Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ጥብቅ ግዴታ

    አሥራት የተቀደሰ የእግዚአብሔር ሀብት ነወ፡፡ የወንጌል ሠራተኞችን ለመርዳት ወደ መዝገብ ቤቱ መሰበሰብ አለበት፡፡ ብዙዎች አሥራት የእግዚአብሔር ሀብት መሆኑን ስለዘነጉ ብዙ ጊዜ ተቀምቶአል፡፡ አንዳንድ ሰዎች «የእግዚአብሔር ሥራ በደንብ አልተካሄደምና ከእንግዲህ አሥራት አልከፍልም» ይላሉ፡፡ ነገር ግን ሥራው በደንብ ያልተካሄደ ስለመሰለህ እግዚአብሔርን መቀማት ትክክል ነው እንዴ? አቤቱታህን በትክክለኛው መንገድ ለሚመለከታቸው ሰዎች አቅርብ፣ ሊታረሙ የሚገባቸውን ነገሮች ማመልከት አንጂ ሌሎች ተሳሳቱ ብሎ ታማኝነትን ማጉደል ተገቢ አይደለም፡፡ የሚልኪያስ 3ኛ ምዕራፍ በማንበብ ስሰአሥራት የተጻፈውን አስተውሉ:GWAmh 143.3

    ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔርን ቃል አክብራ አሥራትን ሁሉ ወደጎተራው ብትሰበስብ ብዙ ወንጌላዊያን በተገኙ ነበር:: ጎተራው መራገፉ ባይነገራቸው ኖሮ ብዙ ወጣቶች ለሥራው በተሰለፉ ነበር፡፡ በጎተራው ውስጥ ብዙ ሀብት መገኘት አለበት፡፡ አንዳንዶች አምነታቸውን ባያጎድሉና አንዳንድ ጊዜም አሥራት ለማይገባ ነገር ባያውሉ ኖሮ ብዙ የተትረፈረፈ ሀብት በተገኘ ነበር፡፡GWAmh 143.4

    የእግዚአብሔር ሀብት እንዲህ ባለ ባልተስተካከለ ሥራ ላይ መጥፋት የለበትም:: አሥራት የእግዚአብሔር ስለሆነ የሚያባክኑትም ካልተናዘዙ በቀር የሰማይን መዝገብ እንደበዘበዙ ተቆጥረው ይቀጣሉ፡፡ አሥራትን እግዚአብሔር ካቀደው ጥቅም ውጭ በማዋል የእግዚአብሔርን ሥራ ዕድገት ማዳከም ተገቢ አይደለም፡፡ ለሌሎቹ የሥራ መስመሮች ሌላ ዘዴ መፈለግ አለበት፡፡ የገንዘብ ድጋፍ አንደሚያስፈልጋቸው ባይካድም የአሥራት ገንዘብ ለወንጌላዊያን ብቻ አንጂ አይፈቀድም፡፡ አዲስ የሥራ ቦታ ሲከፈት ከአሁኑ ይልቅ በቂ ወንጌላዊያን ያስፈልጋሉ፡፡GWAmh 143.5

    ለዚህም ገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ለወንጌል አገልግሎት የሚሰለፉ ሰዎች በጣም ችላ የተባለ ታላቅ ኃላፊነት አለባቸው፡፡- አንዳንዶቹ መስበክ ደስ ቢሳቸውም ለቤተክርስቲያን የግል አገልግሎት አያበረክቱም፡፡ በተለይ በአሥራት አከፋፈል በኩል የቤተ ክርስቲያንን አባሎች ያለባቸውን ግዴታ ጠንቀቀው እንዲያውቁ ወንጌላዊው ማስተማር አለበት፡፡GWAmh 144.1

    ወንጌላዊያናቻችን የሥራቸውን ዋጋ ወዲያው ካላገኙ ምርር ብለው ያዝናሉ፡፡ ግን በእግዚአብሔር ጎተራ ውስጥ በቂ ሁበት መኖር አለመኖሩን መቆጣጠር ተግባራቸው መሆኑን አስበውበታል? ሰዎች የእግዚአብሔር የሆነውን አንዳይቀሙ የሚያስተምሩ ጠንጌላውያን ቁጥር ብዙ ካልሆነ በቀር የእግዚአብሔር ጎተራ ተራግፎ ሥራው መቋረጡ አይቀርም፡፡GWAmh 144.2

    የእግዚአብሔርን መንጋ የሚጠብቅ ጠባቂ ሥራውን በታማኝነት ማካሄድ አለበት፡፡ ያኛውን ነው አንጂ ይህኛውን የሥራ ዓይነት አልፈልግም በማለት ሥራ እያማረጠ ያልፈለገውን የሥራ ዓይነት ለሌላው ቢያሸክም ታማኝ ነው ማለት አይቻልም፡፡ አሥራትን ባለመክፈላቸው እግዚአብሔር ሰዎችን የከሰሰበትን ክስ በሚልክያስ ያንብብ፡፡ እግዚአብሔር በቀማኛነት ከወነጀላቸው በኋሳ «በመርገም ርጉማን ናችሁ” ይላቸዋል:: ታዲያ ሕዝብን የሚመራ አስተማሪ ቀማኞች ሲሆኑ አያየ ሳይመክርና ሳያስጠነቅቅ እንዴት ያልፋቸዋል? እያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያን አባል አሥራቱን በታማኝነት መክፈል መማር አለበት፡፡GWAmh 144.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents