Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ያልተመጣጠነ ምግብ

    እንዲሁ በአልተመጣጠነ ምግብ ተልከፍክፋችሁ ለመኖር አትሞክሩ፡፡ ምን ዓይነት ምግብ አንደሚስማማችሁ ለራሳችሁ እወቁ፡፡ ከዚያም በላይ በሕሊናችሁ ዳኝነት ትክክለኛውን ምረጡ፡፡ በምግብ ጊዜ ማሰብና መብከንከን የለባችሁም፡፡ በችኮላ ሳይሆን በደስታ ለሰጣችሁ በረከት እግዚአብሔርን እያመሰገናቸሁ ተመገቡ፡፡ ወዲያው እንደበላቸሁ አእምሮአችሁን ለማሠራት አትሞክሩ፡፡ ቀላል የሰውነት እንቅስቃሴ በማድረግ ለሆድ ሥራውን የሚጀምርበት በቂ ጊዜ ስጡት፡፡GWAmh 153.3

    ይህ አስተሳሰብ ችላ ሲባል አይገባውም፡፡ የአመጋገብ ሁኔታችን ለማንኛውም የሥራ ዘርፍ ተስማሚ እንዲሆን ማጥናት ተገቢ ነው፡፡ የሥራ መሳካት በሠራተኛው ጤናና ይዞታ ይወሰናል፡፡ ብዙ ስብሰባዎች በተሰብሳቢዎቹ አባሎች ምክንያት ፍሬ ቢስ ሆነው ቀርተዋል፡፡ በወንጌላዊያኑ የምግብ አሰመዋሃድ የተነሣ ብዙ የወንጌል ጉባዔዎች ሳያምርባቸው ቀርተዋል፡፡ ጤና ከፍተኛ በረከት ነው፡፡ ብዙዎች አያውቁትም አንጂ ከፃይማኖትና ከሕሌና ጋር ዝምድና የአንድን ሰው ችሎታም ይወስናል፡፡ እያንዳንዱ ወንጌላዊ ታማኝ የመንጋዎች ጠባቂ ሆኖ ለመገኘት ሰውነቱን በተሟላ ጤና መጠበቅ አንዳለበት አይዘንጋ፡፡GWAmh 153.4

    ሠራተኞቻችን የጤናንና የሕይዎት ደንብ ዕውቀታቸውን ክሥራ ላይ ማዋል አለባቸው፡፡ በዚህ መስመር የተጻፉትን መልካም መጻሕፍት አንብቡ፡፡ ህሊናችሁ የሚነግራችሁን ሃይማኖታዊ መንገድ ተክተሉ፡፡GWAmh 154.1

    ስሰጤና አጠባበቅ በሚሰጠው ትምህርት ብዙዎች፣ ከሥጋ መጎሳቆል፣ ከመንፈስ መዋረድና ከአእምሮ ሙውደቅ እንደሚዳረጉ ጌታ አመልክቶኛል፡፡GWAmh 154.2

    ለጤና የሚረዱ ንግግሮች ይደረጋሉ፡፡ ብዙ ህትመቶች ይዳረሳሉ፡፡ የጤና ሕግና ደንብ ተቀባይነት ያገኛል፡፡ ብዙዎች ቀስ በቀስ ወደ እውነቱ ይጠጋሉ፡፡GWAmh 154.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents