Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 12—ማጠቃለያ ኃይል ለአገልግሎት ቤተክርስቲያን

    ቤተክርስቲያን በዚህ የመጨረሻ ጊዜ አንደ ጳውሎስ ራሳቸውን ላይ ለማዋል የሠለጠኩ፤ የእግዚአብሔርን ሥራ በሚገባ ያስተዋሉ፤ ትጋትና ዕውነተኛነት ያላቸው አርበኞች ያስፈልጓታል፡፡ የተቀደሱና ራሳቸውን የሰዉ፤ ችግርንና ኃላፊነትን የማይፈሩ፤ ጀግኖችና ዕውነተኞች፣ የተስፋ ሁሉ ክብር የሆነው ክርስቶስ በልባቸው ያደረባቸው፤ አናናራቸው በቅዱስና ተነክቶ ቃሉን የሚሰብኩ ሰዎች ያስፈልጋሉ፡፡ እንዲህ ያሉ ሰዎች በመታጣታቸው የአግዚአብሔር ሥራ ተጎሳቁሏል፡፡ አደገኛ ሐሰት ያብዛኛውን ሰብዓዊ ፍጡር ግብረ-ገብ መርዞታል፤ ተስፋውንም አጨልሞበታል፡፡GWAmh 339.1

    በእግዚአብሔር ዘንድ ስዎች ተብለው የሚቆጠሩና ስማቸው በሰማይ መጽሐፍ የሚመዘገቡ አንደ ዳንኤል የእግዚአብሔርን መንግሥት በክፋት ለተዋጠ ዓለም ለማሳየት ከልባቸው የተጣጣሩ ብቻ ናቸው፡፡ በዕውቀች መግፋት ተፈላጊ ነው፡ ለእግዚአብሔር ሥራ የዋለ እውቀት ውጤቱ መልካም ነገር ነው፡፡ ዓለም ርቀው የሚያስቡ፣ መመሪያ ያላቸው፣ በዕውቀትና በጥበብ የሚያድጉት ሰዎች ይፈልጋል፡፡ ዕውነቱ ለወገን፣ ለቋንቋ ለሕዝብ ይዳረስ ዘንድ በስነ ጽሑፍ የበሰሉ ሰዎች ይፈለጋሉ፡፡GWAmh 339.2

    « እንዲሞላ ወደ መንገድና ወደ ቅጥር ውጣና ይገቡ ዘንድ ግድ በላቸው፡፡» (ሉቃስ 14፡23) አለ ክርስቶስ፡፡ ይህን ትዕዛዝ በማክበር በቅርብም በሩቅም ወዳሉት አህዛብ መሄድ አለብን፡፡ «ቀራጮችና አመንዝሮች» የእግዚአብሔርን ቃል መስማት አለባቸው፡፡ በሠራተኞቹ ትዕግስትና ደግነት መልዕክቱ ከኃጢዓት አዘቅት ውስጥ የሰጠሙትን አንዲወጡ ያደርጋል፡፡GWAmh 339.3

    የክርስትና ፍልስፍና ሰይጣን ሊያጠፋቸው ለሚሹት ነፍላት በትጋትና በታማኝነት መሥራትን ያደፋፍራል፡፡ ልባዊና ዕውነተኛ የሆነው ኃይል ለነፍሳት ደህንነት ሲሠራ ምንም ነገር ሊያቀዘቅዘው አይገባም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ክርስቶስን አንዲቀበሉ ነፍሳትን ለማነቃቃት አጣዳፊ ጥሪ መኖሩን አትርሳ፡፡ ሰዎችን በግልም ሆነ በጉባዔ ወደ ክርስቶስ አንዲቀርቡ ለመገፋፋት ማንኛውንም አጋጣሚ ከሥራ ላይ ማዋል አለብን፡፡ ኃይላችን በሙሉ ሰዎችን ወደ ክርስቶስ ለማመላክትና መስዋዕትነቱንና- አዳኝነቱን አንዲቀበሉ ለመገፋፋት አናውለው፡፡ የእግዚአብሔርን ስጦታ በሙሉ ለስመሙሙ ክበር እንዲያውሉት እናስተምራቸው፡፡GWAmh 340.1

    በእግዚአብሔር ዘንድ የሚታይ የሠራነው ጊዜ ርዝመት ሳይሆን ለሥራው ያሳየነው ታማኝነትና ፈቃደኝነት ነው፡፡ በአገልግሎታችን ሁሉ ራስን ፈጽሞ ማስረከብ ይፈልግብናል፡፡ ራስን በመውደድ ከሚሠራና ከሚበላሸ ትልቅ ሥራ ይልቅ በዕውነት የተፈጸመ ዝቅተኛ ተግባር እግዚአብሔርን ያስደስታል፡፡ ምን ያህል መንፈስ እንዳደረብንና ሥራችን ምን ያህል ክርስቶስን የሚገልጥ መሆኑን ያመለክታል፡፡ ከምንሠራው የሥራ ብዛት ይልቅ ለፍቀራችንና ለታማኝነታችን ከፍተኛ ግምት ይሰጠዋል፡፡GWAmh 340.2

    ክርስቶስ በውስጣችን የሜገኝና የእግዚአብሔር ሠራተኛች ተብለን የምንቅጠር ራስን ወዳድ መሆናችን ሲቀር፣፤፣ ለበሳይነት መተናነቅ ሲቀር፤ ልባችን በምሥጋና ሕይወታችን በፍቅር መዓዛ ሲሞላ ብቻ ነው፡፡GWAmh 340.3

    በዓለም ከሚገኙት ሰዎች ሁሉ አገልጋዮች ከሁሉም የበለጡ ራሳቸውን የካዱ፤ ደጎች፣ አክባሪዎች መሆን አለባቸው፡፡ በኑሮአቸው ውስጥ ራስን ያለመውደድ የሥራ ውጤት ሊታይበት ይገባል፡፡ ትህትና የጎደለው፣ የሌሎችን አለማወቅ የማይታገሥ፣ በችኮላ የሚሠራና ሳያስብ የሚናገር ሠራተኛ የሰዎችን ልብ እንዳይቀበሉት ይዘጋል፡፡GWAmh 340.4

    ጤዛና ጠል የጠወሰ\ለጉትን አትክልት አንደሚያጠጡ ሁሉ፤ ሰዎችን ከስህተት ለመመለስ የለዘቡ ቃላት ያስፈልጋሉ፡፡ የእግዚአብሔር የመደመሪያ አቅድ ከሰዎች ጋር መግባባት: ሕይወትን ለማደስ ኃይል እንዲሰጠው በእግዚአብሔር በመተማመን ቃሉን በፍቅር መዝራት አለብን፡፡ በፍቅር የተነገረውን ቃሉን መንፈስ ቅዱስ በሰዎች ልብ ተቀባይነት አንዲኖረው ያደርገዋል፡፡GWAmh 341.1

    በተፈጥሮአችን ለራሴ ባዮች ነን፡፡ ነገር ግን ክርስቶስ እንድንማር የሚፈልግብንን ትምህርት ስንማር ከርሱ ጠባይ ያካፍለናል፡፡ ስለዚህ እርሱ እንደኖረ አንኖራለን፡፡ የክርስቶስ አስገራሚ ምሣሌነት፣ በሴሎች ያሳየው ታላቅ ርህራሄ፣ ከሚያለቅሱ ጋር በማልቀስ፤ ከሚደሰቱ ጋር በመደሰት፣ ሌሎቹን እንደርሱ ለማድረግ አራአያነቱ ታላቅ : በመልካም አነጋገርና በቀና ሥራ መንገዱ ለስላሳ ጎዳናውን ለደከሙ እግሮች እንቀፋት ያደርጉታል፡፡GWAmh 341.2

    የትምህርት ዋና ዓላማው ዕውቀት ማከማቸት ሳይሆን የተማሩትን ትምህርት ከሥራ ላይ ማዋል ነው፡፡ አእምሮ- ከአእምሮ ተጋጭቶ የተገኘው ከፍተኝና ኃይል ከጥቅም ላይ ቢውል ውጤቱ ያምራል፡፡ ሕይወት የሜገኘው ከሕይወጠት ብቻ ነው፡፡ ዓለምን የባረከውን ሕይወት ከለገሠው መለኮታዊ ሕይወት ጋር ለሦስት ዓመታት በየዕሰቱ አብረው የኖሩት ሰዎች እንዴት እድለኞች ናቸው፡፡ ዮሐንስ የተወደደው ደቀ መዝሙር ከጓደኛቹ አብልጦ ሕይወቱን ለዚህ ግሩም ሕይወት አስገዛ፡፡ እንዲህ ይላል «ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል፣፤ አንመሰክርማለን፣ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘለዓለምን ሕይወት አናወራላች3ኋለን፡፡» (1ኛ ዮጠ. 1-2) « ሁላችን ከሙላቱ ተቀበልን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልፍ» (ዮሐ.1፡16) በጌታችን ሐዋርያት ሕይወት ውስጥ የሚያስከብራቸው ምንም የራሳቸው ነገር አልነበራቸውም፡፡GWAmh 341.3

    የሥራቸው ውጤት ያማረላቸው በእግዚአብሔር እርዳታ መሆኑ ግልጥ ነው፡፡ የነዚህ ሕይወት፣ ያገኙት መልካም ጠባይ፣ እግዚአብሔር በነርሱ አማካይነተ የሠራው ታላቅ ሥራ እግዚአብሔር ለመማርና ሰመታዘዝ ፈቃደኛች ሁሉ የሚያደርገውን ቸርነት ይገልጣሉ፡፡ ክክብር ትህትና ይቅደም፡፡ ከሰዎች ሁሉ የበለጠ ደረጃ ለማስያዝ በአምላክ ፊት አንደ ዮሐንስ ራሱን ዝቅ ያደረገውን ሰው ሰማይ ይመርጠዋል፡፡ ከሁሉም እንደ ሕፃን የሆነው ደቀመዝሙር ከማንም የበለጠ የሥራ ክንውንነት ያገኛል፡፡ ራሱን ከፍ ለማድረግ ሳይሆን ፃፍሳትን ለማዳን ከሚጥር ሠራተኛ ጋር የሰማይ መልዕክትኛች በጎኑ ይሰለፋሉ፡፡ መለኮታዊ እርዳታ አንደሚያስፈልገው የሚያውቅ ሰው ስለሚሜለምን መንፈስ ቅዱስ የሱስን ያሳየዋል፤ ስለዚህ ሕይወቱን : የሚያደርግ ብርታት ይቀበላል፡፡ ከክርስቶስ ጋር ግንኙነት ካለው በኃጢዓት የጠፉትን ለማዳን ወደፊት ይገሠግሣል፡፡ ለሥራው ስለተቀባ ከፍተኛ የአእምሮ ችሎታ ያላቸውን ተማርን ተመራመርን ያሉት ያቃታቸውን እርሱ ያክናውነዋል፡፡GWAmh 342.1

    ሰዎችን ወደ ንስሐ የሚጠራ በጸሎት መጠመድ አለበት፡፡ «ካልባረክኝ አልለቅም፣ ነፍሳትን ወደ ክርስቶስ ለመመለስ ኃይል ስጠኝ» እያለ ወደኃያሉ አምላክ መጠጋት ይገባዋል፡፡GWAmh 342.2

    ጳውሎስ «ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝ» (2ኛ ቆሮ” 12፡10) : ደካምነታችን ስንገነዘብ በማይዝል ኃይል ላይ አንደገፋለን፡፡ በልባችን እግዚአብሔር ከሰጠን ኃላፊነት የበለጠ ልናሰላስለው የሚገባን ነገር የለም፡፡ አንደ ክርስቶስ የይቅር ባይነት ና:ቅር አድርጎ ልብን የሚነካ ነገር የለም፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ስንቀራረብ መንፈስ ቅዱስን ስሰሚሰጠን ሰዎችን ለመቅረብ አንችትላለን፡፡ በክርስቶስ አማካይነት ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ የሰማይ ቤተሰብ አባል ሰለሆናችሁ ተደሰቱ፡፡ ከራስህ ሌሳ ከፍተኛ ነገር የተመሰከትህ አንደሆን የሰብዓዊ ፍጡርን ድካም ተገነዘባለህ፡፡ ራስህን እንደናቅህ መጠን የክርስቶስ ደግነት በበለጠ ይስተዋልፃል።፡- ከብርሃንና - ከሕይወት ምንጭ ጋር አንደተቀራረብህ መጠን በአንተ ላይ የበለጠ ብርሃን ይበራልሃል፤ ለሥራም የበለጠ ኃይል ትተበላለህ፡፡GWAmh 342.3

    ለሥራችን ከእግዚአብሔር ጋር ከመገናኘት የበለጠ ተፈላጊ ነገር የለም፡፡ በዕለት ነሮአችን በመድኃኒታችን አማካይነት ሰላምና ዕረፍት እንዳገኘን መግለጥ አለብን፡፡ በልባችን ሰላሙ ካደረብን ገጻችን ይነግራል፡፡ ለምንናገረው ቃል ኃይል ይሰጠዋል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት ጠባይንና ሕይወትን ጨዋ ያደርገዋል፡፡ ሰዎች ክየሱስ ጋር እንደነበሩት እንደ መደመሪያዎቹ ደቀመዛሙርት አድርገው ይገምቱናል፡፡ ሠራተኛው ሌላ ነገር የማይሰጠውን ከፍተኛ ኃይል ይቀበላል፡፡ ይህ ኃይል እንዲቀርበት ለራሱ ምክንያት አንዳይሆን፡፡ ነሮአችን ሁለት ዓይነት ይሁን፡፡ ማሰብና መሥራት፣ ጸሎትና ምግባር ያስፈልጋሉ፡፡ ክእግዚአብሔር ጋር በመተባበር የምናገኘው ብርታት ከጥረታችን ጋር ሲተባበር ለቀን ነ‹ሮአችን ከማዘጋጀደቱም በላይ በምንም አስቸጋሪ ጊዜ ቢሆን መንፈሳችን ሰላማዊ ያደርነፃዋል፡፡GWAmh 343.1

    ከልቡ ለተሰሰፈ ሠራተኛ ክርስቶስ እንካህ.ን በዚች ምድር ሳለ ከአብ ዘንድ ርዕዳታ መጠየቁ ትምህርት ሊሆነው ይችላል፡፡ ከአብ ጋር በነበረው ግንኙነት ሌሎችን ሊያበረታና ሲባርክ አነሆ የእግዚአብሔር ልጅ በአብ ፊት ለጻሉሎት ተንበርክኳል! የእግዚአብሔር ልጅ ቢሆንም ቅሉ፤ አምነቱን በጸሎት ኃይል አበረታ፣ ከሰማይ ጋር ግንኙነት በማድረግ ክፉን የሚቋቋምበት ኃይል ተቀበለ፡፡ ታላቅ ወንድማችን አንደመሆኑ መጠን በዓለም ውስጥ ሆነው ሊያገለግሉተ የሚኩት ምን አንደሚያስፈልጋቸው ያውቃል። የሚልካቸው መልዕክትኞች ደካሞችና ተሳሳቾች መሆናቸውን : ቢሆንም ሊያገልግሉት ለቀረጡ ሁሉ መለኮታዊ እርዳታ ይሰጣቸኛዋል፡፡ ከኃጢዓት ጋር ለሚደረገው ትግል የማይዝልና የጸና ሃይማኖት በእግዚአብሔር ሳላይ ያለው ሰጡ የመንፈስ ቅዱስን አርዳት ተቀብሎ እንደሚያሸንፍ የመድኃኒታችን ሕይወት ማስረጃ ነው፡፡GWAmh 343.2

    የክርስቶስን ምሣሌነት የሚክተል ማንኛውም ሠራተኛ እግዚአብሔር መከሩን ለማሰብሰብ ለቤተ ክርስቲያን ለመስጠት ቃል የገባውን ኃይል ይቀበላል፡፡ የጋዐንጌል መልዕክትኞች ጧት ጧት በጸሎት ተንበርክከው ቃል ኪዳናቸውን በጌታ ፊት ሲያድሱ መንፈሱን ካነቃቁና ከቀዳሽ ኃይሉ ጋር ይሰጣቸዋል፡፡ ወደየቀን ግዳጃቸው ሲሰማሩ የማይታየው የመንፈስ ቅዱስ እርዳት «ከእግዚአብሔር ጋር አብረው የሚሠሩ-» ዘ1ኛ ቆሮ. 3፡9) ያደርጋቸዋል፡፡GWAmh 343.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents