Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ስለ ፖለቲካ ሊኖረን የሚገባ ይዞታ

    ለትምህርት ቤቶቻችን መምህራንና ሥራ አስኪያጆች፡- በትምህርት ቤተቶቻችና በመሥሪያ ቤቶቻችን የሚሠሩ ኃላፊዎች ወጣቶችን ወደ አጉል መንገድ እንዳይመሩ ይጠንቀቁ፡፡ : ቅዱስን ለሚያምነበት የፖለቲካ ቡድን ወይም ለሚወዱት የነገር ልዩነት መደገፊያ የሚያደርጉ ሰዎች የሌሎችን አስተሳሰብ ይለያያለ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካይነት ይህን ልዩነት የሚያስተዋውቁ ሰዎች በቤተ ክርስቲያን መካከል መለያየት ይፈጥራሉ፡፡GWAmh 258.3

    እግዚአብሔር ወገኖቹን ስለ ፖለቲካ ያላቸጡን አስተሳሰብ አርግና አድርገው እንዲተው ይፈል.ጋቸዋል፡፡ በዚህ አቅጣጫ ከመናገር ዝምታ ይበልጣል፡፡ ክርስቶስ ሕዝቡን ንጹህ የወንጌልን መልዕክት በማዳረስ አንዲተባበሩ ይጠይቃቸዋል፡፡ የፓለቲካ ቡድኖትን ከአንዱ አንዱን በመምረጥ የድጋፍ ድምፅ ልንሰጥ አይገባንም፤ ምክንያቱም ከማን ማን እንደሚሻል አናውቅም፡፡ በማንኛውም የፓለቲካ መስክ ተካፋይ ሆነን ዕምነታችን ሳይናጋ ይኖራል ማለት ዘበት ነው። ሥልጣናቸውን የሃይማኖትን ነፃነት ለማጥፋት ለሚሠሩበተ የቤተ ክርስቲያን አባል ከመሆናችን በፊት የነበረብን የሀሳብ ደካማነት አያጥቃን፡፡ አሁን በክርስቶስ ሠራዊት ውስጥ ስለተመዘገብን ለክርስቶስ እንጂ ለጠላት መዋጋት የለብንም፡፡ እውነተኛ ክርስቲያናት የሆኑት የወይኑ ግንድ ቅርንጫፍ፡ ስለሆነ የዕውነተኛውን ግንድ ፍሬ ያፈራሉ፡፡GWAmh 258.4

    የክርስቶስን መለዮ ያጠልቃሉ አንጂ የፖለቲካ አርማ አይና'ራቸውም፡፡ ታዲያ ምን ልናደርግ ይገባናል የፖለቲካን ነገር ጣል እርግና: አድርገን እንተወው፡፡ «ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቀ ከአመጽ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ክፍል አለው? ክርስቶስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው?» (2ቆሮ. 6፡14፡15) የተጠቀሱት ክፍሉች ምን የጋራ ነገር አላቸው? ምንም ዓይነት ጓደኝነት ምንም ዓይነት ስምምነት የላቸውም፡፡GWAmh 259.1

    ጓደኝነት ማለት ተካፋይነት፣ ተባባሪነት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር በዓለም ክና:ሎችና በክርስቶስ ጽድቅ መካከል አንድነት አለመናሩን ለመግለዕ ጠንካራ ምሣሌዎችን ሰጥረቷል፡፡ በጨለማና በብርሃን፣ በጽድቅና በኃጢያት መካከል ምን አንድነት አለ? ምንም የለ፡፡ ብርሃን በጽድቅ ሲመሰል ጨለማ ደግሞ የኃጢዓተ ምሣሌ ነው፡፡ ክርስቲያኖች ከጨለማ ወጥተጡ ወደ ብርሃን መጥተዋል፡፡ ክርስቶስን ስለለበሱ የአውነተኝነትንና የታዛዝነትን አርማ አድርገዋል፡፡ ክርስቶስ በሕይወቱ በገለጠው በቅዱስና በከፍተኛ መመሪያ ይምመራሉ፡፡GWAmh 259.2

    በቤተክርስቲያን ወይም በትምህርት ቤታችን ውስጥ የሜያስተምሩ መምህራን የተለየ የፖለቲካ ዝንባሌ ካላቸው ያለምንም መዘግየት ሥራውን መተው ይገባቸዋል፡፡ ምክንያቱም አምላክ የሥራቸው ተባባሪ አይሆንም፡፡ የአሥራት ገንዘብ በፖለቲካ መስክ ለሚደክም ሰው ሊከፈል አይገባውም፡፡ ማንኛውም ሠራተኛ ዋና ዓላማው ነፍሳትን ለመመለስ ካልሆነ ሥራውን ይልቀቅ፡፡ ከመንገዱ ካልተመለሰ ትርፉ ጉዳት ብቻ ነው፡፡GWAmh 259.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents