Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    «ጠቦቶቼን መግብ ”

    ክርስቶስ ከማረጉ በፊት ለጴጥሮስ የሰጠው ትዕዛዝ «ጠቦቶቹን መግብ” የሚል ነበር፡፡ ይህ ትፅዛዝ ለእያንዳንዱ ወንጌላዊ ተሰጥቷል፡፡ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱን «ተው ሕፃናትን ወደ እኔ ይምጡ አትክልክሏቸው» ሲል በማንኛውም ክፍለ ዘመን ለሚገኙት ደቀመዛሙርቱ መናገሩ ነበር:GWAmh 129.4

    የወጣቶችን መንፈሣዊ ፍላጎት ችላ በማለት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ ነገር ተበላሽቷል፡፡ ወንጌላዊያን በጉባዔአቸው ውስጥ ያሉትን ወንጌላዊያንን በደስታ ይተዋወቁአቸው፡፡GWAmh 130.1

    ብዙዎች ይህን ነገር ችላ ቢሉ በእግዚአብሔር ፊት አንደ ኃጢዓት ይቆጠርባቸዋል፡፡ ከወጣቶች መካከል እውነቱን እያወቁ ልባቸው በእግዚአብሔር መንፈስ ያልተነካ ብቡዎች ናቸው፡፡ ታዲያ እኛ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ነን የምንል ይህን ነገር ከቀን ወደ ቀን፤ ከሳምንት ወደ ሳምንት እንዴት በቸልተኝነት አናልፈዋለን? ማስጠንቀቂያ ሳይደርሳቸው በኃጢዓታቸው ቢሞቱ ደሙ ከቸልተኛው ጠባቂ አጅ ይፈለጋል፡፡GWAmh 130.2

    በአካባቢያችን ያሉትን ወጣቶች ማስተማር ለምን አንደ ከፍተኛ ሚሲዮናዊነት አይቀጠርም? ይህ ሥራ ሰማያዊ ጥበብ የሚያስፈልገው፣ በጣም ጥንቁቅ ዘዴ የሚያሻጡ፤ አጅግ በጣም ከፍተኛ ትጋት የሚጠይቅ አና በጸሎት ኃይል ሊከናወን የሚገባው ተግባር ነው:: ወጣቶችን ሰይጣን አዘውትሮ ዓይኑን ይጥልባቸዋል፡፡ ግን ትህትና፣ ደግነት፣ ርህራሄና በክርስቶስ ፍቅር የተሞላ ልብ ከዚህ አስጊ ወጥመድ ሊያወጣቸው ይችላል፡፡GWAmh 130.3

    ሰወጣቶች አጋጣሚያዊ ምክርና የአንዳንደ ጊዜ ማደፋፈሪያ ብቻ አይበቃቸውም፡፡ ብርቱ፣ በጸሎት የተደገፈ፣ በጥንቃቄ የታቀደ ጥረት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ወላዋይና አፈግፋጊ የሆኑትን ወጣቶች ሊያስተምር የሚችል የክርስቶስ ፍቅር በሕይወቱ የሚታይበት ሰው ብቻ ነው፡፡ ሁሉም የሚያስፈልጋቸው ዕርዳታ አንድ ዓይነት አይሆንም፡፡ እግዚአብሔር ሰዎችን የሚቀርባቸው አንደፀባያቸው ስለሆነ እኛም የእርሱ አባሪዎች መሆን አለብን: ፊት ብቻ ተመልክተን የምንርቃቸው ሰዎች በደንብ ብንቀርባቸው የሥራን ዋጋ የሚከፍሉ ብርቱ ክርስቲያኖች ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ወጣቶችን እንዴት ማስተማር አንደሚቻል ብርቱ ትምህርት መስጠት አለበት፡፡ ስለዚሁ ተግባር ጸሎት መዘውተር ይገባዋል፡፡GWAmh 130.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents