Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ዕውነተኛነት (ልባዊነት)

    የክርስቶስ አገልጋዮች ሥራቸውን ከልብ የማከናወን ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ወጣት ደቀመዛሙርትን ቀስ በቀስ አየመሩ በብልዛሃት ወደ ላይ አዝልቀው፣ ወደፊት አራምደው ጠቃሚውን ሀሳብ ሁሉ ማስጨበጥ አለባቸው፡፡GWAmh 241.1

    ምንም መደበቀዋ የለባቸውም፡፡ ግን ደግሞ የሚታወቀው እውነት ሁሉ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ተዘርዝሮ ሊገለጥ አይቻልም፡፡ የራሱን ልብ በመንፈስ ሞልቶ መምህሩ ቀስ በቀስ በጥንቃቄ ለአዳማጮቹ መልዕክቱን በጊዜው ማሳተፍ አለበት፡፡GWAmh 241.2

    ወንጌላዊያን ያስተማራቸው ሰዎች እውነትን ከስህተት ለይተው በተመለሱ ጊዜ ሥራቸው ያበቃ ) አንዳይ!ዘነጉ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ሁለት አፍ እንዳለው ሰይፍ በሰውየው ልብ ቆርጦ ገብቶ ኃጢዓተኛውን ኃጢዓቱን ሲያስገነዝበው ሥራቸው ያለቀ የሚመስላቸው አሉ፣፤ ነገር ግን ተጀመረ አንጂ አላለቀም፡፡ እንዲህ ሲሆን ደህና አጀማመር ተጀመረ ማለት ነው፡፡ ግን በጸሎትና በትጋት ሥራው ካልቀጠለ ሰይጣን ያፈራርሰዋል፡፡ ሠራተኛች በፈጸሙት ተደስተው በመዝናናት አይረፉ፡፡ እውነት ጠለቅ ብሉ መከተል አለበት፤ ይህም ሊሆን የሚችል ዕውነትን ለመቀበል የሚታገሉት ሰዎች አስተሳሰባቸው በትክክል የተመራ እንደሆን ነው፡፡GWAmh 241.3

    አብዛኛውን ጊዜ ሥራው ተጀምሮ ስለሚቀር ውጤቱ ባዶ ይሆናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ በርከት ያሉ ሰዎች ካመኑ በ፲ጊላ ወንጌላዊው ዕቃውን ጠቀልሎ ወደ አዲስ ቦታ ይሄሄዳል፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ በቁ ምርምር ሳይደርግ ልቀቅ ተብሎ : ይህ ስህተት ነው፡ ሳይፈጽም ቢተወው ከጥቅ”መሙ ይልቅ ገጉዳቱ ያመዝናልና የደመረውን ሥራ ከፍጻሜ ያድርሰው፡፡GWAmh 241.4

    አረምን ሰማብዛት ያህል ብቻ ታርሶ እንደተተወ እርሳ አሳዛኝ የለም፡፡ እንዲህ ያልበቃ ትምህርት ተሰጥቷቸው የቀሩ ሰዎች ለሰይጣን ፈተናና ለሌላ ቤተ ክርስቲያናት አባሎች ነቀፋ ተጋልጠው ይቀራሉ፡፡ ብዙዎችም ሁለተኛ እንዳይገኙ ሆነው ይስሻሉ፡ ወንጌላዊ ሁልጌዜ ሥራውን ከልቡ የሚከታተል ካልሆነ በቀር ሰሥራው ጥንቱንም ባይሰለና፡ ይሳላል፡፡GWAmh 241.5

    አዲስ አማኞችን ሁል ጊዜ የማያቋርጥ ሥራና ጥናት እንደሚጠብቃቸው ማስገንዘብ ነው፡፡ ባስተማርነው እውነት የተመለሱ ሰዎች ብዙዎቹ ከዚያ ፊት የጠለቀ የመጽሐፍ ቅዱስ ፅጡቀት አይኖራቸውም፡፡ ምክንያቱም በአብዛኛዎቹ ቤተ. ክርስቲያናት የእግዚአብሔር ቃል በብዙው አይጠናም፡፡ ሕዝቡ የሚጠባበቁት ወንጌላዊው ተመራምሮ እንዲያስረዳቸው ብቻ ነው፡፡GWAmh 242.1

    ብዙዎቹ የእውነትን ሥራ መሠረት ለማግኘት ጠለቅ አድርገው ስለማይቆፍሩ ተቃውሞ ሲመጣባቸው ስጸመንን ያሉሱችን ዕምነት መደገፊያ ባሳ : አንዲያው አመንን አሱ አንጂ ቀድሞጡንም የዕውነትን ምንነት አላወቁትም ስለ ክርስቶስ በደንብ አንዲያውቁ ደረጃ በደረጃ አልተመሩም ኖራል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ መንፈሣዊነታቸው ለይምስል ስለሚሆን ሁል ጊዜ የሚሰሙት ቃል ሳይነገራቸው ሲቀር ጨርሶ ይሞታል። አማኛች ከልባቸው ካልተመለሱ፤ በሕይዎታቸው ፍጹም ለጡጥ ካልታየ ነፍሳቸው ከዘዘለዓለማዊው ቲጥኝ ጋር ካልተጣበቀ፤ ፈተናን ሊቋቋሙ አይሻሉም፡፡ ወንጌላዊው ሲል፣ የነገራቸው ሲረሳ «ታጥቦ ጭቃ» ይሆናሉ፡፡GWAmh 242.2

    የአግዚክብሔር ሥራ ባወጣ ያውጣህ ተብሎ በግዴለሽነት የሚሠራ አይደለም፡፡ አንድ ወንጌላዊ የተሰለፈበትን ሥራ አሳምሮ መሥራት አለበት፡፡ የመለሳቸው አማኞች ከእግዚአብሔር ሙሉ በረከት ተቀብለው ያመነትን አምነት በሥራ አስኪያውሉት ድረስ ወንጌላዊው ተሳካልኝ ብሉሱ አፎይ ሊል አይገባውም፡፡ ከበታቹ የነበሩትን በሚገባ ካስተማራቸው ትቷቸው ሲሄድ አምነታቸው፡፡ ለዘለዓለም አንዳይነቀል ሆና ተተክሏልና አይጠፋምGWAmh 242.3

    ወንጌላዊ ከቤተ ክርስቲያን ተናግሮ ሲወጣ አማኛቹን ያለረዳት ሊተዋቸው አልተፈቀደለትም፡፡ በሕዝቡ አእምሮ ውስጥ ያለውን ለማወቀ መሞከር አለበት፡፡ በትምህርቱ ስሜት ካደረባቸው ጋር መነጋገርና መጸለይ ይገባዋል፡፡- «ለክርስቶስ ና:ጹማን አድርጎ ለማቅረብ» (ቀላ.1፡28) በጥበብ ያስተምራቸው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አሰጣጡ የሰዎችን አንዲነካ ግልጽና ቀጥተኛ መሆን አለበት፡፡ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ እውቀታቸው ስላልገፉ ከኃጢዓት ደዌ የሚያላቅቅ ከሥራ ላይ የሚውል ጠቃሚ ትምህርት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡GWAmh 242.4

    አንድ ወንጌላዊ የማይመቸው የመሰለውን የሥራ ክፍል ተተኪው ወንጌላዊ ይፈጽሠዋል ብሎ መተው የሰበትም፡፡ እንዲህ ከሆነ ተከታዩ ወንጌላዊ የመጀመሪያው ወንጌላዊ ያላስተማረውን ሲያስተምር ከሕዝቡ መካከል «የፊትኛው ወንጌላዊ እንደዚህ አላለንም» በማለት ሊሸሹ ይችላሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ቅራታ ሊሰማቸው ይችላሉ፡፡GWAmh 243.1

    ጥቂቶች የአሥራት አከፋፈልን ደንብ አይቀበሉም፤ እውነቱን ከሚክተሉት ጋር አንድ ለመሆን አይፈልጉም፡፡ ሌላም ነገር ቢነገራቸው «እንዲህ አልተባልንም» ይሉና ችላ ይሉታል፡፡ የመጀመሪያው ወንጌላዊ የቤተ ክርስቲያኗን ዋና ዋና ትምህርቶች አውስቶላቸው ቢሆን ኖሮ እንዴት መልካም ነበር! እግዚአብሔር ስድሳ ሰዎች ለስሥ- (ለይምስል) ከሚያምኑ፣ ስድስተ ሰዎች ብቻ ከአውነት ከልባቸው ቢቀበሉት ይደሰታል፡፡GWAmh 243.2

    ወንጌላዊ አማኞቹን ሲያስተምር ለእግዚአብሔር ምስጋናቸውን ለመግለጥ አሥራት መክፈል እንደሚያስፈልጋቸው. ሳያሰገነዝብ አከይቅር፡፡ አዲሶቹ አማኛች የእግዚአብሔርን ለአግቢአብ/ቤኬር ሰመመለስ መዘጋጀት አለባቸው፡፡ አሥራትን መክፈል ችላ እንዳይባል ግልጽ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡ ሰለዚህ ዋና ጉዳይ ሳያስተምር የቀረ ወንጌላዊ የሥራውን አብዛኛ ክፍል ሳይስራ ተወው ማለት ነው፡፡GWAmh 243.3

    ወንጌላዊያን አማኞችን በእግዚቢአብሔር ሥራ ተካፋይነት ሊኖራቸው አንደሚገባ ማስተማርን አይርሱ፡፡ ሁሉም የፈቃደኝነት ሥራ ይጠብቀዋል፡፡ ማንኛውም የሥራ ክፍል ድጋፋቸውን እንደሚፈልግ አማኞቹ ይወቁት፡፡ ታላቅ የሚሲዮናዊነት ሥራ በፊታችን ስለተደቀነ ይህ ትምህርት መብራራት ይገባዋል፡፡ መንግሥተ ሰማያትን የሚወርሱ አድራጊዎች አንጂ ታቃሉን ሰሚዎች ብቻ አለመሆናቸውን ሕዝቡ ያስተውሉ፤ በሥራው ተካፋይ የሆነት ደግሞ ገንዘባቸውን ብቻ ሳይሆን ራሳቸውን ሳይቆጥቡ ለእግዚአብሔር መስጠት እንዳለባቸው አክይርሱ፡፡GWAmh 243.4

    አንዳንድ ወንጌላዊያን በቀላሉ ከሥራቸው ይወገዳሉ፣ ተስፋ ይቆርጣሉ ወይም የቤት ውስጥ ጣጣ ይበዛባቸዋል፡፡ በእነርሱ ቸልተኛነት ተነሳስቶ የነበረው የአዳማጮች ጉጉት ይጠፋል፡፡ በእንዲህ ያለ ግዴለሽነት የጎደለው ሥራ ከግምት በላይ ነው፡፡ አንድ የወንጌል ጥረት ሲጀመር ለሥራው ኃላፊነት የተጣለበት ወንጌላዊ የበኩሉን ድርጓ በማከናወን ታማኝነቱን መግለጥ ይገባዋል፡ ሥራው ውጤተ ቢስ ቢሆንበት ጉድለቱን ለማወቅ ከልቡ ይጸልይ፡፡GWAmh 244.1

    ራሱን በመመርመር ነዋሱን በትህትና ለጌታ ያስገዛ፡፡ የመሰኮትን ተስፋ በአምነት ይጨብጥ፡፡ ሥራውን በታማኝነት . እስኪታወቀው ድረስ በታማኝነተ ሥራውን ይቀጥል፡፡ የተፈለገውን ውጤት ለማግኘት ኃይሉን በሥራው ላይ ያውል፡፡GWAmh 244.2

    አንድ ሠራተኛ ራሱን የተቀደስ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ካላቀረበ ምንም ሥራው ቢያምር ተቀባይነት የለውም፡ ሥሩ ቅዱስ ካልሆነ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ ጤነኛ ና:ሬፊ አይገኝም፡፡ የዓለም ታላላቅ ሥራዎች፣ አስገራሚ ድርጊቶች፣ የሰዎች ዕቅዶችና ሀሳብ አንደሣር ሲጠፋ፤ «ጥበበኞች አንደሰማይ ጸዳል፤ ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘለዓለም ይደምቃሉ፡› (ዳንኤል 12፡3)GWAmh 244.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents