Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ትህትና በቤት ውስጥ

    ለኑሮ ጥቃቅን ነገሮች አለመጠንቀቅ አደጋ አለው፡፡ ወንጌላዊ በቤቱ ውስጥ በትህትናና በለዘበ አነጋገር መናገርን ችላ ማለት የለበትም፡፡ ወንጌላዊ ወንድሜ ሆይ፣ በቤትህ ውስጥ ፍጥጫና ግልምጫ፤ ትህትና የጎደለው ጠባይ ታሳይ ይሆን? እንዲህ ካደረግህ ምንም ያህል ከፍተኛ ሥራና ማዕረግ ቢኖርህም የእግዚአብሔርን ሕግ ሽረሃል፡፡ ምንም ዓይነት ደግነት ለሌሎች ብታሳይ በቤተሰብህ ውስጥ የክርስቶስን ፍቅር ካልገለጥህ ከተመደበልህ መንፈሣዊ ደረጃ አልደረስህም፡፡ ይህን የተቀደሰ ሥራ ተረክቦ በቁጣ፣ በብስጭት፣ ወይም በቀልድና በፌዝ የሚጨማለቅ ሰው የክርስቶስ ወኪል አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅር የለበትም፡፡ ልቡ ራስን በመውደድና፣ ራስን በማመጻደቅ የተሞላ ስለሆነ የሥራውን ቅዱስነት አልተገነዘበም፡- ክርስቶስ ከአርሱ ጋር ስለሌለ ለዘመኑ የሚጠቅም መልዕክት የለበትም፡፡GWAmh 128.3

    በአንዳንድ በኩል የወንጌላዊያን ልጆች በጣም ይጎዳሉ ምክንያቱም አባታቸው ከእነርሱ ጋር ስለማይሆን የፈለጉትን ጨዋታ ዓይነት ወይም ኑሮ ይመርጣሉ፡፡ ወንጌላዊው ወንዶች ልጆች ቢኖሩትም ፈጽሞ ሀሳቡን በአናታቸው ላይ : ለእናቲቱ ከምትችለው በላይ ከባድ ሸክም ይሆንባታል፡፡ የልጆቹ የቅርብ ወዳጅ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ከመጥፎ ጓደኝነት እርቆ ጠቃሚ ነገር እንዲሠሩ ይቆጣጠራቸው፡፡ እናትዮዋ ራሷን የመቆጣጠር ኃይሏ ዝቅተኛ ከሆነ አባትየው ሙሉ ኃላፊነት ወስዶ ልጆቹን መቆጣጠር አለበት፡፡ የልጆቹን ሕይወት ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ለማዋሃድ ታላቅ ጥረት ያድርግ፡፡GWAmh 129.1

    ልጆች ያሏት የወንጌላዊ ሚስት በቤቷ ውስጥ የወንጌል ሥራ መኖሩን ችላ አትበል፡፡ የሥራዋ ውጤት ዘለዓለማዊ እንደሚሆን ተገንዝባ ባላት ኃይል፤ በትጋትና በንቃት መሥራት ይገባታል፡፡ የልጆቿ ህይወት አንደ ሌላው ሕዝብ ሕይወት የከበሩ አይደሉምን? በፍቅር ትንከባከባቸው፡፡ የቤተሰብ ሃይማኖት ምን ያህል ጠቃሚ መሆኑን ለዓለም የማሳየት ኃላፊነት አንደተጣለባት ይግባት፡፡ በስሜት ሳይሆን በሕግና በሥርዓት መምራት አለባት፡፡ በሥራዋ እግዚአብሔር ብርቱ : መሆኑን አትዝንጋ:: ከሥራዋ በምንም ምክንያት ቢሆን መነቃነቅ የለባትም፡፡GWAmh 129.2

    ክክርስቶስ ጋር ግንኙነት ያላት አናት መምህርነት ጠቃሚነቱ አቻ የለውም፡፡ አገልጋይነቷ ቤትን ቤቴል (የእግዚአብሔር ቤት) ያደርገዋል፡፡ እግዚአብሔር ተራውን ውኃ የሰማይ ወይን በማድረግ ከእርሷ ጋር ይሠራል፡፡ ልጆቿ በዚህም በሚመጣው ዓለም ያስከብራታል፡፡GWAmh 129.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents