Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሕዝቦችን ለጋስ እንዲሆኑ ማስተማር

    በየቦታው የክርስቲያን ህብረቶችን የሚያቋቁም ሰው አዲሶቹን አማኞች እግዚአብሔር የሥራው ተካፋይ ሆነው ሥራውን እንዲደግፉ መፈለጉን ሳያስገነዝብ ማለፍ የለበትም፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እውነቱን የሚቀበሉ ሰዎች አምብዛም ሀብት የሌላቸው ናቸው፡፡ ነገር ግን ድህነታቸውን የተገለጠላቸውን ብርሃን ላለማዳረስ ምክንያት ማድረግ የለባቸውም፡፡ ድህነታቸው በሰማይ ሀብት ከመሰብሰብ ሲያግዳቸው አይገባም፡፡ ባለጸጎች የሚያገኙትን በረከት ድሆችም አኩል ሊቀበሉ ይችላሉ፡፡ ያላቸውን ጥቂቱን በታማኝነት ከሠሩበት በእምነታቸው መሥረት የሰማይ ሀብታቸው ይበዛላቸዋል፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባነት የሚያስገኝ የሥጦታው ብዛት ሳይሆን የአስጣጡ ስሜት ነወ፡፡GWAmh 140.2

    ሁሉም የሚችሉትን ያህል ለጌታ መሥራት መማር አለባቸው፡፡ የተጣለባቸውን ድርሻ ያህል ያከናውኑ:: ማንም ካገኘው ቢያንስም ቢበዛም ከአሥር አንዱን ለጌታ አንዲመልስ ይጠየቃል፡፡ ይህን ካላደረገ እንደሌባ ወይም እንደ ወንበዴ ከመቆጠሩም በላይ የአምላክን በረከት ይወርድልኛል ብሎ አይጠባበቅ፡፡ የቤተ ክርስቲያኗ አባሎች ድሆች ቢሆኑም ሥኑሥርዓቱ አይጓደል፡፡ እግዚአብሔር ምን ጊዜም ቢሆን ቃሉን አያፈርስም፡፡ የስጦታ ምንጩ አያልቅም፤ ፈቃዱን ሁሉ በረከቱን ያድላቸዋል፡፡GWAmh 140.3

    ካለው ከጥቂቱ በፈቃደኝነት የሰጠ ከተትረፈረፈው በግዴለሽነት ከለገሰው የበሰጠ በረከትን ይቀበላል፡፡GWAmh 140.4

    የተሰጣቸውን ችሎታ ከሥራ ላይ ያዋሉት በዚያው ልክ ችሎታቸው ሲዳብርላቸው፤ ያላቸውን አውቀት ከጥቅም ላይ ያላዋሉት ግን በዚያው ልክ ችሎታቸው ይቀነስባቸዋል፡፡ አንድ መክሊት ተቀብሎ ያችንም የቀበራት አገልጋይ በእግዚአብሔር ዘንድ ተኮንኗል፡፡GWAmh 140.5

    የእግዚአብሔር የአስራት ደንብ ቀላልና መድሎ የሌለበት ነው፡፡ የመለኮት ሥኑሥርዓት ስለሆነ የተከተለው ሁሉ ይጠቀማል፡፡ መምሪያው ቀላል ከመሆኑ የተነሳ ትፅዛዙን ለማሟላት ጥልቅ ትምህርት አያሻውም፡፡ የከበረውን የመዳን ሥራ ወደፊት ለማስገሥገሥ በዚህ የአሥራት ሥኑሥርዓት አማካኝነት ማንም ተካፋይ ሊሆን ይችላል፡፡ ሴት ወንድ፣ ጠጣት ሽማግሌ ሳይባል ሁሉም የእግዚአብሔር መዝገብ ቤት ሊሆን ይችላል፡፡ መዝገቡን ለመሳተም ወኪል ሊሆን ይችላል፡፡GWAmh 141.1

    በዚህ አቅድ ብዙ ታላላቅ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡ ሁሉም ታማኝ ቢሆን ሥራውን ወደፊት ለማራመድ ችግር ባልተገኘም ነበር፡፡GWAmh 141.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents