Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከስብከቱ ቀነስ፣ ከማስተማሩ ገፋ

    በስብሰባችን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚሰጠውን ስብከትና ትምህርት በሙሉ እንዲያጠቃልሉ የሁለት ሶስት ሰዎች ዕዳ መሆን : አንዳንድ ጊዜ ጠቅላላውን ጉባዔ በክፍል በክፍል መድቦ ማስተማር ይቀላል፡፡ በዚህ መንገድ መምህሩ ክሰዎቹ ጋር የበለጠ መቀራረብ ይኖረዋል፡፡GWAmh 270.1

    በስብሰባችን ከሚገባው በላይ ስብከት ይደረጋል፡፡ ይህ ዘዴ ወንጌላዊያንን ያደክምና ሊሰማ የሚገባው ብዙ ባ:ራሬ ነገር በቸልታ ይታለፋል፡፡ ወደ ክፋት የሚመሩ ጥቃቅን ነገሮች ልብ ሳይባሉ ያልፋሉ፡፡ ወንጌላዊው ብርታቱ ይጎዳል፤ የራሱን ሕይወት ከክርስቶስ ፍቅር ጋር ሰማያያዝ ሊያሳልፈው የሚገባው የግል ጊዜውም ይወዐወሰድበታል፡፡ ከስብሰባ ሳይ ስብሰባ ሲደጋገም ሐዝቡም የሰሙትን የሚያሰላስሱሉበት ጊዜ ያጣሉ፡፡ ሀሳባቸው ይደበላለቅባቸውና ስብሰባው ያሰለቻቸዋል፡፡ ከስብከቱ ቀነስ ከትምህርቱ ገፋ ማድረግ ይሻላል፡፡ በስብከት ጊዜ ከሚሰሙት የበለጠ ግልጽ ብርሃን መቀበል የሚያስፈልጋቸው አሉ፡፡ የቀረበውን ዕውነት ለመረዳት አንዳንዶቹ ከሌሉቹ የበለጠ ጊዜ ይፈልጋሉ፡፡GWAmh 270.2

    በበለጠ ተብራርቶ ቢነገራቸው በግልጽ ተመልክተው ይጸነብበታል፡፡ በማያጠራጥር ቦታ ላይ አንደተመታ ምስማር ይሆንላቸዋል፡፡ ስብሰባትን በመነቃቃትም ሆነ በክንውንነት መሳጓሻል አንዳሰበት ተነግሮኛል፡፡ ወደ መጨረሻው አንደተቃረብን መጠን ክስብክቱ ይልቅ የመጽሐና ቅዱስ ጥናት መብዛት አንዳለበት ተገልጦልኛል፡፡ ቡድን ቡድን ሆነው በየመሪያቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አያጠወጠጡ በማንበብ ይነሃጋገሩ፡፡GWAmh 270.3

    ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱን ያስተማራቸው በዚህ መንገድ ነበር፡፡ ብቡ ሕዝብ ዙሪያውን ሲከበጡ ጉባዔውንና ደቀመዛሙርቱ ያስተምራል፡፡ ንግግሩ ካበቃ በኋላ ደቀመዛሙርቱ ሕዝቡን በቡድን በቡድን አድርገው ክርስቶስ ያስተማረውን ይደጋግመላቸዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ሕዝቡ የክርስቶስን አባባል ስለ ማያስተውሉት ወይም በአጉል መንገድ ስለሚተረጉመሙት ደቀመዛሙርቱ የክርስቶስን ትምህርት በጥቅስ እየደገፉ ይብራሩላቸዋል፡፡GWAmh 270.4

    በፍጥረት ሁሉ ያለውን ድምጽ ይሰሙ ዘንድ ታላቁ መምህር ሰሚዎቹን በተፈጥሮ አማካይነት ያስተምር አእምሮአቸው ለማስተዋል፤ ዓይናቸው ለማየት ሲከፈት ያዩትን ተፈጥሮአዊ መግልጫ መንፈሳዊ ትርጉም አንዲሰጡት ይረዳቸው. ነበር፡፡ ያስተምርባቸው የነበሩት ምሣሌዎች በተፈጥሮ አማካይነት መንፈሳዌ ትምህርት ማስተማር መውደዱንና ከፅለት አጋጣሚዎች ጠቃሜ ትምህርት ማስተማር መቻሉን ያመለክታሉ፡፡ የሰማይ አዕዋፍ፣፤ የምደረበዳ አበቦች፤ ዝርና ዘሪው፣ ጠባቂውና በጎቹ፡ ክርስቶስ ከነዚህና እነዚህን ከመሳስሉት የተፈጥሮ ሀብት የማይጠፋ ዕውነት አስተምራል፡፡ አዳማጮቹ ከሚያውቋቸው የፅለት ተግባሮችና አጋጣሚዎችም ብዙ ጠቃሚ ትምህርት አስተምራል፡፡ ለምሣሌ : አርሾ፣ የተደበቀው መዝገብ፣፤ እንቁ፣ የአሳ አጥማጅ መረብ፣ የጠፋው ድሪም፤ የጠፋው በሕንዛና በአሰዋ ላይ የተሰራው ቤት፡፡ ትምህርቱ በሙሉ የሰሚዎችን ልብ የሚነካ፣ አስተሳሰባቸውን የሚያነቃቃ ነበር፡፡GWAmh 271.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents