Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሩቅ ቦታዎች

    የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የተቋቋመችው ወንጌልን ለማዳረስ ነበር፡፡ የሚሲዮናዊነት ሥራ ቤተ ክርስቲያንን በማያወላውል ጽኑ መሠረት ላይ ያንጻታል።፡ መሠረቱም «ጌታ ለርሱ የሆኑትን ያውቃል» (2ጢሞ. 2፡19) የሚል ማህተም አለበት፡፡ በዚህ ሠራተኞቹ ራሳቸውን ለመካድ፤ ወደ ሩቅ ቦታዎች ዕውነቱን በመስዋዕትነት ለማዳረስ ይነሳሳሉ፡፡ በማያምኑ ላይ ታላቅ ምሣሌነት አለው፡፡ ሠራተኞቹ በመለኮታዊ መሪነት ሲሠሩ ዓለማዊያን እግዚአብሔር ለሚያምነበት የሠጠውን የማያልቅ በረከት ያያሉ፡፡ በዓለም ፊት የእግዚአብሔርን መንግሥት ዓላማ እንገልጥ ዘንድ ከባድ ኃላፊነት ተጥሎብናል፡፡ የክርስቶስን መስቀል ዋናነት ለዓለም ለማሳወቅ ቤተ ክርስቲያን በተደራጀ መንገድ በኀብረት መሥራት አለባት፡፡GWAmh 310.4

    የእርሱ መልዕክትኞች ለመሆን ያላቸውን ሁሉ የሚተው ሰዎችን እግዚአብሔር ይጠራል። ጥሪውም መልስ ያገኛል፡፡ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ከተገለጠ አንስቶ ሰዎች የክርስቶስን ወንጌል በየቦታው ለማዳረስ ያልተነሳሱበት ክፍለ-ዘመን የለም፡፡ በክርስቶስ ና:ቅር በመነሳሳት፣ የጠራን ስዎች በመሻት ብዙ ሰዎች ቤት ንብረታቸውን፤ ወዳጀ ዘመዳቸውን (ልጆችና ሚስቶቻቸውን ሳይቀር) ትተው ወደ ጣኦት አምላኪዎችና የሥልጣኔን ጭላንጭል ወዳላዩ ጎሳዎችና ነገዶች በመሄድ ወንጌልን አስተምረዋል፡፡ አንዳንዶች በሥራው ላይ አንዳሉ ሕይወታቸው አልፏል፤ ሌሎችም ሥራውን ለማካሄድ ከሞት የዳኑ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ ቀስ በቀስ ሥራው አደገ፤ በዕንባ የተዘራው ዘርም ብዙ ምርት ብዙዎች ስለ እግዚአብሔር ከማወቃቸውም በላይ የመስቀሉ አርማ በአረማዊያን አገሮች ተተአክለ፡፡GWAmh 311.1

    በእግዚአብሔር ፊት የዕውነትን ቨር ለመዝራት ወደ ሩቅ ቦታ ለቀራጥነት ከሚቕሄዱትና ምርት ለማፈስ ተስፋ ከሚያደርጉት ወንጌላዊያን የበለጠ የተከበረ ሰው የለም፡፡ የጠፉትን ሲሱ አገልጋዮቹ የሚደርስባቸውን ስቃይ የሚያውቀው ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ መንፈሱን ስለሚያድላቸው ነፍሳት በነርሱ አማካይነት ከኃጢዓት ወደ ጽድቅ ይመለሳሉ፡፡GWAmh 311.2

    አንድ ኃጢዓተኛን ለመመለስ ወንጌላዊ ኃይሉን በሙሉ ያዳክማል፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው፣፤፣ ክርስቶስ ያዳነው ነፍስ ክቡር ነው፡፡ ወደፊት ብዙ ተስፋ አለው፤ መንፈሳዊ መብት ተሰጥቶታል፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ከጥቅም ላይ ቢያውለው ችሎታው ይዳብርለታል፡፡ በወንጌል ተስፋ አማካይነት አለመሞትን ይቀዳጃል፡፡ ክርስቶስ ዘጠና ዘጠኙን በጎች ትቶ አንዲን የጠፋችውን ሊፈልግ ክሄደ እኛ እንደርሱ የማናደርግበት ምን ምክንያት አለን? አንደሠራው አለመሥራት፣ እንደሰጠው አለመስጠት እውነትን ከመሸጥ አይቆጠርም?GWAmh 311.3

    የውጭ አገሮች ብዙ ነገር አንደሚያስፈልጋቸው ተገልጦልኛል፡፡ ከጥቂት ጊዜ በፊት ተዘግተው የነበሩትን በሮች ሁሉ መልዓክት በየአገሩ እየከፈቷቸው ነው፡፡ ከሕንድ አገር፤ ከአፍሪካ፣ ከቻይና ክሌሎችም ቦታዎች «አለፉና እርዱን» የሚል ጩኸት ይስማል፡፡GWAmh 312.1

    ወደ ውጭ ሄዶ ለመሥራት ፈቃደኛ መሆን ያገር ውስጥን ሥራ ያፋጥነዋል፡፡ በሩቅ አገር በተደረገው የወንጌል ሥራ መጠን ያገርን ውስጥ ሥራ እግዚአብሔር ያሳድገዋል፡፡ ያለንን ለሌሎች ለመስጠት ፈቃደኞች ስንሆን ከእግዚአብሔር ዘንድ የማያልቅ በረከት እንቀበሳለን፡፡ እግዚአብሔር የሚሲዮናዌያንን ሥራ የሚመዝነው በውጭ ባከናወነት ሞያ መሠረት ነው፡፡ በጨለማ ውስጥ ነፍሳትን ለማዳን ለሚታገሉት አንዳንዱ ቤተሰብ፣ ቤተ ክርስቲያንና የሥራው አማካይ ከፍተኛ እርዳታ ቢያደርግ ያምላክ ፈቃድ ነው፡፡GWAmh 312.2

    በአንድ ቦታ ሥራው ለመርዳት የተሰጠው እርዳታ በሌላ ቦታ ያሉትን የሥራ አቋሞች ያበረታታል፡፡ ወንጌላዊያን ገንዘብ ነክ ችግር ካላሳሰባቸው ጥረታቸው ይቀጥላል። ዕውነቱ ለሰዎች እየተገለጠ ክርስቲያኖቹ እየዳበሩ ሲሄዱ ራሳቸውን ከመቻል አልፈው ሌሎችን መርዳት ይጀምራሉ፡፡GWAmh 312.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents