Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ቀላል ዕውቀት

    ወጣት ወንጌላዊ በመጠነኛ ዕውቀቱ ተማምኖ መቀመጥ የለበትም:: ምክንያቱም የት ሄዶ ለማስተማር አንደሚጠራ ስለማያውቅ : ብዙዎች ለምሰክርነት በነገሥታትና በሊቃውንት ፊት ይቆሙ ይሆናል፡፡ ስለመጽሐፍ ቅዱስ ጥልቅ ዕውቀት የሌላቸው ወንጌላዊያን ሳያፍሩ የወንጌል ገበሬዎች ለመሆን ያዳግታቸዋል፡- ይደናገራቸዋል! የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅስ በግልጽ ለማብራራት አይችሉም፡፡ የወንጌል ሥራ በተማሩ አገልጋዮች ወደኋላ መጉተቱ ያሳዝናል፡፡ ብዙዎች የግብረ-ገብና የአእምሮ መሻሻል ያስፈልጋቸዋል፡፡ አእምሮአቸውን አስጨነቀው፤ የተደበቀውን መዝገብ ከልብ አይሹም፡፡ ላይ ላዩን በመነካካት የላይ ዕውቀት ይቀራሉ፡፡GWAmh 57.2

    ሰዎች ራሳቸውን ለማሻሻል ሳይሞክሩ በጭንቅ ጊዜ ከመልካም ደረጃ ላይ እንወጣለን ብለው ያስቡ ይሆን” ለሥራው ገጣሚ ሆነው ለመገኘት ባላቸው ችሎታ ሳይጥሩ ለእግዚአብሔር የተመረጡ ዕቃ ሆነው ለመገኘት ያስቡ ይሆን? የእግዚአብሔር ሥራ ለማቀድ፣ ለመምራት፣ ለማነጽ፣ ለማደራጀት የሚችሉ ትጉ ሰዎች ይፈልጋል፡፡ በይሆናል ብቻ የሚጐተቱ ሠራተኞች ነን ባዮች በኃጢያት የቆሰሉትን ነፍሳት ለማዳን ዕውነተኛ ትምህርት ያሻቸዋል፡፡GWAmh 57.3

    ወንጌላዊ የበቃኝን ያህል ተምሬአለሁ ብሉ አፎይ ማለት የለበትም፡፡ በእየቀኑ ከትምህርት ላይ ትምህርት በመጨመር ዕድሜ ልኩን መማር አለበት:: በመሠልጠን ላይ ያሉት ዕጩ ወንጌላዊያን ሊረሱት የማይገባቸው ከሁሉ በበለጠ የሚያስፈልገው የልብ ዝግጅት መሆኑን ነወ፡፡ የልቦናን ዝግጅት የአእምሮ ብስለት ወይም የትምህርት ጥልቀት አይስተካከለውም፡፡ በጨለማ ላሉት ብርሃን ከማዳረሱ በፊት በሠራተኛው ልብ ውስጥ የጽድቅ ብርሃን ጨረር ማብራት አለበት፡፡GWAmh 57.4

    ሌሊት አምላክ ስለሥራው ራዕይ ገለጠልኝ፡፡ የሁሉ ባለሥልጣን የሆነው አምላክ የላከልኝን መልዕክት ለመናገር አሞክራለሁ፡፡GWAmh 58.1

    የወንጌል ሥራ መዳከሙ ነው: ምክንያቱም ቅዱስ ሥራ ሳይዘጋጁ የሚሰለፉት በመበርከታቸው ነው፡፡ አንዳንዶቹ (በአጋጣሚ) ለሥራው ተካፋይ ለመሆን ይሞክራሉ:: በሌላ የሥራ መስመር ቢሰለፉ የበለጠ ውጤት ባስገኙ ነበር፡፡ ከአሥራት ገንዘብ ደሞዝ ቢከፍላቸውም ሥራቸው የተዳከመ ነጡ፡፡ ለዚህ ዓይነት ሥራቸው የአሥራትን ገንዘብ ማባከን የለባቸውም፡፡ በብዙ መንገድ የወንጌል አገልግሎት መልኩንና የተቀደሰ ዓላማውን ስቷል፡፡GWAmh 58.2

    ለወንጌል ሥራ የተጠሩ ሰዎች ራሳቸውን ለመስዋዕትነት ከማቅረብ ወደኋላ የማይሉ መሆን አለባቸው፡፡ ነፍሳትን መመለስ ታላቅ ሥራ ነው::: ለዚህ ቅዱስ ሥራ የተሰለፉ ሰዎች ቆርጠው መሥራት አለባቸው፡፡ የማያቋርጥ የፀጋ ኃይል ካልተሰጣቸው የሚወድቁ መሆናቸውን ተገንዝበው በርትተው መሥራት አለባቸው፡፡ ሠራተኞቹ እንዲህ ከሆኑ ፍሬ ያመርታሉ፡፡ ብዙ ነፍሳት ከዕውነቱ ጋር ይተዋወቃሉ፡፡ የእግዚአብሔር ሀሳብ ሰልጆቹ ማንም ሰብዓዊ አዕምሮ-: ሊመራመረው የማይችል ከፍተኛ ነው:: ሊደረሰብት የሚፈለገው ግብ አምላክን እንዲመስሉ ነው:: ተማሪው የማያቋርጥ ዕድገት ይጠብቀዋል፡፡GWAmh 58.3

    መልካምነትን፣ ንጽህናንና ጨዋነትን የሚያጠቃልል ደረጃ አንዲደርስ ከፍተኛ ሙያ አንዲያከናውን ታቅዶለታል፡፡ በተቻለው ፍጥነት የተቻለውን ያህል የዕውነተኛውን ዕውቀት ቅርንጫፎችና ዘርፎች መከታተል አለበት፡፡ መጽሐፍ መስጥ ለወንጌላዊነት እንደ ትምህርት ይቆጠራል፡፡GWAmh 58.4

    ወጣቶች ለወንጌል ሥራ ልምድ ከሚያገኙባቸው የሥራ ዓይነቶች አንዱ መጽሐፍ መሽጥ ነው:: ጠቃሚ ዕውነት የያዙትን መጻሕፍት ለመሸጥ ከከተማ ወደ ከተማ ይዘዋወራሉ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ጊዜ ዕውነትን የማዳረስ ዕድል ያጋጥማቸውና የዘሩት ዘር ፍሬ ያፈራል፡፡ ሕዝቦችን ተገናኝተው ጽሑፎቻችን ሲያደርሱ መልካም የሥራ ልምድ ያገኛሉ፡፡ ወጣቶች ነፍሳትን የማዳን ስሜት ገፋፍቷቸው በሥራው የተሰለፉበት እንደሆን ከጥረታቸው የተነሳ ታላቅ መክር ለአምላካችን ይሰበሰባሉ፡፡ ከዚያ ከኋላ ሚሲዮናዊያን ሆነው ይሥሩ:: የሚያዳርሱት መልዕክት የእግዚአብሔር መሆኑን ::GWAmh 58.5

    ወንጌላዊያን ለመሆን ለሚሹና ራሳቸውን ሳይቆጥቡ ለአምላክ ለማስረከብ ለሚፈልጉ መጽሐፍ መሸጥ ዋና መዘጋጃቸው ሊሆን: ለእግዚአብሔር መንጋ ጠባቂ እንዲሆኑ ሰዎችን የሚያዘጋጃቸው የመንፈስ ቅዱስ መሪነት ነው፡፡ ክርስቶስ አንደማይለያቸው ሲገነዘቡ ፈተናም ቢገጥማቸው ደስታና ፍሰሀ ከቶ አይለያቸውም፡፡ ሲሠሩ መጸለይ በትዕግሥት፣ በደግነት፣ ሳይሰለቹ፤፣ ለመማር ፈቃደኛ ይሆናሉ፡፡GWAmh 59.1

    ክርስቶስ መሪያቸው መጥፎ ቃላትና ያልተባባሱ አነጋገር የማያስደስተው መሆኑን በመገንዘብ የታረሙ ትሁታን ክርስቲያናት ይሆናሉ፡፡ ከአንደበታቸው የሚወጡት ቃላት የታረሙ ይሆናሉ:: የመናገር ችሎታቸው ከላይ የተቀበሉት የክበረ መክሊት መሆኑን ያምኑበታል፡፡GWAmh 59.2

    ሰብዓዊ ወኪል መለኮታዊ አምላኩን በትክክል ሊወክል ቅዱስ መንገዱን ስለተማረ፣ ቀንበሩን ስለተሸከመ የማይታይ የማይለየውን ቅዱስ ያከብረዋል፡፡ ከሃይማኖት የጐለመሱ ከዚህ ቢሹት የማይገኝ ደረጃ ይደርሳሉ:: መልዕክቱን በተዋበ ዕውነት አስጊጠው ለማቅረብ ችሎታ ይሠጣቸዋል፡፡GWAmh 59.3

    ወጣቶች ሆይ ጌታን ለማወቅ ብትከታተሉ «አንደ ወገግታ ተዘጋጅቶ” ታገኙታላችሁ:: ለመሻሻል ዘወትር አትስነፉ:: ከመድኃኒታችን ጋር የቅርብ ግንኙነት አንዲኖራቸሁ ከልብ ታገሉ፡፡ እንደሠራው ለመሥራት ሞክሩ፡፡ ሕይወቱን የለወጠላቸውን ነፍሳት ለመመለስ በርትታችሁ ሥሩ፡፡ የምታገኙአቸውን ሁሉ ሞክሩ፡፡ ከዚያም ጥቂት፣ ከዚህም ጥቂት ጨማምሮ ዕውቀታችሁን የሚያዳብረውን ወንድማችሁን ክርስቶስን አትልቀቁ: ለጠፋው ዓለም ራሱን ከሠዋው ጋር ቅርብና ጥብቅ ግንኙነት ካደረጋችሁ ብቁ ሠራተኞች ትሆናላችሁ፡፡GWAmh 59.4