Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የመጥምቁ ዮሐንስ ታሪክ

    ዮሐንስ መጥምቁ በበረሃ ሲኖር ስለእግዚአብሔር በሚገባ አወቀ:: ስለእግዚአብሔር በተፈጥሮ አማካይነት ተማረ፡፡ በመሰኮት ዕርዳታ የነቢያትን መጽሐፍ አጠፍ ቀንም ሆነ ሌሊት የሚያስብ ስሰክርስቶስ ነበር፡፡ በራዕይ የነገሥታትን ንጉሥ በሙሉ ግርማው ተመለከተው፡፡ የቅዱሱን ግርማ ሲመለከት የራሱን ብቁ አለመሆን ተገነዘበ፡፡ ማቴዎስ 5፡8፤ ፅብራዊያን 11:5:GWAmh 32.5

    የእግዚአብሔርን መልዕክት ያውጅ ነበር፡፡ በእግዚአብሔር ኃይልና ጽድቅ ይራመድ ነበር:: የሰማይ መልዕክትኛ ሆኖ ለመላክ ፈቃደኛ ነበር፡፡ በምድራዊ ነገሥታት ፊት መቆም አያስፈራውም፡፡ ምክኒያቱም በነገሥታት ንጉሥ ፊት በየጊዜው ስለሚቆም ነበር፡፡GWAmh 33.1

    ዮሐንስ በማያወላውል አነጋገር መልዕክቱን ጀመረ፡፡ በምድረ በዳ ቁልጭ ያለውና በተግሣጽና በተስፋ የተሞላው ድምጹ «ንስሐ ግቡ የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችፍ›” ሕዝቡን በአዲስና ባልተለመደ ምልዕክት አናወጠው፡፡ አገር በሙሉ ሕሊናው ታወከ፡፡ ብዙ ሕዝብ ወደ ምድረ በዳው ተጓዘ፡፡GWAmh 33.2

    ተራ ገበሬዎችና አሳ አጥማጆች፣ የሮማዊያን ወታደሮች ከሄሮድስ ግቢ፣ ቀራሙች፣ ፈሪሣዊያንና ሰዱቃዊያን ሳይቀሩ ወደ ስብሰባው ቦታ ሄዱ፡፡ ሁሉም በፀጥታ ያዳምጥ ማሾፍ ፤መቀለድ ቀርቶ ሁሉም ኃጢዓቱ ተሰማው፡፡ ኩሩው ሄሮድስ አንኳን ከቤተመንግሥቱ እንዳለ መልዕክቱ ደርሶት በፍርሃት ተንቀጠቀጠ፡፡GWAmh 33.3

    በአሁኑ ዘመንም የሱስ በሰማይ ደመና ከመገለጡ በፊት ዮሐንስ የሠራው ዓይነት ሥራ መፈጸም አለበት፡፡ በታላቁ የጌታ ቀን ጸንተው የሚቆሙ ሰዎች ለማዘጋጀት መልዕክትኞቹን እግዚአብሔር ይመርጣል፡፡ «ከክርስቶስ የመጀመሪያ ምፃት በፊት የነበረው መልዕክት፣ቀራሙችና ኃጢዓተኞች ንስሀ ግቡ፣ ፈሪሣዊያንና ሠዱቃዊያን ተመለሱ፤ ንስሀ ግቡ፤ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና» የሜል ነበር፡፡ በክርስቶስ ዳግም ምፃት የምናምን ስለሆንን .«ጌታን ለመገናኘት ተዘጋጁ::»- የሚለውን መልዕክት ማዳረስ - አለብን:: መልዕክታችን አንደ ዮሐንስ መልዕክት ቀጥተኛ መሆን አለበት፡፡ ነገሥታትን ሳይቀር ስለኃጢዓታቸው ገሠጻቸው፡፡ ለሕይዎቱ ሳይሳሳ ለአምላኩ መሰከረ፡፡ ማቴዎስ 3፡2፤ አሞጽ 4:12:GWAmh 33.4

    የእኛም ሥራ እንደዚሁ በታማኝነት መከናወን አለበት:: እንደ ዮሐንስ ለመመስክር እርሱ ያገኘውን መንፈሣዊ ሕይዎት ማግኘት አለብን፡፡ ያው ዓይነት ሥራ በእኛ ውስጥ መፈጸም አለበት፡፡ እግዚአብሔርን አየተመለከትን በራሳችን ላይ ያለንን ትምክህት መተው አለብን፡፡ ዮሐንስ ሰው በመሆኑ ደካምነትና ስህተት አይታጣበትም፡፡ ግን የመለኮት ኃይል ለወጠው፡፡GWAmh 33.5

    ክርስቶስ ሥራውን ከጀመረ በኋላ የዮሐንስ ደተመዛሙርት ወደ እርሱ ወጥተው ሰዎች ሁሉ የሱስን ይከተላሉ ብለው አጉረመረሙ:: ዮሐንስ ግን መደሰቱንና ስለክርስቶስ ያለውን ፍቅር ገለጠላቸው፡፡GWAmh 34.1

    «ዮሐንስ መለሰ እንዲህም አለ፡፡- ከሰማይ ካልተሰጠው ሰው አንዳች ሊቀበል አይችልም፡፡ እናንተ:- እኔ ክርስቶስ አይደለሁም ነገር ግን ከእርሱ በፊት ተልኬአለሁ አንዳልሁ ራሳችሁ ትመሰክሩልኛላችሁ፡፡ ሙሽራይቱ ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው፡፡ ቁሞ የሚሰማው ሚዜው ግን ድምፅ አጅግ ደስ ይለዋል፡፡ እንግዲህ ይህ ደስታ ተፈጸመ፡፡ እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል፡፡ ከላይ የሚመጣው ክሁሉ በላይ ነው፡፡ ከምድር የሚሆነው ከምድር ነው፡፡ የምድሩንም ይነግረናል፡፡»GWAmh 34.2

    ዮሐንስ ወደ አምላክ በመመልክት ራሱን ዝቅ አደረገ፡፡ ስዎችን ወደእርሱ ለመሳብ አልፈለገም፡፡ ግን ሀሳባቸውን ወደ እግዚአብሔር በግ መራው:: ራሱ ድምፅ፣ የምድረ በዳ ድምፅ መሆኑን ገለጠላቸው፡፡ ሰዎች ሁሉ የሕይወትን ብርሃን ይመለክቱ ዘንድ እርሱ ዝም አለ::GWAmh 34.3

    ዕውነተኛ የእግዚአብሔር መልዕክትኛች ለራሳቸው ክብር አይሹም፡፡ ለራሳቸው ያላቸው ፍቅር በክርስቶስ ፍቅር ይዋጣል፡፡ ዮሐንስ አንደመሰከረው «አነሆ የእግዚአብሔር በግ የዓለምን ኃጢዓት የሚያስወግድ፡፡› አያሉ ይመሰክራሉ፡፡ ዮሐንስ 3፡27-31፣ዮሐንስ 1:29::GWAmh 34.4

    የነቢዩ ሕይዎት በመለኮታዊ ፀጋ፣ ተሞልቶ ነበር:: ስለመሲሁ ክብር እንዲህ ሲል መሰከረ:: «ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፣፤ ከምድር የሚሆነው ከምድር ነው፡፡ የምድሩንም ይናገራል፡፡ ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፡፡ እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ይናገራልና እግዚአብሔር መንፈሱን ሰብሮ አይሰጥምፍ”GWAmh 34.5

    የክርስቶስን ክብር ተከታዮቹ ሁሉ ይካፈላለ፡፡ መድህኑም እንዲህ ይላል፡፡ «እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፡፡ አንደሰማሁ አፈርዳለሁ፡፡ ፍርዴም ነው፡፡ የላከኝን ፈቃድ አንጅ ፈቃዴን አልሻምፍ ራሳችን ችላ ባልን መጠን የእግዚአብሔርን መንፈስ አንቀበላለን፡፡ ሐሳባችን ለክርስቶስ አንዳስገዛን መጠን የእግዚአብሔር ተከታዮች ልንሆን እንችላለን፡፡ ይህን ለሚያደርጉ ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ሳይሰፈር ይሰጣቸዋል፡፡› በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና ለአለቅነትና ለሥልጣንም ሁሉ ራስ በሆነ በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችሁአል፡”GWAmh 34.6

    የዮሐንስ ኑሮ የስንፍና፣የጨለማና ራስን ዘግቶ የመኖር ኑሮ አልነበረም፡፡ በየጊዜው ከሰዎች ጋር ይገናኝ ነበር፡፡ በዓለም የሚደረገውን ድርጊት ሁሉ አተኩሮ ይመለከት ነበር፡፡ ብቻውን ሆኖ እያንዳንዱን ሁኔታ በጽሞና ተመለከተ፡፡ ከሰማይ በተገለጠለት ራዕይ የሰዎችን ጠባይ አጥንቶ በምን ዓይነት ዘዴ አንደሚያስተምራቸው አወቀ፡፡ የሥራው ኃላፊነት ተሰማው፡፡ ለሥራው ይበረታ ዘንድ በፀሎት ወገቡን ታጠቀ፡፡ ዮሐንስ 3:31:34፤ ዮሐንስ 5:፡3ዐ፣ ቆላሳይስ 2:10:GWAmh 35.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents