Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሥራ ማብዛት የሚያሰከትለው አደጋ

    ሕዋርያት ከወንጌል ሥራ ሲመለሱ መድኒታችን «ወደ በርሃ ዕረፉ»። አላቸው፡፡ በሙሉ ኃይላቸው ይሠሩ ስለነበር አካልና ክእምሮአቸው ዝሎ ስለነበር ማረፍ ነበረባቸው፡፡GWAmh 154.4

    ክርስቶስ ያን ጊዜ ለነበሩት ደቀመዛሙርቱ እንዳዘነ ሁሉ ለዛሬዎቹም “ዮና ዕረፉ» (ማር. 6፡31) : ይህን የሚናገር አሰከሚደክማቸው ለሠሩት ነው፡፡ በመንፈሣዊ አገልግሉት ቢሆንም ሁል ጊዜ በሠራና በስጋት መኖር ተገቢ አይደለም፡፡ እንዲህ ከሆነ ሰውነት፣ አእምሮ የግል ሃይማኖትም ይዳከማል፤ ለክርሰቶስ መሥራት ራስን መካድና መስዋዕተነትን ይጠይቃል፡፡ ነገር ግን የጤናን ሕግ ተላልፎ የራስን ሕይዎት ከአደጋ ላይ መጣል እግዚአብሔርን ያሰቀይማል፡፡GWAmh 154.5

    የሱስ ራሱ ተአምራት ሠርቶ ለደቀመዛሙርቱም ተአምራት የመሥራት ኃይል ቢሰጣቸውም የደከሙት አገልጋዮቹ እንዲያርፉ አዘዛቸው፡፡ መክሩ በዝቶ ሠራተኞች ማነሳቸውን ሲናገር ለዕረፍት እንዲሠሩ አላዝዘዛቸውም፡፡ በዚህ ፈንታ «የመከሩን ጌታ ለምኑ ለመከሩ ሠራተኞች ይልክ ዘንድ» (ማቴ.9፡38) አለ፡፡ እግዚአብሔር ለሁሉም እንደችሎታው ሥራ ሰጥቶታል፡፡ ይህን ያደረገበት ምክንያት አንዱ ከመጠን በሳይ ሥራ ሲበዛበት ሴላው ሥራ ፈትቶ አንዳይቀመጥ ነው፡፡GWAmh 154.6

    የክርሰቶስ አገልጋዮች ጤናቸውን እንዲበድሉ አይፈለግም፡፡ በሥራ ብዛት ጤናውን በድሎ መሥራት አስኪያቅተው መሠቃየት የለበትም፡፡GWAmh 155.1

    የሁለት ቀን ሥራ በአንድ ቀን ለመጨረስ አትሞክሩ፡፡ ኃይላቸውን ቆጥበው በዝግታ የሚሠሩ ተጣድፈው ኃይላቸውን ከሚጨርሱት ያላነሰ ሥራ ያከናውናሉ፡፡GWAmh 155.2

    የእግዚአብሔር ሥራ ዓለም አቀፍ ስለሆነ እያንዳንዷን ንኡስ ችሎታ (መክሲት) ከሥራ ሳይ ማዋል አለብን፡፡ መክሩ መድረሱን ሲመሰከቱ ሠራተኞች ኃይላቸውን ይቀንሳሉ የሜል ስጋት አለ፣ እግዚአብሔር ግን ይህን አይፈልግም፡፡ አገልጋዮቹ ያለ አቅማቸውን ከተጠቀሙበት በ3ጊላ ‹ዕውነትም መከሩ ብዙ ነው ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው» ሊሉ ይችላሉ።፡ «እግዚአብሔር እኛ ከፍጥረታችን አፈር እንደሆንን ያውቃል፡፡» (መዝ. 103፡14)GWAmh 155.3

    የመብል፣ የመጠጥ፣ የሥራና የማንኛውም ነገር መሻትን አለመግዛት አለ፡፡ በጥቂት ጊዜ ብዙ ነገር ለመሥራት የሚሹና ዕረፍት ሲያሻቸው የሚሠሩ ይከስራሉ አንጂ አያተርፉም፡፡ ለወደፊቱ የሚስፈልጋቸውን ኃይል ያባክናሉ፡፡ አሁን ያባከኑት ጉልበት በሚፈለግበት ጊዜ ቢሹት አያገኙትም፡፡ የክካል ኃይላቸው ይሸሻአዋል፣ የማስተዋል ችሎታቸውም ይዝላል፡፡GWAmh 155.4

    እያንዳንዱ ቀን ራሱ ግዳጅና ኃላፊነት ስላለው የዛሬው ስራ ወደነገው መሸጋሸግ የለበትም፡፡ እግዚአብሔር አስተዋይ፤ አዛኝ ስለሆነ የሚጠይቀው ጥያቄ የተመጠነ ነው፡ ጤናችንን የሚያጎሳቁል፣ አካላችንን የሚበድል፤ አእምሮአችን የሚያነሖልል ከባድ ሥራ አልጫነብንም፡፡ በጭካኔ ሥራውን ሁሉ አጠቃልሎ በግዴታ አያጋፍጠንም፡፡GWAmh 155.5

    የእግዚአብሔር ምርጥ ሠራተኞች «ዕረፍት ያሰፈልጋችኋል» የተባለውን ትዕዛዝ ማክበር አለባቸው፡፡ ብዙ ሰዎች ይህን ማስጠንቀቂያ ችላ ስላሉ ሕይወታቸው አልፏል፡፡ ሳይዘገዩ ዕረፍት እንደሚያሻቸው ተገንዝበውት ቢሆን ኖሮ ስራውን በውጭም ሆነ በአገር ውሰጥ ለማፋጠን ለመርዳት ከመካከላችን ሊገኙ የሚችሉ ብዙዎች ነበሩ፡፡ አንደ እነዚህ ያሉት ሠራተኞች የመከሩን ስፋት ከሠራተኞቹ ማነስ ጋር ያመዛዝኑና ከሚችሉት በላይ ለመሥራት ይሰለፋሉ፡፡ ተፈጥሮ እጥፍ ታሻሸንል ስትላቸው ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ሥራቸውን ዕጥፍ ያደረጉታል፡፡ ያን ጊዜ እግዚአብሔር ጻድቃንን የሚጠራው የኋለኛው መለከት አሰኪነፋ ድረስ በመቃብር እንዲያርፉ ይፈቅዳል፡፡GWAmh 156.1

    ሠራተኛ በሥራ ብዛት ምክንያት መንፈሱ ሲታወክ፤ ብርታቱ ሲዳከምና አእምሮው ለራሱ ደስታ ሳይሆን ሥራውን አንደገና በአዲስ ሃይል ለማካሄድ አንዲችል ማረፍ ይገባዋል፡-፡ ወጥመዱ አንዲይዝለት በመንገዳችን ላይ ሆኖ ጧት ማታ የሚያደባ ኃይለኛ ጠላት አለብን፡፡ አእምሮ ሲሰለች፣ አካል ሲጎሳቆል ያን ጊዜ ፈተናውን ያበዛብናል፡፡ ሠራተኛው ብርታቱን በጥንቃቄ ይንከባከብ፤ በሥራ ብዛት ሲደክም ከክርስቶሰ ጋር ይገናኝ፡፡GWAmh 156.2

    ይህን የምለው ከእከሌ ይልቅ እኔ ብዙ ሥራ ተጥሎብኛል እያሉ ለሚያጉረመርሥሙ አይደለም፡፡ የማይሠሩ አያስፈልጋቸውም፡፡ ጉልበታቸውን ቆጥበው የተሰጣቸውን የሥራ ክፍያ አጣጥመው የማይሠሩ ሞልተዋል፡፡ ስለ ከባድና አድካሚ ኃላፊነት ያወራሉ እንጂ ምን አንደሆነ አያውቁትም። የሥራቸው ውጤት አጥጋቢ አይደለም፡፡GWAmh 156.3

    ክርስቶስ የርህራሄ ማስጠንቀቂያውን የሰጠ ከልባቸው ሠርተው ለደከሙት እንጂ አንዲሁ ለሚያውደለድሉት አይደለም፡፡ ዛሬም ቢሆን ራሳቸውን ክደው፣ ችሎታቸውን ሳይቆጥቡ ለሚሠሩት፣ ከሥራ ብዛት የተነሣ ደክመው ሥራቸውን ለመቀጠል ላልቻሉት «ኑና እረፉ» ብሏል፡፡ ለእግዚአብሔር የሚሠሩ ሰዎች ከዓለም የተለየ ባሕርይ ማሳየት አለባቸው፡፡ ከዓለም ወግና ሥርዓት ተለይቶ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መራመድ የእያንዳንዱ ተግባር መሆን አለበት፡፡ በዚህ የጥድፍያና የሩጫ ዓለም ውስጥ እግዚአብሔር ፀጋውን ያሳረፈበት ሰው በሕይዎቱ ላይ ምልክት ይታያል፡፡ ዕውነተኛ ዕረፍት የሚገኘው በእግዚአብሔር ፍቅር ስር ነው፡፡ የሰው ሕይወት መልካም መዓዛ ይሆንና የመሰኮትን ፍቅር ይገልጣል፡፡GWAmh 156.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents