Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የቤተ ክርስቲያን መልካም ጠባይ (መተራረም)

    የተሳሳቱን የቤተ ክርስቲያን አባሎች ለመቅረብ ወይም ሰመቆጣጠር የእግዚአብሔር ሰዎች በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ አሥራ ስምንት የተሰጠውን ምክር ይከተሉ፡፡ (ማቴ. 18፡15-18)GWAmh 334.2

    ሰብዓዊ ፍጡር በከበረ ዋጋ የተገዛ፣ አብና ወልድ በገለጡለት ፍቅር የታሰረ የክርስቶስ ሀብተ ነው፡፡ እርስ በርሳችን በምናደርገው አቀራረብ በጣም መጠንቀቅ አለብን፡፡ ሰዎት በባልንጀሮቻቸው ላይ ክፋትን መተብተብ የለባቸውም፡፡ የተሳሳቱን ለማረም የቤተ ክርስቲያን አባሎች በስሜታቸው ብቻ መመራት የለባቸውም፡፡ ስለተሳሳተው ሰው የጥላቻ መንፈስ ማሳየት የለባቸውም፡፡ እንዲህ ካደረጉ በሌሎች ሰዎች አእምሮ- ውስጥ የክፋት ጩመሩ ማለት ነው፡ ስለወንድሞችና አህቶች የሚነገሩ መጥፎ ወሬዎች ካንዱ የቤተ ክርስቲያን አባል ወደሌላው ይነፍሳሉ፡፡ ክርስቶስ የሰጠውን መመሪያ ለመከተል ባለመፍቀድ ስህተት ይፈጸማል፣ ያልቀና ነገርም ይሠራል፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ የሚከተለው ነው «ባልንጀራህ ባሳፈረህ ጊዜ አንዳትጸጸት ለክርክር ፈጥነህ አትውጣ፡፡ ክርክርህን ከባልንጀራህ ጋር ተከራከር የሌላ ሰው ምስጢር ግን አትግለጥ፡፡ የሚሰማ አንዳይነቅፍህ፡፡› ምሳ. 25፡8፣9 ነገሩ ካንዱ ወደሌላው የተራባ አንደሆነ ያልሰማው እየሰማ ችግሩ የቤተ ክርስቲያኑ አባሎች በሙሉ ሊሆን ይችላል፡፡ ወንድምህ ኃጢዓት እንዲሠራ አትፍቀድለት፤ ግን ነቀፋው የጥላቻና የበቀል እንዳይመስል አታጋልጠው። በእግዚአብሔር ቃል እንደተመለከተው አድርገህ ለማረም ሞክር፡፡GWAmh 334.3

    ቅሬታ ወደጥላቻ አንዲለወጥ ምክንያት አትሁን፡፡ ቁስሉ በመርዘኛ ቃላት አንዲያመረቅዝና የሚሰሙትን ሁሉ አእምሮ እንዳይበክል ተጠንቀቅ፡፡ መጥፎ መጥፎ ነገር ባንተም በርሱም አእምሮ አንዳያድር አስብበት። ወደ ወንድምህ ሄደህ በትህትናና በዕውነት ስለነገሩ ተነጋገሩበት፡፡GWAmh 335.1

    ቅሬታው ምንም ዓይነት ቢሆን ጌታ በፈቀደው መንገድ ሊመራ ይችላል፡፡ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ሰውየውን ለብቻ ማነጋገር ችግርን ያቃልላል፡፡ በክርስቸችስ ፍቅር ልብህን ሞልተህ ወደ ተሳሳተው ሰው ሂድና ነገሩን ለማስተካከል ሞክር፡፡ በለዘብታና በጸጥታ አወያየው፡፡ ከከናፍርህ የቁጣ ቃላት አይውጣ። በሚያስተውለው መንገድ ቅረበውና አወያየው፡፡ «ኃጢዓተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልስ ነፍሱን ከሞት አንዲያድን የኃጢዓትንም ብዛት አንዲመልስ ይወቅ፡» (ያዕ. 5፡ 20) የሚለውን የሐዋርያውን አነጋገር አትርሳ፡፡GWAmh 335.2

    የወንድምህን የጥላቻ ቁስል ሰመፈወስ ሞክር፡፡ በበኩልህ የቻልከውን ያህል እርዳው፡፡ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ስትል ይህን ማድረግ ከመብትና ከግዴታ ቁጠረው፡፡ ከሰማህ ወዳጅህ አደረግኸው ማለት ነው፡ በበደለና በተበደለ በሚደረግ ሰላማዊ ውይይት የሰማይ ሠራዊት በሙሉ ይደስሰታል፡፡ የተሳሳተው በክርስቶስ ፍቅር የተነገረውን ተግሣጻዊ ምክር ተቀብሎ አግዚአብሔርንና የተበደለውን ወንድሙን ይቅርታ ሲጠይቅ ሰማያዊ ብርሃን በልቡ ውስጥ ያበራል፡፡GWAmh 335.3

    ክርክር ተወግዶ ወዳጅነትና መተማመን ይሰፍናል፡፡ በስህተት የተፈጠረውን አለመግባባትና ቁስል የፍቅር ዘይት ያለዝበዋል፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅር ልብ ለልብ ስላገናኛቸው በሰማይ የደስታ ሙዚቃ ያስተጋባል፡፡GWAmh 335.4

    እነዚህ በክርስትና ወንድማማኝችኝነት አንድ የሆነ ሰዎች ሲጸልዩና ለመግባባት፣ ምህረትን ለመውደድ፤ ከእግዚአብሔር ጋር በትህትና ለመራመድ ቃል ኪዳን ሲገቡ ከሰማይ ታላቅ በረከት ይወርድላቸዋል፡፡ ሌሎፕንም በድለው አንደሆን ይናዝዘዛሉ፣ ይመለሳሉ፣ ይግባባሉ፣ አንዱ ሰሌላጡ መልካም ለመሥራት ይፈልጋሉ፡፡ የክርስቶስን ሕግ መፈጸም ማለት ይህ ነው፡፡GWAmh 336.1

    «አንተን ባይሰማህ ግን ሌሳ ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ይዘህ ሞክረው፤ በሁለት ወይም በሦስት ሰዎች ምስክርነት ነገር ትጸናለችፍ » ካንተ ጋር መንፈሳዊያን ሰዎች ወጠስደህ የበደለህን ሰው ምከሩት፡ ወንድሞቹ በንብረት ሲማጽኑት ይሰማ ይሆናል፡፡ እነርሱ በነገሩ ሲስማመብት ሲያይ ነገሩ ሊስተዋለው ይችል ይሆናል፡፡GWAmh 336.2

    «እነርሱንስ ባይሰማ» ምን ማድረግ ይቻላል? ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአንድ ኮሚቴ አባሎች የሆኑ ሰዎች ብቻ በሥልጣናቸው ከአባልነት አነሱን ባይሰማ ለቤተ ክርስቲያን ንገር፡፡ ስለአባሎቿ አንድ ነገር ማድረግ የምትችል ቤተ ክርስቲያን ብቻ ነኘ፡፡GWAmh 336.3

    «ቤተ ክርስቲያንን እንቢ ካለ አንደኃጢዓተኛና እንደቀራጭ ቁጠረው፡፡ ›: የተሰጠውን ምክር ሁሉ ካልተቀበለ፤ ቤተ ክርስቲያን አንዲመለስ ያደረገትለትን ጥረት ለመቀበል አሻፈረኝ ካለ ከአባልነት የማሰናበቱ ኃላፊነት በቤተ ክርስቲያን ላይ ተጥሏል፡፡ ከዚያ በኋላ ስሙ ከመዝገብ መፋቅ አለበት፡፡GWAmh 336.4

    ክርስቶስ ያዘዘው ትዕዛዛዊ ምክር ከመሰጠቱ በፊት አንድ ጥፋት የፈጸመ ክርስቲያን ከቤተ ክርስቲያን አባልነት እንዲሰናበት የቤተ ክርስቲያን ባለሥልጣን ሊያዝ፣ ኮሚቴ ሊወስን፤ ቤተ ክርስቲያንም ልትወስን አይገባም፡፡ ግን ሥርዓቱን የተከተለ ተግባር ከፈጸመች ቤተ ክርስቲያን በአግዚአብሔር ፊት ንጹህ ሆነች ማለት ነው፡፡ ክፉ በክፋቱ ታውቆ እንዳይስፋፋ ይሆናል፡፡ በክርስቶስ ፊት ንጽህት በጽድቅ መጎናጸፊያ የተጎናጸፈች ሆና ትቆም ዘንድ የቤተ ክርስቲያን ደህንነት መጠበቅ አለበት፡፡GWAmh 336.5

    የተሳሳተው ቢመለስና ለክርስቶስ ቢያድር ሴላ ሙከራ ይሰጠው፡፡ ባይመለስና ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ቢሆንም አንኳ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ለርሱ የሚፈጽሙለት ሥራ አለባቸው፡፡ አንዲመለስ ከልባቸው ሊደክሙለት ይገባል፡፡GWAmh 337.1

    ምንም ያህል ጥላቻው የከረረ ቢሆን የመንፈስ ቅዱስን ምክር ተቀብሎ ኃጢዓቱን የመተው ምልክት ከታየበት ይቅርታ ተቀብሎ ከመንጋው ሊቀላቀል ይችላል፡፡ ወንድሞች በቀና መንገድ ሲቀርቡትና ሊያደፋፍሩት ይገባል፡ እነርሱ ራሳቸው እንደርሱ ቢሆኑ ሰዎች ሊመሰከቷቸው በሚፈልጉት መንገድ ይመልክቱት፡፡GWAmh 337.2

    ክርስቶስ «ዕውነት ዕውነት እላችሏጊለሁ፣ በምድር ያሰራችሁት በሰማይ የታሠረ ይሆናል፤ በምድር የፈታችሁትም በሰማይ የተፈታ ይሆናል» ሲል ንግግሩን ይህ አነጋገር በበመናት ሁሉ ሥልጣን አለው፡፡ ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ፈንታ የመሥራት መብት ተሰጥቷታል፡፡ ሕግንና ሥርዓትን በሕዝቡ መካከል ለማስከበር የእግዚአብሔር መሣሪያ ናት፡-፡ አምላክ ንጽህናዋን፣ ብልጽግናዋን፣ ሥርዓቷን የሚነካውን ነገር ሁሉ መፍትሔ እንድታገኝለት ለቤተ ክርስቲያን ሥልጣን ሰጥቷታል፡፡ በማይገባ ከክርስትና ውጭ በሆነው አድራጎታቸው ዕውነትን የሚያዋርዱትን ሁሉ ከማህበሯ እንድታገልል (እንድታባርር) ሥልጣንና ኃላፊነት ተጥሎባታል፡፡GWAmh 337.3

    የእግዚአብሔርን ትፅዛዝ በመከተል ቤተ ክርስቲያን የምትፈጽመውን ሥራ በሙሉ ሰማይ ያጸድቀዋል፡፡GWAmh 337.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents