Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የሰማሪያዊቷ ሴት

    የሱስ ብዙ ሰዎች አልተሰበሰቡም ብሎ ለማስተማር አልቦዘነም ነበር፡፡ ከታላላቅ ንግግሮቹ መካከል ለግለሰብ የተነገሩት ብዙዎች: እስቲ ለሰማሪያዊቷ ሴት የተናገረውን ግሩም ቃል አዳምጡ፡፡ እንድትረዳው ስለጠየቃት ተገረመች:: «የምጠጣው ስጭኝ አባክሽ» አላት፡፡ ቀዝቃዛ ውኃ እንድትሰጠው በመጠየቅ ለእርሷ የሕይወት ውኃ የሚሰጥበትን መንገድ አዘጋጀላት፡፡GWAmh 121.1

    ሴትዮዋም «አንተ አይሁድ ነህ፤ እኔ ግን ሳምራዊት ነኝ ታዲያ ውኃ እንድሰጥህ የምትጠይቀኝ ምን ግንኙነት ኖሮን ነው?” : ክርስቶስም «የእግዚአብሔርን ሥጦታ ብታውቂና ውኃ ስጭኝ የሚልሽ ማን መሆኑን ብታውቂ ኖሮ ራስህ ስጠኝ ባልሽ ነበር፡፡ እኔ ከምሠጠው ውኃ የሚጠጣ ሰው ለዘለዓለም አይጠማም፣ በሆዱ ውስጥ የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆንለታል፡፡>>GWAmh 121.2

    በዚህች አንዲት ሴት ክርስቶስ መደሰቱን ገለጠ፡፡ አነጋገሩ በእውነት የታሰበበትና ግልፅ ነበር:: ሴትዮዋ በንግግሩ ከመነካቷ የተነሳ የመጣችበትን ውኃ ትታ ወደ ከተማ ሄደችና «ኑና ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ይህ ክርስቶስ አይደለም አንዴ?» አለች ብዙዎቹ ሥራቸውን ትተው በያዕቆብ ጉድጓድ ያለውን እንግዳ ለማየት ሄዱ፡ ብዙ ጥያቄዎችን አቀረቡለት፤ የሚሰጣቸውንም መግለጫ በጉጉት (በናፍቆት) ያዳምጡ የብርሃንን ጨረር ተከትሎ የሚያንጸባርቅ ብርሃን ለማግኘት የሚጠባበቅ ሰው ይመስሉ ነበር፡፡GWAmh 121.3

    የሱስ ጠምቶትና ርቦት ያስተማረው ትምህርት ብዙዎችን ባረከ፡፡ ሊረዳት የተሰለፈላት አንዲት ሴት መልዕክቱን አዳረሰች:: የእግዚአብሔር ሥ'ራ ምንጊዜም በዓለም ዙሪያ ሊስፋፋ የሚችል በዚህ መንገድ ነው፡፡ የአንተ መብራት ሲበራ የሌሎች መብራት ከአንተው ይቀጣጠላል፡፡GWAmh 121.4

    የእግዚአብሔር ሠራተኞች በተፈለገ ጊዜ የሚደርሱ ዝግጁዎች መሆን አለባቸው፡፡ ወንድሞቼ ሆይ፣ እግዚአብሔር በየጊዜው የአገልግሉት በር ይከፍትላችኋል፡፡ የቻላችሁትን ያህል ለመሥራት ተዘጋጁ፡፡ ያ ለተራቡ ነፍሳት ለማስተማር የተሰጠ እድላችሁ እንደገና አያጋጥማችሁም ይሆናል:: ጊዜአችሁን አባክናችሁ አትጸጸቱ::- ዮሐንስ 4:7-30 ተመልከት)GWAmh 121.5

    የማይመረመረውን የክርስቶስ ጸጋ ለሌሎች ለማስተዋወቅ ችላ አለማለት ነው፡፡ አንድ ጊዜ ያመለጠ ምቹ ጊዜ ቢፈልጉም አይገኝም፡፡GWAmh 122.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents