Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከቤተሰብ ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ

    ..….. …... …….ከሰማይ የተሰጠ መምሪያ ነው፡፡ በዚህ የሥራ መስክ ሰዎችን ለመርዳት የሚሰለፉ ወጣቶች አሉ፡፡ በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የሰለጠኑ ሰዎች ለእግዚአብሔር ታማኝ ሠራተኞች ይሆናሉ፡፡ በዚህ መንገድ በሽህ የሚቆጠሩ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ይሰማሉ:: ወንጌላዊያንም ከሰዎቹ ጋር በበለጠ ይተዋወቃሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በቤተሰብ ውስጥ ሲነበብ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይተዋወቃል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን አንብቦና ተመራምሮ መቀበል ወይም መንቀፍ የእያንዳንዱ ሰው ኃላፊነት ነው:: እግዚአብሔር ለስሙና ለክብሩ የሚደረገውን ማንኛውንም ጥረት ያለዋጋ አይተወውም፡፡GWAmh 119.2

    በማንኛውም አዲስ ሥራ ትእግስትና አለመሰልቸት ተፈላጊነታቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ በቀላሉ ተስፋ መቁረጥ የሥራ እንቅፋት ነው፡፡ በትንሹ የተጀመረ ሥራ አብዛኛውን ጊዜ ታላቅ ውጤት ያስገኛል፡፡ ከሰዎች ጋር ግልጽ ግንኙነት እንዳደረግን መጠን ሥራችን እየተስፋፋ ይሄዳል፡፡ የግል ምሣሌነት ኃይል አለው፡፡ አብረውን የሚኖሩ ሰዎች በማይታዩ መልካም ምሣሌነታችን ይሳባሉ፡፡ የቅርብ መተዋወቅ ከሌለው አንድ ሰው ሰዎችን ወደፈለገው መንገድ ሲመራቸው አይችልም፡፡ ክርስቶስ ነፍሳትን ለማዳን ሰማይን ለቆ መጣ፡፡ የምትሠራላቸውን ሰዎች በድምጽህ ብቻ ሳይሆን በአነጋገርህ፣በሥራህ፣ በመሪነትህ ሊያውቁህ ይገባል፡፡GWAmh 119.3

    ወንጌላዊያን ወንድሞች ሆይ፣ ነፍሳትን የምትረዱበትና፤ ሥራችሁን የምታከናውኑበት መንገድ ንግግር ብቻ አይምሰላችሁ፡፡ ከሁሉም የበለጠ ልታከናውኑት የሚገባ ተግባር ማስተማርና ማሠልጠን ነው፡፡ ዕድል ባጋጠማችሁ ቁጥር ከየቤተሰቡ ጋር በመቀመጥ መጽሐፍ ቅዱስን ማስጠናት ችላ አትበሉ፡፡ ከስብከቱ የሚጠየቁትን ጥያቄ ሁሉ በትዕግሥት መልሱላቸው፡፡ ከስብከቱ ቀነስ አድርጋችሁ ከማስተማሩ ላይ : ከቤተሰብና ከአነስተኛ ጉባኤ ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብና መጸለይን አትርሱ፡፡GWAmh 119.4

    ከክርስቶስ ጋር በሕብረት የምትሠሩ ሰዎች ሁሉ ባጋጠማችሁ ጊዜ ሁሉ በምድጃ ዙሪያም ቢሆን ቃለ-እግዚአብሔርን አስተምሩ፡፡ ቅዱሳችሁን አንስታችሁ በውስጡ ካለው የእውነት ምንጭ አጠጡአቸው:: የሚሳካላችሁ በእውቀታችሁ መጠን ሳይሆን ሰዎችን ስትቀርቡ ባላችሁ የአቀራረብ ዘዴ ነው፡፡GWAmh 120.1

    በንግግር ከምታደርጉት ይልቅ አብሮ በመኖርና በመተዋወቅ የሰዎችን ልብ ወደ እውነት መመለስ ትችላላችሁ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ለብዙ ጉባኤ ከሚሰጠው ትምህርት ይልቅ ለጥቂት ሰዎችና፤ ለቤተሰብ፣ የሚሰጠው ትምህርት ነፍሳትን ወደ ክርስቶስ ለመመለስ የበለጠ ኃይል አለው፡፡GWAmh 120.2

    በዚህ ሥራ የሚሰለፉ ሰዎች ሥራቸው የተለምዶ እንዳይሆንባቸው መጠንቀቅ አለባቸው፡፡ በየጊዜው ያለማቋረጥ መማር አለባቸው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ እውቀታቸው የዳበሩ ሰዎች ይሆኑ ዘንድ ለከፍተኛ ብቃት መጣጣር አለባቸው:: አእምሮአቸውን ሰፋ ባለ አስተሳሰብና ምርምር ማሰልጠን ተገቢ ነው፡፡ በተለይ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና በጸሎት መትጋት ይገባል፡፡GWAmh 120.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents