Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ጤናማ ለመሆን የምንፈጽመው ግዳጅ

    ወንጌላዊያን ተዳክመው፤ በሽተኛ ሆነው ካልጋ ላይ ያለጊዜአቸው ሲሞቱ፤ ልቤ በጣም ያዝናል፡፡ ይህ ዓይነት አደጋ ከሚደርስባቸው መካከል ኃላፊነት ያለባቸውና ከፍተኛ ሥራ የሚወጡት ይገኛሉ ሥራውን ክመተው መሠቃየትን እንዲያውም አየሰሩ መሞትን ይመርጣሉ፡፡GWAmh 151.3

    የሰማይ አባታችን ልጆቹን ሊያሰቃይ አይፈልግም፡፡ የሕመምና የበሽታ ወይም የሞት ፈጣሪ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር የሕይወት ምንጭ ነው፡፡ ሰዎች አንዲኖሩ ይፈልጋል፤ «አንዲኖሩም ሕጉን እንዲጠብቁ ይመክራቸዋል፡፡ የዘለዓለምን እውነት ከልባቸው የሚቀበሉ እምነታቸው በሥራ አንዲገለጥ ያደርጋሉ፡ ሌሎች ኑሮአቸውን በመመልከት አንዲደሰቱ ይፈልጋሉ፡፡ እውነተኛ የወንጌል ገበሬ ዘሩን ቋጥሮ በእየወንዙ አጠገብ ሲዘራ፣ ሲጸልይ አእምሮውና አካሉ በከባድ ሥራ ይጠመዳል። ከሥራው ከባድነት የተነሣ ሳይሆነው ይወድቃል፡፡ በየጊዜው ብርታት የሚሰጥ ምግብ ከእግዚአብሔር ቃል ማግኘት ይገባል፡፡ ይህ ለሰሚዎቹ ኃይልና ሕይዎት ይሰጣል፡፡ እግዚአብሔር ሥራህ ጣዕምና ለዛ እስከሚያጣ ድረስ እንድትደክም አይፈልግም፡፡GWAmh 151.4

    በትምህርትም ሆነ በስብከት የአእምሮ ሥራ የሚበዛባቸው ለውጥና ዕረፍት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ጥናት የሚያበዛ ሰው አእምሮውን ከመጠን በላይ ያሠራዋል፤ የሰውነት ማጠንከሪያ ልምምድ ስለማያደርግ አካሉ ይደክማል፤ አእምሮም ስለደከመ ጥረቱን ያቋርጣል፡፡ ስለዚህ ተማሪው ካሰበው ዓላማ ሳይደርስ ይቀራል፡፡GWAmh 152.1

    አካልንና አእምሮአቸውን አኩል ቢያሠሩት ኖሮ ወንጌላዊያን ለሕመም ባልተሰጡም ነበር፡፡ ሠራተኞቻችን በሙሉ የጉልበት ሥራ ቢሠሩ ጤናማ በሆኑ የተጠሩበትን ግዳጅ በሚገባ ባከናወኑ ነበር፡፡ ለሙሉ መዝናናት ጊዜ ቢያጥራቸውም አጆቻቸውን አፍታትተው ጸልየው ቢመለሱ በአካልም በመንፈስም ታደሱ ማለት ነው፡፡GWAmh 152.2

    አንዳንድ ወንጌላዊያን ለኃላፊዎቻቸው ለማሳወቅ በእየቀኑ የተወሰነ ሥራ ለማከናወን ይፈልጋሉ፡፡ መንፈስ ስለሚነሳሱ ጥረታቸው ደካማና ዋጋ ቢስ ይሆናል፡፡ ከሥራ ነፃ የሆነ የዕረፍት ጊዜ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ቢሆንም ሰውነትን በጉልበት ሥራ ማፍታታት መባል የለበትም፡፡GWAmh 152.3

    ወንድሞቼ ሆይ ሰውነታችሁን ለማጠንከር በአትክልት ቦታችሁ ስትቆፍሩ ልክ በጉባዔ ስትናገሩ የምትፈጽሙትን ሞያ አንዳከናወናችሁ ይሰማችሁ፡፡ እግዚአብሔር አባታችን ስለሆነ ይወደናል፤ አካላችን አንዲጎሳቆል አይፈልግም፡፡ ሌላ የጤና ጠንቅ የምግብ አለመዋሃድ ነው፡፡ የማድቀቅ ኃይል ሲቃወስ አእምሮ በትክክል መሥራት አይችልም፡፡ ብዙዎች ዓይነታቸው የተለያየ የምግብ ዓይነቶች በችኮላ ስለሚበሉ የምግብ ማድቀቅ ሥርዓት ይቃወስና ሰውነት ይታወካል። ለጤና የማይስማማ ምግብና ከመጠን በላይ መብላት መከልከል አለበት፡፡GWAmh 152.4

    ብዙዎች ደግሞ የጤናን ሕግ በመቃወም በፈለጉት ጊዜ ይበላሉ፡፡ ይህን ጊዜ አእምሮአቸው ጉም ይለብሳል (ይጨልማል)፡፡ ሰዎች ራሳቸውን ካልገቱና የተሰጣቸውን መምሪያ ካልተከተሉ እንዴት ሰማያዊ ምሥጢር ይገለጥላቸዋልGWAmh 153.1

    ወንድሞቼ ሆይ ራሳችሁን መቆጣጠር የሚገባኙሁ ዛሬ አይደለምን? «በእሽቅድድም ቦታ የሚሮጡት ሁሉ እንዲሮጡ አንዱ ግን ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? አንዲሁም ታገኙ ዘንድ : የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፡፡ እነዚያ የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው እኛ ግን የማይጠፋውን፡፡ ስለዚህ እኔ ያለአሳብ እንደምሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፡፡ ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም፡፡ ነገር ግን ሰዎች ሰብኬ እኔ ራሴ የተጣልሁ አንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ፡፡» (1ኛቆሮ”. 9፡24-27)GWAmh 153.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents