Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የአገር ውስጥ ቤተ ክርስቲያኖች ሊሰጡት የሚገባ ዕርዳታ

    በአገር ውስጥ ያሉ ቤተ ክርስቲያናት አባሎች በውጭ ላለው ሥራ ማሰብ ይገባቸዋል፡፡ አንድ አሜሪካዊ ነጋዴ ክርስቲያን ከስራ ባልደረባው ጋር ሲነጋገር እንዲህ አለ «በሥራዬ ሁሉ ጌታዬን ለማገልገል አእሞክራለሁ፤ አድል ባጋጠመኝ ቁጥር ሌሎችን ወደርሱ ለመመሰስ እሞክራለሁ፡፡ ቀኑን ሙሉ ለክርስቶስ አሠራለሁ፣ ሌሊት ስተኛ ደግሞ በቻይና አገር ለርሱ የሚሠራ ሰው አለኝ፡፡»GWAmh 312.4

    የብዙ ቤተ ክርስቲያን አባሎች በኀብረት ለምን አንደ ሚሲዮናዊ ቀጥረው ወደውጭ አይልኩም? ራሳቸውን ቢክዱ ይህን ማድረግ ይችላሉ፡፡ ወንድሞችና እህቶች ለዚህ ታላቅ ሥራ. እርዳታ አታበረክቱም? ለክርስቶስ የምታደርጉትን ሥራ አሁኑን እንድትፈጽሙት እአማጸናችኋለሁ፡፡ በገንዘባችሁ ወንጌላዊ አማካይነት የሚመለሱት ነፍሳት በክርስቶስ ዘውድ ላይ የሚያበሩ ክዋክብት ሊሆኑ ይችላሉ። ሥጦታችሁ ምንም ያህል ቢያንስ ለጌታ ለማቅረብ ቅር አይበላችሁ፡፡ በፍቅር ልብ ከተሰጠች ትንሷ ሥጦታ ሆና ትቆጠራለች፡፡ የሱስ ክርስቶስ ስለአሮጊቷ ስጦታ «ከሁሉ የበለጠ ሰጠች» ባለ ጊዜ አስተሳሰቧን ብቻ ሳይሆን የውጤቱንም ታላቅነት መናገሩ ነበር፡፡ «ሁለቱ ድሪሞች» አይሁዶች ከሰጡት ብዙ ገንዝብ ይልቅ የበለጠ ግምት ተሰጣቸው፡፡ ካነሳሱ ትንሽ ስጦታ ምሣሌነቷ ለዘመናት ሁሉ ተላልፏል፡፡ ራሷን ክዳ የሰጠችው ያሮጊቲ ስጦታ በልዩ ልዩ አገር በልዩ ልዩ ዘመን የነበሩትን ሰዎች አነሳስታለች፡፡ ከፍተኞችና ዝቅተኞች ሀብታሞችና ድሆች ወደ እግዚአብሔር ግምጃ ብዙ ገንዘብ እንዲያመጡ ረድታለች፡፡ መሥሪያ ቤቶችን ለማካሄድ፣ የተራቡትን ለመመገብ፤ ወንጌልን ለማዳረስ ምክንያት ሆናለች፡፡ ራስን ባለመውደድ በፈጸመችው ተግባር ብዙ ሰዎች ተባረኩ፡፡ እንደዚሁም በዚሁ መንፈስ የተሠራ ሥራ የተሰጠ ሥጦታ፣ እግዚአብሔርን ለማክበር ከተደረገ ሁሉን ከሚችለው ሀሳብ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ለመልካምነት ያለውን ውጤት ማንም ሊገምተው አይችልም፡፡GWAmh 313.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents