Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ላለማወቅ (ለድንቁርና) ምክንያት የለም

    አንዳንድ ወንጌላዊያን- የኃላፊነታቸው ከባድነት አይሰማቸውም፡፡ የወንጌላዊነት ብቁነታቸው የተሳሳተ ነው፡፡ ወንጌላዊ ለመሆን መጠነኛ የሰነፍ ጥረትና የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት በቂ ይመስላቸዋል፡፡ ኣንዳንድ ወንጌላዊያን አንድ ጥቅስ በቃላቸው መጥቀስ አይችሉም፡፡ የእግዚአብሔር ቃል አንደፈለጉ በማወላገድ ኃጢዓት ይሠራሉ፡፡ «ያልተጻፈ በማንበብ” የመጽሐፍ ቅዱስን ትክክለኛ ትርጉም ያበላሻሉ፡፡GWAmh 64.4

    አንዳንዶቹ «አንድ ሰው መንፈስ ቅዱስ ካደረበት መጽሐፍ አዋቂነቱ እምብዛም ተፈላጊ አይደለም” ይላሉ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ድንቁርናን ለመካስ መንፈሱን አይልክም፡፡ ለመማር አድል ያላገኙትን ይባርክ ይሆናል፡፡ ደካምነታቸውንም በብርታቱ ይደግፍላቸዋል፡፡ ቢሆንም ማንም ቃለ-እግዚአብሔርን የመማር ግዳጅ አለበት፡፡ በሳይንስ አለመራቀቅ የመጽሐፍ ቅዱስን ጥናት ችላ ለማለት ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት የሳይንስ ዕውቀት የሌለው ሰው አንብቦ ሊረዳው ይችላል፡፡GWAmh 65.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents