Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የሄኖክ የሕይዎት ታሪክ

    ሄኖክ ስድሣ አምሥት ሲሞላው ልጅ ወሰደ ተብሎ ተጽፏል። ከዚያም በኋላ ለሶስት መቶ ዘመናት ከእግዚአብሔር ጋር ተራመደ በእነዚያ ዓመታት ሁሉ ሄኖክ እግዚአብሔርን ፈርቶ ትዕዛዙን አክብሯል፡፡ እንዲያውም የበኩር ልጁን ከወለደ በኋላ ከእግዚአብሔር ግንኙነቱ በበለጠ ጠነከረ፡-፡ ልጁ በእርሱ ላይ ያለውን ሙሉ ዕምነት በተመለክተ ለልጁ ያለውን ፍቅር በተገነዘበ ጊዜ የእግዚአብሔር ልጆች ከአምላካቸው ጋር ያላቸውን የልብ ግንኙነት በበለጠ አስተዋለ፡፡ በቀንና በሌሊት እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል ለሰዎች ያደለውን ፍቅር ያሰላስል አብረውት ለሚኖሩት ሰዎች ይህን የተሰማውን ታላቅ ፍቅር ከልቡ ሊያስረዳ ሞከረ፡፡GWAmh 31.1

    ሄኖክ ከእግዚአብሔር ጋር የተራመደ በሕልም ወይም በራዕይ ሳይሆን በዕለት ተግባሩ ነበር፡፡ ከሰዎች ተለይቶ ባሕታዊ አልሆነም፡፡ ምክኒያቱም በሰዎች መካከል ለእግዚአብሔር የሚያከናውነው ብዘ ሥራ ነበረው፡፡ በቤተሰቡ ውስጥ በአባትነትና በባልነት ኃላፊነቱ፤ በአካባቢውም በጉርብትና ኃላፊነቱ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሆኖ ቀጥ ብሎ ሠራ: በቀን ሥራውም ላይ ሳለ ሄኖክ ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ግንኙነት አቋርጦበት አያውቅም አንዲያው ሥራ ሲበዛበት በበለጠ ጸሎት ያዘወትር ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከሰዎች ገለል ይል ነበር:: በማስተማርና በምከር ሰዎችን ሲመክር በኋላ በብቸኛነት ሆኖ ከአምላኩ መለኮታዊ ዕውቀት ይሻ ነበር፡፡GWAmh 31.2

    እንዲህ ያለ ግንኙነት ከአምላኩ ጋር ስለነበረው ሄኖክ የመለከትን በበለጠ ያንጸባርቅ ጀመር፡፡ ፊቱ በብሩህ ብርሃን አንዲያውም ከየሱስ የመጣለት ብርሃን መሆኑ ያስታውቅ ነበር ስለአምልኮ ግድ የሌላቸው አንኳን ይህን ብርሃን ማየት አልተሳናቸውም፡፡GWAmh 31.3

    ዘመናት እንዳለፉ መጠን ፍቅሩ አየሞቀ፣ ዕምነቱ አየጠነከረ ሄደ፡፡ ፀሎትን የሚመለከተው የነፍስ አስትንፋስ አድርጐ ነበር:: ሰማያዊ አካባቢ ይሰማው ነበር፡፡GWAmh 31.4

    የወደፊቱ ስለ ተገሰጠለት ሄኖክ የጽድቅ አስተማሪ ሆነ:: ማስጠንቀቂያውን ሰው ሳያማርጥ ለሚሰሙት ሁሉ ያዳርስ ነበር፡፡ ቃየል ከአምላክ ፊት በኮበለለበት በዚያው ቦታ ላይ ሄኖክ ነቢዩ በራዕይ የታየውን መልዕክት እንዲህ እያለ መሰከረ፡፡GWAmh 31.5

    «ከአዳም ደምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ:- አነሆ ጌታ በሁሉ ላይ ሊፈርድ በኃጢዓተኛነትም ስላደረገ ስለኃጢዓታቸው ሁሉ ዐመጸኞችም በእርሱ ላይ ስለተናገሩት ስለጭከና ነገር ሁሉ ኃጢዓተኞችን ይወቅስ ዘንድ ከቅዱሳኑ ጋር ይመጣል ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ፡፡»GWAmh 32.1

    በሰሙት ሁሉ ዘንድ በአገልጋዩ አማካይነት የተላከው የእግዚአብሔር ኃይል ተሰማቸው፡፡ አንዳንዶቹ መልዕክቱን አዳምጠው ከኃጢዓታቸው ሲመለሱ አብዛኛዎቹ ግን በመልዕክቱ ይቀልዱ ነበር፡፡ የአምላክ አገልጋዮች በመጨረሻ ዘመን ይህንኑ መልዕክት ማዳረስ አለባቸወ፡፡ ግን አብዛኛው ሕዝብ በቀልድና በፌዝ ማሾፉ የታወቀ ነው፡፡ ዘመናት አንዳለፉ መጠን የኃጢዓት ብዛት እየጨመረ፣ ስለመለከት ያለው የሕዝብ ዕውቀት አየጨለመ ይሄዳል፡፡GWAmh 32.2

    ቢሆንም ሄኖክ ምክሩን፣ ማስጠንዋቂያውንና ተማጽኖን መስጠቱን አላቋረጠም፡፡ የዚያ ትውልድ ሰዎች ለዓለም ሀብት ብርና ወርቅ የማይጥር ሰነፍና ቁል አድርገው ቀቆጠሩት፡፡ እርሱ ግን ለእነርሱ ለማይታያቸው መዝገብ ይጣጣር ነበር፡፡ ንጉሱን በጽዮን ከተማ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ይመለከት ኃጢዓት እንደበዛ መጠን ወደ እግዚአብሔር ቤት የነበረው ናፍቆት እየጠነከረ ሄደ:: በመሬት ላይ አያለ በሃይማኖት በሰማይ ይኖር ነበር፡፡ «ልባቸው የነዛ የተመሰገኑ ናቸው እግዚአብሔርን ያዩታልፍ” ሄኖክ ከሰማይ ጋር ለመግባባት ለሶስት መቶ ዓመታት የልብ ንጽህና ሲሻ ኖረ፡፡ ለሶስት መቶ ዓመታት ከእግዚአብሔር ጋር ተራመምመደ፡፡ ቀን በቀን ግንኙነታቸው እየጠነከረ ሲሄድ እግዚአብሔር በመጨረሻ ወሰደው:: በመጨረሳ ወደሰማይ በር ገባና የመጀመሪያው ሰው ሆኖ በቅዱስ ከተማ ተገኘ፡፡ «ሄኖክ ሞትን አንዳያይ በዕምነት ተወሰደ፡፡ እግዚአብሔርም ስለወሰደው አልተገኘም፡፡ ሳይወስደው እግዚአብሔርን ደስ አንዳሰኘ ተመስክሮሰታልፍ”GWAmh 32.3

    እግዚአብሔር የሚጠራን ለእንደዚህ ያለ ግንኙነት ነው:: በሁለተኛ የጌታ መምጣት ሲድኑ የሚፈልጉ ስዎች ሄኖክ አንደኖረው ያለ ሕይወት መኖር አለባቸው፡፡GWAmh 32.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents