንሳል! በዚህ የመጨረሻ አብይ ሥራ ከጌታ ጋር ልብ ለልብ የተሣሠርን ምንኛ እናንሳለን! ላልዳነ ነፍሳት ሊኖር ከሚገባው ፍቅር አንድ አሥረኛው አንኳን አይገኝም፡፡ ብዙ ማስጠንቀቂያ የሚያስፈልጋቸው አያሌ ነፍሳት ቢድኑ ግድ የሌላቸውም በዚያው ልክ ናቸው፡፡ ኤልያስ ከኤልሣዕ ሊለይ ሲል እንዲህ አለው ‹ከአንተ ሳልወሰድ አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምን› ኤልሣዕም «መንፈስህ በእኔ ላይ ሁለት አጥፍ ይሆን ዘንድ እለምንህአለሁ›” (2ኛ ነገ 2:9) አለው፡፡GWAmh 71.2

    ኤልሣዕ ምድራዊ ማዕረግና ሥልጣን አልለመነም፡፡ የጠየቀው አምላክ ሊያሳርገው ከተዘጋጀው የበለጠ የመንፈስ ቅዱስ በረከት: ለታጨበት ሥራ ሌላ ሊጠቅመው የሚችል አለመኖሩን አውቷል፡፡GWAmh 71.3

    የወንጌል ገበሬዎች ሆይ! ይህን ጥያቄ ተጠይቃችሁ ቢሆን ኖሮ መልሳችሁ ምን ይሆን? ለእግዚአብሔር ሥራ ስትሰለፉ ያላችሁ ታላቁ የልብ ምኞት ምንድነው?GWAmh 71.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents