Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የወንጌላዊ ሚስት (ባለቤት)

    ወንጌላዊ ለሥራው አበል መክፈሉ መልካም ነው፡፡ ባለቤቱ ከቤት ወደቤት እየተዛወረች ሰዎችን ብትጎበኝ፤ ራሷን ለስራው ተባባሪ አድርጋ፤ ባትመረቅም መጽሐፍ ቅዱስን ለሰዎች ብታነብና ለሥራው ከልቧ የተሰለፈችበት ሆና ከታየች የወንጌላዊነት ተግባር ፈጸመች ማለት ነው፡፡ ታዲያ አገልግሎቷ እንዲሁ ይታለፍ?GWAmh 302.4

    አንደ ባሎቻቸው በርትተው በሚሠሩ፤ እግዚአብሔር የወንጌል አገልግሎታቸውን ባወቀላቸው ሴቶች ላይ ብዙ ጊዜ ግፍ ተፈጽሞባቸዋል፡፡ ለባሎቻቸው እየከፈሉ አኩል ለሚደክሙ-ት ሜስቶቻቸው አለመክፈል ከአግዚአብሔር ፈቃድ ውጭ ነው፤ ይህ ነገር ከቀጠለ ለሥራው የተነሳሱትን እህቶቻችን ተስፋ ያስቆርጣቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ቅን አምላክ ነው፤ ከባሎቻቸው ጎን ተሰልፈው ሰወንጌል መዳረስ የሚሰሩ እህቶቻችን ባይጠይቁ እንኳ ከባሎቻቸው ደሞዝ ተጨማሪ አበል ይሰጣቸው፡፡GWAmh 303.1

    ሰባተኛውን ቀን አክባሪ አድቬንቲስቶች ምንም ቢሆን የሴቶችን አገልግሉት ዝቅ አድርገው መመልክት የለባቸውም፡፡ አንዲት የቤት እመቤት የቤት ሥራዋንና የልጆቿን ጉዳይ ለታማኝ ረዳቶቿ ትታ በወንጌል ሥራ ከልቧ ብትሰለፍ ደመወዝ መከፈል እንደሚገባት መሥሪያ ቤቱ ይገንዘብ፡፡GWAmh 303.2

    እግዚአብሔር ለወንዶች ብቻ ሳይሆን ለሰሴቶችም የሥራ ቦታ አዘጋጀቲል፡፡ ገርነትን ከክርስቶስ ዘንድ ከተማሩ ለእግዚአብሔር መልካም ሥራ ሊፈጽሙ ይችላሉ፡፡ የየሱስን ስም መጥራት ብቻ ሳይሆን መንፈሱ ሊያድርባቸው ይገባል፡፡ ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ነፍሳቸውን በመከልከል እርሱ አንደተራመደ መራመድ ተገቢ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ የክርስቶስን ሙሉነት ለሰዎች በማስተዋወቅ ሌሎችን ሊጠቅሙ ይችላሉ፡፡GWAmh 303.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents