Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ጉድለትን ማስወገድ

    በአነጋገር በኩል ያለበትን ጉድለት በጥረት ሳያስወግድ ማንም ወንጌላዊ ብቁ ነኝ ማለት የለበትም፡፡ የመናገርን ዘዴ ሳይማር ለሕዝብ ለመናገር የሚሞክር ወንጌላዊ ውጤቱ አጥጋቢ አይሆንም፡፡ ምክንያቱም፣ የጉባዔውን ስሜት ሊሳብ : ማንኛውም ሰው የድምጹን አጠቃቀም ካላወቀ ነገር ሊያበላሽ ይችላል፡፡ ተናጋሪውና አድማጩ በሓይል ሲነጋገሩ አይጣጣሙም፡፡ ደረቅና የአዛዥነት ስሜት የሚያጠቃቸው ድምጾች ወዳጆችን አጣልተው ለነፍሳት መጥፋት ምክንያት ሆነዋል፡፡GWAmh 53.5

    በሕብረት ስብሰባ ግልጽ የሆነ ንግግር ማህበረተኞችን ያቀራርባል፡፡ ችግሮች ይወገዱና ኀብረትን ያጸናል:: አብዛኛውን ጊዜ ግን ምስክርነት ሲሰጥ በጐለደፈ አንደበት ባልተስተካከለ ድምጽ ስለሚሆን መግባባት ይጐድላል፡፡ ስለዚህ በረከት ይቀንሳል:: የሚጸልዩ ወይም የሚናገሩ ግልጽ በሆነ አነጋገር ይናገሩ፡፡ በትክክል የሚቀርብ ፀሎት ኃይል : መዝገብ ለሰዎች ለማስረከብ የአምላክ የመገናኛ ዘዴ ነው:: ለእግዚአብሔር የቀረበው ፀሎት ተሰሚነት ሲያጣ ሰይጣን ይደሰታል፡፡ የእግዚአብሔር ሰዎች ሲጸልዩና ሲናገሩ የሚያምኑትን በግልጽ ለማስረዳት መቻል አለባቸው፡፡ በንግግራችን እግዚአብሔርን ልናከብረው እንችላለን፡፡GWAmh 54.1

    እግዚአብሔር ሰዎችን ለከፍተኛ ይጠራቸዋል፡፡ ለአምላክ ክብር ለመመስክር የሚችል ሰው በግደየለሽነት አነጋገሩን ሲያዝረከርክ እግዚአብሔርን አዋረደ ማለት ነው፡፡ ቃለ እግዚአብሔር በአሳላፊዎች ምክንያት ተቀባይነት ሊያጣ ይችላል፡፡ ማንም በተሰናከለ አነጋገር ክቡር ዕውነትን አያራክስ:: የመገናኛ ዘዴአቸውን ሳያደረጁ ለወንጌል ስራ በቅተናል የሚሉ መጀመሪያ የንግግር ጉድለታቸውን ማሟላት አለባቸው፡፡GWAmh 54.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents