Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሠራተኞችን ለማሰልጠን የአነጋገር ዘዴ

    በወንጌል ሥራችን ውስጥ ስሰአነጋገር በጥልቅ ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ዕውቀት ቢኖረንም የአነጋገራችን ፊሊጥ ካልሰመረ ዕውቀታችን ገደል ገባ ማለት ነው፡፡ ሀሳባችን ለዛ ባለው አነጋገር አስጊጠን ካላቀረብነው የትምህርታችን ጥቅሙ እምን ላይ ነው? የንግግር ችሎታችን ካላዳበርነው የዕወቀታችን ጥቅሙ አጭር ይሆናል፡፡ ግን ዕውቀታችን ለዛ ባለው ንግግር ታጅቦ የሰዎችን ስሜት ሲስብ ሲችል ጥረታችን ውጤቱ ያምራል፡፡GWAmh 53.1

    ለወንጌል ሥራ የሚሰለጥኑ ተማሪዎች ግልጽ የሆነ የማያዳግም ያነጋገር ዘዴ መማር አለባቸው:: ግልጽ ባሰ ቀላል አነጋገር መጠቀም ለማንኛውም የሥራ መስክ ይጠቅማል፡፡ ማርቆስ 14:34:GWAmh 53.2

    የእግዚአብሔር ቃል ባልተረታ አንደበት ምክንያት ትርጉሙ ሊጠፋ አይገባም፡፡ ስለሚሸጠው መጽሐፍ ጠቃሚነት በግልጽ ለማስረዳት የሚችል መጽሐፍ ሻጭ ለሥራው ክንውንነት ማግኘቱ አይጠረጠርም፡፡ ከመጽሐፉ አንድ ምዕራፍ እንዲያነብ ቢጠየቅ በድምጽ ትክክለኛ አነሳስና አወዳደቅ የአዳማጩን ጆር ሊማርክ መጽሐፉን በቀላሉ ለመሸጥ ይችላል፡፡GWAmh 53.3

    የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ለጉባዔ የሚያሰማ ሰው በሚያስደስት ድምዕ ካነበበ የአዳማጮችን ስሜት ሊመስጥ ይችላል፡፡ ወንጌላዊያን በግልጽና አስረግጦ በመናገር የቃላቱ ክብደት ለአዳማጮች ሕሊና ሊሰማ ይገባል፡፡ የወንጌላዊያኖችንን ያልተስተካከለ ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ያሳዝነኛል፡፡ እንደ እንደዚህ ያሉ ወንጌላዊን የእግዚአብሔርን ክብር ያስቀሩበታል፡፡GWAmh 53.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents