Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የወደፊቱ::

    የዚች ዓለም ታሪክ ሊታጠፍ በተቃረበበት ወቅት አንኖራለን፡፡ የመጨረሻውን የማስጠንቀቂያ መልዕክት የማዳረስ ታላቅ ተግባር ተደቅኖብናል፡፡ ከእርሻ፣ከወይን ቦታና ከሌሎችም የሥራ መስመር ተነስተው ወደዚህ ሥራ የሚሰማሩ ስዎች አሉ፡፡ ዓለም ሥነ ሥርዓት ጐድሏታል፡፡ ሁኔታውን ስንመለከት የወደፊቱ አስፈሪ ነው፡፡ ይህንኑ የዓለምን ደህንነት የሚያደፈርሱትን ሰዎች ክርስቶስ የተስፋው ወራሾች እንዲሆኑ ይጋብዛቸዋል፡፡ ለመማር ፈቃደኞች ከሆኑ በመንፈስ ቅዱስ ረዳትነት ተከታዮቹና ረዳቶቹ ያደርጋቸዋል፡፡GWAmh 22.1

    ብዙ ያልተሠራባቸው ማሳዎች ስላሱ አዳዲስ የወንጌል ገበሬዎች ያስፈልጉአቸዋል፡፡ ስለዓለም ያለው የክርስቶስ ብሩህ አስተያየት ለሠራተኞቹ መበረታቻ ነው፡፡ ትሁታን ከሆነ ከጊዜውና ከቦታው ጋር ገጣሚዎች ዕውነተኛ ሰዎች ይሆናሉ፡፡፡ ክርስቶስ ሰዎችን የሚያስፈራራውን ችግር ሁሉ ይመለከተዋል፡፡ ይህ ችግር ለብዙዎች የልብ ሸክም ይሆንና ተስፋ ያስቆርጣቸዋል፡፡GWAmh 22.2

    የራሳቸው ትክክለኛ ዘዴ ምንም ያህል ዋጋ የለውም፡፡ ከመሰላሉ አማካይ ላይ ሆነው ሰዎችን «ኑ እኛ ካለንበት ቦታ ድረሱ ይላሉ : ግን ምስኪኖቹ ጀማሪዎች እንዴት ወደዚያ አንደሚደርሱ አያውቁም፡፡GWAmh 22.3

    እርሱን ብቻ ተስፋ አድርገው ዘዴውን ከእርሱ ለመማር የሚፈልጉትን አገልጋዮች እግዚአብሔር በጣም ይወዳቸዋል፡፡ ብዙ አገልጋዮችን ተስፋ የሚያስቆርጡትን ሁኔታዎች አንዳሉ ይቀበላቸዋል፡፡GWAmh 22.4

    ያለብንን መጥፎ ስህተት : ሸክማቸው የከበደባቸውን እንዴት አንደምንቀርባቸው ያስተምረናል፡፡ ሠራተኞች አገለግሎታቸውን በደስታ የሚቀበሏቸው ሰዎች ሲያገኙ ይስ ይላቸዋል፡፡ በራሳቸው ያላቸውን ዕምነትና ትምክህት ችላ ብለው ክብርን ሁሉ ለአግኬአብሔር ይሰጣለ፡፡ ያላቸው ችሎታ እስከዚህም ባይሆን ልባቸው በፍቅርና በእርዳታ መንፈስ የተሞላ ነው:: ክርስቶስም የዘወትር ረዳታቸው ነው፡፡ ምህረትን በምህረትነቱ ከሚያምነበትና ለሥራው ሲሉ ሁሉንም ከሚተውት ጋር ክርስቶስ ይሠራል፡፡GWAmh 22.5

    የዓለም ብርሃን ዘወር ሲል መከራ የበረታ፤ሥነሥርዓት በምስቅልቅል የተተካ፣ ክንውንነት ቦታውን ለውድቀት የለቀቀ ይመስላል፡፡ አህቶችና ወንድሞች አገልግሎታችሁን ለሰዎች ማቅረቢያ ተጠቀሙበት የተጣሉትን አንሱ:፡ ችግርን በትዕግሥት፣ ፈተናን በጽሞና ተቀበሉ፡፡ ሥራችሁ በችግር ጊዜ ተስፋን የሚያበቅል ይሁን፡፡GWAmh 23.1

    ተራ ሰዎች ሠራተኖች ሊሆኑ ይችላሉ: ክርስቶስ ለሰብዓዊ ፍጥረት ሁሉ አንዳዘነ እነርሱም ለመሰሎቻቸው ሰዎች በማዘን ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር ሲሠራ በሃይማኖት ሊያዩ ይችላሉ፡፡ «ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧል የእግዚአብሔር ቀን ድምጽ ተርባል፡፡ አጅግም ፈጥኗል፡፡ ኃይሉም በዚያ በመራራ ልቅሶ ይሙሃል፡፡»GWAmh 23.2

    ለሠራተኞች በመሉ የምለው የሚከተለውን ነው በትሁት ልብ ወደፊት ግፉ፣ እግዚአብሔር አይለያችሁም፣ ግን በጸሎት ትጉ:: ይህ የሥራችሁ አቅድ ነው: ኃይሉ ግን የእግዚአብሔር ነው፡፡ የእርሱ ተባባሪዎች መሆናችሁን ስትረሱ በርሱ ታምናችሁ ሥሩ፡፡ ረዳታችሁ ነው፡፡ ብርታት የምታገኙ ከእርሱ ነው፡፡ ጥበባችሁ፣ ጽድቃችሁ፤ፍጽምናችሁ፣ መዳናችሁ እርሱ ነው:: ቀንበሩን ተሸከሙ፣ ትሁትና ገር መሆንን ተማሩ፡፡ አጽናኛችሁና ዕረፍታችሁ እርሱ ይሆናል፡፡ ዘፎንያ 1:14::GWAmh 23.3

    እግዚአብሔር የዓለምን ችግር ወርድና ቁመት ስሰሚያውቅ መፍትሄውም በአጁ ነው:: በሐዘን የተጨቆኑትን ምስኪን ነፍሳት ይመለከታል፡፡ ግን መውጫቸውንም ያውቃል፡፡ ሊደርሱበት የሚችሉበትን ደረጃም ያውቀዋል፡፡ ምንም አንኳን ሰዎች የተሰጣቸውን ምህረት ቢንቁም፣ መክሊታቸውን ቢያባክኑም፣የአምልኮት ክብራቸውን ዝቅ ቢያደርጉትም፣ ፈጣሪ በመዳናቸው ይከበራል፡፡GWAmh 23.4

    ክርስቶስ ለተከታዮቹ ከሚጠይቁት ወይም ከሚያስቡት የበለጠ ሊያደርግላቸው ይፈልጋል፡፡ ከክፋት ጋር የሚደረገውን ትግል በመንፈስ ቅዱስ መሣሪያነት የታጠቀው ዕውነት ያሸንፋል፡፡ ተከታዮቹ በክርስቶስ ደም ያጌጠውን የድል አርማ ያውለበልባሉ:: የደቀ-መዛሙርቱ ኑሮ እንደመሪያቸው አንደሚሆን ክርስቶስ ያውቃል፡፡ አሁን ባናውቀውም ድል በድል መጐናጸፋችን አንገነዘበዋለን፡፡ «በእኔ ሳላችሁ ሰላም የወንጌል አገልጋዮች እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኃለሁ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፡፡ ነገር ግን አይዞአችሁ እኔ ዓለምን አሸንፌአለሁ፡፡ »GWAmh 23.5

    ክርስቶስ አላቃተውም፤ ተስፋም አልቆረጠም፡፡ ተከታዮቹ አንደእርሱ መሆን አለባቸው፡፡ ታላቁ መሪአቸው ነውና አንደኖረ መኖር፣ እንደሠራ መሥራት አለባቸው፡፡ ድፍረት፣ ኃይል፤ አለመሰልቸት ሀብታቸው መሆን አለበት:: ብዙ እንቅፋት ቢያጋጥማቸውም በፀጋው ወደፊት መገሥገስ አለባቸው፡፡ በችግር ከመደናቀፍ ይልቅ ችግርን ማለፍ አለባቸው፡፡ ተስፋ ሳይቆርጡ ወደፊት መታገል ይገባቸዋል፡፡ በወርቃዊ የፍቅር ሰንሰለት ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ዙፋን ጋር አስተሳሥሮአቸዋል፡፡ በዓለም ታላቁ አነሳሽና ጸገቃቂ አኃይል አንዲሰጣቸው ፍላጐቱ ነው፡፡ ክፉን የመቋቋም ኃይል ይኖራቸዋል፡፡ ይህን ኃይል ሞት፣ገሃነም፣ሊያሸንፈው አይችልም፡፡ ክርስቶስ ድል እንደነሳ ይህ ኃይል እነርሱንም ድል ነሸዎች ያደርጋቸዋል፡፡ ዮሐንስ 16:33::GWAmh 24.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents