Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የነፍሳት ሽክም

    የክርስቶስ አገልጋዮች ከክርስቶስ ጋር ጥብቅ ግንኙነት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በሕይወት ንጽህና፣ ራሳቸውን በመካድ፣ በትጋት፣ በአክብሮት ምሣሌነቱን መከተል ይገባቸዋል፡፡ የመጀመሪያ ዓላማቸው ነፍሳትን ወደ ክርስቶስ መመለስ መሆን : ክርስቶስ እንዳደረገው በማያቋርጥ ጥረት መሥራት አለባቸው፡፡GWAmh 19.1

    ጆን ዌልክ የተባለ መንፈሳዊ ለሰዎች ያለበት ኃላፊነት እየተሰማው ሌሊት እየተነሳ ይጸልይ ነበር፡፡ አንድ ቀን ባለቤቱ ጤናው አንዳይጐዳ ያን ልምዱን ይተው ዘንድ ለመነችው፡፡ «አህቴ ሆይ የሶስት ሽህ ነፍሳት ኃላፊነት አለብኝ፡፡ እነርሱ ግን ምን ያህል እንደሚሰማቸው አላውቅም” አላት::GWAmh 19.2

    ኒው ኢንግላንድ በምትባለው ከተማ ጉድጓድ ሲቆፈር ሥራው ሊጠናቀቅ ትንሽ ሲቀረው አንድ ሰው በጉድጓዱ ውስጥ ተደረበና ቀበረው፡፡ ድንገት ዑዑታ ተሰማና ሰው ሁሉ አየተሯሯጠ ደረሰ፡፡ ፈቃደኞች መሰላል፣ ገመድ፣ አካፋ፤ ይዘው ተሰለፉ፡፡ «አድኑት ኧረ አድኑት› የሜል ጩኽት በረከተ: ሰዎች ሁሉ በላቦት አስቲሰጥሙ ድረስ ሠሩ፡፡ በመጨረሻ ሰውየው በሕይወቱ እንዳለ ለማወቅ በአንድ ቧንቧ አማካይነት አንዲያነጋግራቸው ቧንቧውን ላኩለት፡፡ «በሕይወቴ ቶሎ ቶሎ በሉ፣ አዚህ መሆን አቤት ሲያስፈራ! » የሚል መልስ አገኙ፡፡GWAmh 19.3

    ሰዎቹ ኃይላቸውን አደሱና ቶሎ ብለው አወጡት፡፡ ከወጣ በኋላ «ዳነ! ዳነ!” የሚል ድምዕ ተሰማ፡፡ አንድ ሰው ለማዳን የተደረገው ጥረት ከሚያስፈልገው በላይ ነበር ወይም በፍጹም አልነበረም፡፡ ግን የጊዜአዊ ሕይወት ጥፋት ከዘለዓለም የነፍስ ጥፋት ጋር ሲመዛዘን እንዴት ያንሳል? የአንድ የአንድ ሰው ጊዜአዊ ሞት በሰዎች ልብ ያን ያህል ጭንቀት ሲፈጥር የአንድ ነፍስ ዘለዓለማዊ ጥፋት ምን ያህል ያሳስብ! ያን ከጉድጓድ ውስጥ የገባውን ሰው ለማዳን የተደረገውን ጥረት ያህል በኃጢዓት ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ መውጫ ለጠፋበት ሰው የእግዚአብሔር አገልጋዮች ጥረት ማድረግ አይገባቸውም ወይ?GWAmh 19.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents