Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ልጆችን ማስተማር (ለልጆች መስበክ)

    በማንኛውም አጋጣሚ የየሱስ የፍቅሩ ታሪክ ተደጋግሞ ይነገራቸው፡፡ በማንኛውም አገልግሉት ለእነርሱ የሚሆን ትምህርት ሳይሰጥ አይታለፍ፡፡ የክርስቶስ አገልጋይ ከእነርሱ ጋር የማይረሳ ወዳጅነት ሊኖረው ይገባል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀታቸው የላቁ እንዲሆኑ ከማስተማር አይቦዝን፡፡ ይህ ዘዴ ከተገመተው በላይ የሰይጣንን አካሔድ ያደናቅፍበታል፡፡ ልጆች ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በደንብ ከተዋወቁ ተጠራጣሪነት አያጠቃቸውም፤ ጠላትን «ተጽፏል” በሚል ጋሻ ሊከላከሉት ይችላሉ፡፡GWAmh 130.5

    ወጣቶችንና ልጆችን የሚያስተምሩ ሰዎች አሰልቺ ንግግር ከማድረግ መቆጠብ አለባቸው፡፡ ንግግራቸው አጠር መጠን ብሎ ተፈላጊውን ትምህርት ያጠቃለለ ይሁን:: ብዙ ሊሰጥ የሚገባው ትምህርት ካለ ከፋፍሎ ማስተማር ነው፡፡ ሁሉን ትምህርት በአንድ ጊዜ ከመጫን በየጊዜው እየከፋፈሉ ማስተማር ዋጋ አለው:: ረዥም ንግግር የወጣቶችን አእምሮ ያደክማል፡፡ ብዙ ንግግር መንፈሳዊ ትምህርትን አንዲጠሉ ደርጋቸዋል።፡ ልክ ከመጠን በላይ ሲበሉ አህል አንደሚያስጠላ ማለት ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ትምህርታችን በተለይ ለወጣቶች የሚሰጠው ከዚህ ትንሽ ከዚያ ትንሽ፣ መስመር በመስመር ቃል በቃል ላይ መሆን አለበት፡፡ ልጆችን ወደሰማይ ለማቅረብ የሚረዳ , ግልምጫ ሳይሆን ፍቅርና ደግነት ነው፡፡GWAmh 131.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents