Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የወንጌል ድጋፍ

    አምላክ የወንጌልን መዳረስ በአገልጋዮቹ ፈቃደኝነትና ጥረት ላይ አሳርፎታል፡፡ የምህረቱን ወንጌል የሚያደርሱ ሁሉ ሥራውን በገንዘባቸው አማካኝነት መደገፍ አንዳለባቸው አይዘንጉ፡፡ የወንጌል እውነት የደረሳቸው ሁሉም ከሐብታቸው ጥቂቱ ክፍል ለእግዚአብሔር ሥራ መዋል እንዳለበት ይገንዘቡ፡፡GWAmh 141.3

    ይህ ትምህርት በቃልም በአርአያነትም መፈጸም አለበት፡፡ የሥራውን ጠቃሚነት ራሱ በሥራው የሚያስተባብል ወንጌላዊ አይሳካለትም፡፡GWAmh 141.4

    አንደ መጽሐፍ ትዕዛዝ የእግዚአብሔር እንዲሆን መድበን ያስቀመጥነው የእኛ የወንጌል ድርሻ ነው፡፡ ይህን ገንዘብ ወስዶ ለግል አገልግሎት ማዋል ከስርቆት ይቆጠራል፡፡ አንዳንዶች ለእግዚአብሔር ተለይቶ ከተቀመጠው ቅዱስ ገንዘብ በመቆንጠር ተሳስተዋል፡፡ ይህን ነገር ሁሉም በግልጽ ማስተዋል አለበት፡፡ ማንም ይህን የእግዚአብሔርን ገንዘብ የማስቀመጥ ኃላፊነት ቢሰጠው በሌላ ጊዜ እተካለሁ በሚል አስተሳሰብ ሕሊናውን ደልሎ ከገንዘቡ ለራሱ ጥቅም ማዋል የለበትም፡፡ የእግዚአብሔርን ገንዘብ ለግል አገልግሎት ከማዋል ይልቅ ፍላጎትን ተቆጣጥሮ ለዕለት የሚያስፈልገውን ወጭ መቀነስ በጣም የተሻለ ነዉ፡፡GWAmh 141.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents