Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የተሳሳቱ ዘዴዎች

    አስተዋይ አእምሮ ያላቸው፣፤ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ያላቸው እውነት የጠለቀ ሳለ በተሳሳተ የአሠራር ዘዴአቸው ብቻ ሥራቸው የማይሳካላቸው ብ ሰዎች አሉ፡፡ ነፍሳትን በማዳን ሥራ የተሰለፉ ሰዎች በጉጉት የጀመሩትን ሥራ ከልብ ስለ ማያካሄሂዱት ሳይቀናቸው ይቀራሉ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ሰለ ሰዎቹ የተሳሳተ አስተሳሰብ ያድርባቸውና ሳይግባቡ ይቀራሉ፡፡ አንዳንዶቹ አንደ አካባቢው ሆነው ሰዎቹን አሉበት ቦታ ማንሳት አንዳለባቸው ነኩሮአቸውን አሻሸለው ከእውነተኛ የክርስትና ደረጃ አንዲደርሱ ከሚረዲቸው ሰዎች ጋር ራሳቸውን አንድ አድርገው አይቆጥሩም፡፡ ሌሎችም በክርክር ብቻ ስለሚተማመነ አይቀናቸውም፡፡ እግዚአብሔርን በጥበብ እንዲመራቸው በጸጋው አእንዲቀድሳቸው አይለምኑትም፡፡GWAmh 251.2

    ወንጌላዊያን በጨሰማ ውስጥ ከሚዳበሱት አዲስ ሰሚዎች ብዙ ነገር አይጠባበቁ፡፡ ያለመንፈስ ቅዱስ መሪነት ጥረታቸው ክንቱ መሆኑን አምነው ሰሚዎቻቸው በመንፈስ ቅዱስ ተነክተው እውነትን እንዲለዩ በእግዚአብሔር ጥበቅ እምነት ይኑራቸው፡፡ በየግለሰቡ ያለውን የአስተሳሰብ ልዩነት በመገንዘብ ከሰዎች ጋር በሚያደርጉት አቀራረብ ትዕግሥትኞች መሆን ያሳቸዋል፡፡ የሱስን ገለል በማድረግ የበሳይነቱን ለራሳቸው አንዳይዙ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡GWAmh 251.3

    በሙሉ ሀሳባቸው ለመሥራት የማያቋረጥ ትግል ማስፈለጉን በመዘንጋት የማይሳካላቸው ወንጌላዊያን አሉ፡፡ ዕውነተኛ ሠራተኞች ስላልሆነ ከመናገሪያው ቦታ ሲወርዱ ተግባራቸውን ያቆማሉ፡፡ ከቤት ወደ ቤት እየዞሩ ቤተሰቦችን ማስተማር አይፈልጉም፡፡ ለሚጠነዋቁላቸጡ ነፍሳት ደግና አሳቢዎች የሚያደርጋቸውን ተፈላጊ የክርስትና አክብሮት ለማግኘት መጣር ይገባቸዋል፡፡ እንዲህ ከልብ ከሠሩ የሕይወትን መንገድ ሊያስይዚቸው ይችላሉ፡፡GWAmh 251.4

    በሰብዓዊ ዘዴ ሰዎችን በመሳብ ጊዜአዊ ክንውንነት የሚያገኙ ወንጌላዊያን አሉ። የሰዎችን ስሜት አንደቦይ ውኃ በመምራት አሁን አስለቅሰው ወዲያው የሚያስቁ አሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ የብዙዎቹ ስሜቶ ተነሳስቶ ክርስቶስን ተቀበልን ይላሉ፤ መነቃቃትም የመጣ ይመስላል፡፡ ግን ፈተና ሲመጣ መቆም የለም፡፡ ስሜታቸው ተነሳስቶ ብዙኑዎች ከሰማይ በሚያደርስ በሚመስል ማዕበል ይጠረጋሉ፡፡ ነገር ግን የችግር ጎርፍ ሲመታ መቋቋም አይችሉም፡፡ እንዲህ ያለ ሠራተኛ ራሱን አታልሉ አዳማጮቹንም በተሳሳተ መንገድ ይመራል፡፡GWAmh 252.1

    ወንገጌላዊያን የእግዚአብሔርን ሥራ በራሳቸው ዕቅድ እንዳያበላሱ መጠንቀቅ አለባቸው፡፡ አንዳንዶቹ በተወሰነ ሰበካ (ቀበሌ) ሥራቸውን በመወሰን የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ ያጠባሉ፡፡ ለተለያዩት ብዙዙ የሥራ ዘርፎችም መንገድ አይጠርትም፡፡GWAmh 252.2

    ሌሎችም ብዙ አኩል ተፈላጊነተ ያላቸው አርዕስቶች አያሉ አንድ አርዕስት ብቻ የሚመርጡ አሉ፡፡ እንዲህ ያሉት ሰዎች «አንድ- ፊት»ይባላሉ፡፡ ያለ ጥረታቸጡን ሁሉ ለጊዜው ትዝ ባላቸው አርፅስት ላይ ያውሱሉታል። ይህ በተለየ የሚወዱት ትምህርት አርዕስት የሀሳባቸው መጀመሪያና መደምደሚያ፣ የንግግራቸው መነሻና መድረሻ ነው፡፡ ሌላጡ ነገር ሁሉ በዋለው ይቀራል (ይረሳል)፡፡ ያው ክንድ ሀሳብ ሲነገርለትና ሲተረትለት ከመና'ሩ የተነሳ በሰዎች ዘንድ የመሰልቸት ያጋጥመሥመዋል፡፡GWAmh 252.3

    አንዳንድ ወንጌላዊያን ደግሞ ትልቅ ጉባዔን በውጫዊ ሁኔታ በመሳብ የሚሳካላቸው እየመሰላቸው ታቃለ-እግዚአብሔርን በቂያትር መልክ ለማቅረብ የሚሞክሩ አሉ፡፡GWAmh 252.4

    ይህ ከእግዚአብሔር የተላከውን አሳት በመጠቀም ፋንታ እንግዳ አሳት እንደመጠቀም ይቆጠራል፡፡ እግዚአብሔር በእንዲህ ያለው ሥራ አይደሰትም፡፡ የክርስቶስን መንገድ በመከተል አንጂ በውጫዊ ታይታና በውድ ጌጣ ጌጥ በመብለጭለጭ ሥራውን ፍጻሜ ለማቅረብ አይቻልም፡፡ «በኃይልና በብርታት አይደለም በመንፈሴ ነው አንጂ ይላል እግዚአብሔር የሠራዊት ጌታ» (1ካ. 4፡6) ሁለት አፍ አንዳለው ሰይፍ ቆርጦ ሊገባ የሜችል ያልተስፋፈነ እውነት ነው። ወንጌል ከእግዚአብሔር ሃሳብ ጋር ተስማምቶ ሲቀርብላቸው ሰዎች ይቀበሉታል፡፡GWAmh 252.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents