Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የሥራ ስብሰባዎች

    በሥራ በማህበራዊም ሆነ በመንፈሣዊ ስብሰባዎቻችን የሱስ መሪያችንና መካሪያችን ይሁን፡፡ የመድኃኒታችን ባጠገባችን መገኘት ከተሰማን ዋዘኞች አንሆንም፡፡ ራሳችን ከፍ ከፍ አናደርግም፡፡ ሊሠራ የታቀደውን ሥራ ከፍ አድርገን አንገምተዋለን፡፡ ሥራውን የጥበብ ሁሉ ምንጭ እንዲመራ እንፈቅዳለን፡፡GWAmh 298.1

    ዓይኖቻችን እንደሚገባው ቢከፈቱ ኖሮ የሰማይ መልዓክት በስብሰባችን መካከል በታዩን ነበር፡፡ እንዲህ ከሆነ ለስብሰባችንና ለሥራችን መበላሸት ምክንያት የሚሆኑትን ጥቃቅን ነገሮች ቦታ ባልሠጠናቸውም ከልብ ብንጸልይ ኖሮ፣ ለከፍተኛ ነገሮች ታላቅ ግምት ሰጥተናቸው ቢሆን ኖሮ የሥራ ስብሰባችን ከፍተኛ ለውጥ ባስገኘ ነበር፡፡ ስብሰበባው ሥራውን ለማራመድ መሰብሰቡንና ዋና ዓላማው ነፍሳትን ማዳን መሆኑን ሁሉም በተገነዘቡ ነበር፡፡GWAmh 298.2

    የምንሥራውና የምናደርገው ሁሉ በሰማይ መጽሐፍ ይመዘገባል፡፡ የእግዚአብሔርን ሥራ አንደ ተራ ሥራ ዝቅ አድርገን በመገመት ወንጀል አንፈጽም፡፡ ደረጃችን ከፍ አድርገን አስተሳሰባችን ማሳደግ አለብን፡፡GWAmh 298.3

    ጥቂቶች ሰዎች ወንድሞቻቸው ወደፊት ሲገፉ እነርሱ ወደኋላ መጎተት ሥራቸው ነው፡፡ የተሰጠውን አስተያየት ሁሉ ይቃወማሉ፤ ራሳቸው ያላመነጩትን ማንኛውንም ዕቅድ ይጻረራሉ፡፡ ራሴ አውቃለሁ የሜል መንፈስ ያድርባቸዋል፡፡ ትሁትና ገር መሆንን ከክርስቶስ አልተማሩም፡፡ ለሀሳበ-ግትር ሰዎች የራሳቸውን ሀሳብ ትተው የሌሎችን አስተያየት ከመቀበል የበለጠ ጭንቅ ነገር የለም፡፡ እንደነዚህ ያሉትን ሰዎች ማስተማር፣ ጨዋ ማድረግንና ለመቀራረብ ችግር ነው፡፡GWAmh 298.4

    በሥራ ስብሰባችን በማይጠቅም ነገር በመከራከር ጊዜ አንዳይጠፋ ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ያልሆነ መነቃቀፍ ይወገድ፤ ምክንያቱም አለመግባባትን ፈጥሮ ሳይታወቅ ግልጽ የሆኑትን ነገሮች ምስጢር ያስመስላል፡፡ በወንድሞች መካከል ሌላውን ከራስ አብልጦ የሚያስገምት ፍቅር ካለ መግባባትና የራስን ፈቃድ መተው ቀላል ነው፡፡ በየቀኑና በየሰዓቱ ክርስቶስ እኔና አብ አንድ እንደሆንን ደቀመዛሙርቴም አንድ ይሁኑ ያለው ጸሎቱ እንዲፈጸም ምክንያት እንድንሆን ማሰብ ይገባናል፡ የጌታችን ጸሎት በማስታወስና እንደፈቃዱ ለማድረግ በመሞከር ከፍተኛ ትምህርት ልንማር እንችላለን፡፡GWAmh 299.1

    በሥራ ስብሰባችን ጊዜ የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ እንዳናነሳ መጠንቀቅ አለብን፡፡ ሀሳብ ስናቀርብ አንድ ጊዜም ቢሆን የእግዚአብሔርን ስም ሳያስፈልግ ማውሳት የለብንም፡፡ በምንም መንገድ ቢሆን አክብሮት፣ ጽናትና ዕውነተኛነት ሊከበሩ ይገባል፡፡ አሳባችን፣ ሥራችንና አነጋገራችን እንደ ክርስቶስ ፈቃድ መሆን ይገባዋል፡፡GWAmh 299.2

    የእግዚአብሔርን ሥራ ለመሥራትና ለማሰብ ተሰልፎ ግልፍተኝነት ነው፡፡ ክርስቶስ ስብሰባውን አንዲመራ፤ ጥበቡን፣ ጸጋውንና ጽድቁን አንዲሰጥ ተጸልዮአል። ሥራውን የሚቃወምና መንፈሱን የሜያሳዝን ስራ መፈጸም ታዲያ አይገባም፡፡GWAmh 299.3

    የሱስ በመካከላችን አንዳለ ሆኖ ይሰማን፡፡ ያን ጊዜ በስብሰባው ውስጥ ከእግዚአብሔር መንፈስ ብቻ የሚገኝ ከፍተኛና ራስን የመግታት ስሜት ይገኛል፡፡ «ክስማይ የመጣው ንጹህና ታራቂ የሆነ በምህረትና በፍሬ የሞላ የማይሳሳት ጥበብ» ይገኛል፡፡ በውሳኔውና በዕቅዱ ውስጥ በሙሉ «የራሷን የማትሻ፣ በቀላል የማትቆጣ፤ ክፉ የማታስብ፣ በዕውነት አንጂ በኃጢዓት የማትደሰት፣ ሁሉን የምታምን፣ ሁሉን የምትታገሥ፤ ሁሉንም ተስፋ የምታደርግ፤ ፍቅር» ዘ1ቆሮ. 13፡5-7) ትገኛለች፡፡GWAmh 299.4

    በስብሰባው ተካፋይ የሆነው ሁሉ በልቡ «ለዘለዓለም አሠራለሁ፤ ለምሠራው ሥራ ሁሉ በአግዚአብሔር ዘንድ ኃላፊነት አለብኝ» የሚል ቃል ይጻፍበት፡፡ ዓላማው ይህ ይሁን፤ ዳዊት የጸለየውን ጸሎት ይጸልይ ፡፡ «አቤቱ ጠባቂ አነር የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ፣ ልቤን ወደክፉ ነገር አትመልሰው፡፡ ዓመጽን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ለኃጢዓት ምክንያት እንዳልሰጥ ከምርጦቻቸው ጋር አልተባበር፡፡› (መዝ. 141:3-4)GWAmh 299.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents