Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 4—ተፈላጊ ግዳጆች

    ራስን ቀድሶ ማቅረብ

    አንድ ወንጌላዊ የተሳካላት ሊሆን ቢፈልግ የመጽሐፍ ዕውቀት ብቻ አይበቃውም፡፡ ቅድስና፤ ትብብር፣ ማስተዋል፤ በርትቶ መሥራት፣ ኃይልና ዘዴ ያስፈልጋል፡፡ እነዚህን ተፈላጊ መታወቂያዎች የያዘ ወንጌላዊ ዝቅተኛ አይሆንም፡፡ በዚህ ፈንታ መልካም አራአያነት አለው:፡GWAmh 68.1

    ክርስቶስ ሀሳቡን በሥራው ላይ አሳርፎ : ሲያከናውነው ለመጣው ሥራ፣ ሁሉንም አስገዛ፡፡ አናቱ ከመምህራን ጋር አግኝታ «ልጄ ሆይ! አባትህ ስንፈልግህ ለምን እንዲህ ሠራህ? ብትለው «ለምን አሻችሁኝ” አባቴን አገለግል ዘንድ አንዲገባኝ አታወቁምን?” አላቸው፡፡GWAmh 68.2

    በክርስቶስ ዘንድ የነበረው የሥራ ስሜት በአገልጋዮቹም ዘንድ ማደር አለበት፡፡ ክርስቶስ የሰላም ቤቱን ትቶ መጣ:: የጠፋውን ዓለም ለማዳን ደሙን አፈስሰሰ፡፡GWAmh 68.3

    አገልጋዮቹም ገበሬዎች መሆን አለባቸው፡፡ አብርሃም የወንጌል ገበሬ እንዲሆን ተጠራ፡፡ «ከቤትህ ውጣ ከዘመዶችህም ተለይ፡፡ ከአባትሀ ቤት ወደ ማሳይህ ቦታ ሂድ:: «የሚሄድበትን ሳያውቅ ወጣ፡፦›” የእግዚአብሔርን ብርሃን የሚያዳርሱ መብራት ተሻካሚ ሆነ፡፡ አገሩን፣ ዘመድ ወዳጆቹን ተወ፡፡ መናኝና መጻተኛ ሆነ፡፡ ዘዘፍጥረት 1፲2፡፡፣ ዕብራዊያን 11:8)GWAmh 68.4

    ሐዋርያው ጳውሉስ በኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ ሲጸልይ «ሂድ፣ እኔ ወደ አህዛብ ከዚህ ወደ ሩቅ አልክህአለሁ፡፡› የሐ. ሥራ 22:2፤ የሚል መልዕክት መጣለት፡፡ ስለዚህ ከክርስቶስ ጋር ለክርስቶስ እንሠራለን የሚሉ ሁሉ ሁሉን ትተው እርሱን መከተል አለባቸው፡፡ የዱሮ አጉል ልምድ ቀርቶ ምድራዊ ሀሳብ በሰማያዊ ዓላማ መተካት: ዘሩ በከባድ ሥራና በእንባ፣ በብቸኝነትና በመሥዋዕትነት መዘራት አለበት፡፡GWAmh 68.5

    አካላቸውን፤፣ መንፈሳቸውንና ነፍሳቸውን ለእግዚአብሔር ያስገዙ ሰዎች የአካል፤ የአእምሮና የመንፈስ ብርታት ይታደላቸዋል፡፡ የማያቋርጠው የሰማይ በረከት ይዘንብላቸዋል፡፡ ክርስቶስ ከሕይወቱ ሕይወት፣ ከመንፈሱ መንፈስ ያካፍላቸዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው ተገኝቶ ታላቅ ሥራ ያሠራላቸዋል፡፡ የእግዚአብሔር ፀጋ ችሎታቸውን፣ ያዳበረላቸውን የመለኮት ዕርዳታ አይለያቸውም፡፡ በሰብዓዊ ደካምነታቸው ተስፋ ሳይቆርጡ ከክርስቶስ ጋር በመተባበር ታላቅ ኃይል ይሠራሉ፡፡GWAmh 69.1

    አዳኛችን በሁለት ልብ የሚሰጥን አገልግሎት አይቀበልም፡፡ የእግዚአብሔር ሠራተኛ ራስን ማስረከብ ምን ማለት አንደሆነ በእየዕለቱ መማር አለበት፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል እያጠና ትዕዛዙን ማክበር አለበት፡፡ እንዲህ በማድረግ ከተፈለገው የክርስትና ደረጃ ሊደርስ ይቸላል፡፡ በፈተና ጊዜ ጸንቶ መቆም የሚያስችለውን ጠባይ ክርስቶስ ቀስ በቀስ ይሰጠዋል፡፡ አማኙ ቀን በቀን ወንጌል የወደቀውን ሰው ከምን ደረጃ ሊያደርስ አንደሚችል በሰዎችና በመላዕክት ፊት ይመሰክራል፡፡ ክርስቶስ ደተመዛሙርቱን አንዲከተሉት ሲጠራቸው የሚያስጐመጅ ተስፋ በመስጠት አላባበላቸውም፡፡GWAmh 69.2

    በዓለም ትርፍ ወይም ክብር አንደሚጉናጸፉ ተስፋ አልሰጣቸውም፡፡ ማቴዎስ ከመንገድ ዳር ተቀምጦ ቀረጥ ሲሰበስብ ጌታ «ተከተለኝ» (ማቴ 9፡9) አለው፡፡ ማቴዎስ በቀራጭነት ከሚያገኘው የበለጠ ደሞዝ አንደሚያገኝ ተስፋ አልተሰጠውም፡፡- ያለምንም ጥያቄና ማወላወል የሱስን ተከተለ፡፡ ከመድኃኒታችን ጋር ሆኖ ቃሉን መስማትና በሥራ መተባበር በቂው ነበር፡፡GWAmh 69.3

    ከዚያ በፊት የተጠሩት ደቀመዛሙርትም ከዚሁ የተለዩ አልነበሩም፡፡ ጴጥሮስና ጓደኞቹ ሲጠሩ ጀልባቸውንና መረባቸውን ትተው ተከተሉት፡፡ ከእነዚህ ደቀመዛሙርት መካከል ዕርዳታቸውን የሚሹ ዘመዶች ነበሯቸው፡፡ ግን ክርስቶስ ሲጠራቸው «ዘመዶቼን ማን ይረዳልኛል?” አላሉም፡፡ ጥሪውን ተቀበሉ፡፡ የሱስ ቆየት ብሎ ‹ያለኮሮጆና ያለከረጢት ያለማጭድም በላክኋችሁ ጊዜ አንዳች ጐደለባችሁን?» ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ «ምንም አልጐደለብንም» (ሰ.ቃ. 22:35) ሲሉ መለሱ፡፡GWAmh 69.4

    ማቴዎስን፤ ጴጥሮስንና ዮሐንስ ለሥራው አንደጠራ ሁሉ ጌታ ዛሬ እኛንም ይጠራናል፡፡ ልባችን በክርስቶስ ከተነካ «ምን ይከፈለኛል?” የሚለው ጥያቄ በአእምሮአችን ውስጥ ቦታ የለውም፡፡ ከክርስቶስ ጋር መስራት ደስ ይለናል፤ በእርሱ ሳይ እንተማመናለን፡፡ እግዚአብሔርን ብርታታችን ካደረግን፣ የሥራችን ዋና ዓሳማ ይገባናል፡፡ ለራሴ የሚለው ስሜት ይለቀናል፡፡GWAmh 70.1

    አብዛኛዎቹ እግዚአብሔር ሲፈልጋቸው ከእርሱ ድምፅ ይልቅ የሌሎችን ያዳምጣሉ::: እራስ ወዳድ ልምድ ወደኋላ ወጥሮ ይይዛቸውና ከአምላካችን ጋር ጥብቅ ግንኙነት ሳያደርጉ ይቀራሉ፡፡GWAmh 70.2

    ሰዎች ለእግዚአብሔር ሥራ ከዘመድና ከወዳጅ ፍቅርና ምክር ይልቅ ከፍተኛ ቦታ ቢሰጡት እንዴት በተባረኩ!GWAmh 70.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents