Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ከሰማይ እርዳታ

    በውጭ አገር የሚሠራ ወንጌላዊ ለደህንነቱ ዋስተና የሆነውን የስማይ ዓና፡/ቅርንና ሰላምን በልቡ መያዝ አለበት፡፡ በችግርና በድንግርግር፣ በፍርሃትና በስቃይ ጊዜ አንደሰማፅት ቆራጥ፣ አንደአርበኛ ደፋር በመሆን፤ «አልደነግጥም አልፈራምም» አያለ የማይለቀውን እጅ ይጠማጠም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን በሚሜገባ አየተመራመረ አዘውትሮ መጸለይ አለበት፡፡ ለሰዎች ከመናገሩ በፊት ከላይ እርዳታ ቢጠይቅ የሰማይ መልዓክት ከርሱ ጋር ይሆናሉ፡፡ የሰዎች ጓደኝነት በሚያስፈልገው ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር በመገናኘት ሊደፋፈርና ለሊጽናና ይችላል፡፡ « እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሰዘለዓለም ከላንት ጋራ ነኝ» (ማቴ. 28፡20) በሚለው የጌታ ቃል ይጽናና፡ የመለኮት አብሮ መኖር ሲሰማው ነፍሳትን ለማዳን በቂ ዕውቀት ይኖረዋል፡፡GWAmh 314.5

    በሚሲዮናዊነት ሥራ ብርታትና መስዋዕትነት ያስፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር የመስቀሉን ድል ነሸነት የሚያውጁ፣ በችግር ጊዜ ተስፋ የማይቆርጡ የማይናጋ ጽነ ዕምነት ያላቸውን ሰዎች ይፈልጋል፡፡ ጠንክረው በመሥራትና በአሥራኤል አምላክ በመተማመን ቆራጥ ሰዎች አስገራሚ ሥራ ይሠራሉ፡፡ በግልጽ አስተሳሰብና በከፍተኛ ሙከራ የሚመራ ሥራ ውጤት ወሰን የለውም፡፡GWAmh 315.1

    እግዚአብሔር የሚቀበለው ሥራ በውጭ አገር በመፈጸሙ ደስ ይበለን፡፡ በውጭ ስለታየው የሥራ ውጤት እግዚአብሔርን አናመስጥግን፡፡ የማይሳሳተው የጦር መሪያችን አሁንም ቢሆን ‹«ግሩ፣ ወዳዳዲስ ቦታዎች : በየትም አገር የሥራውን ደረጃ ከፍ: አድርጉ» : ‹ብርሃንሸ መጥቷልና፣ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሽ አብሪ፡፡» (ኢሳ. 60፡1)GWAmh 315.2

    በእግዚአብሔር ሠራተኛች አማካይነተ ብራናው ለዓለም የሚገለጥበት ጊዜ አሰለ፡ የአንደኛው የሁለተኛውና የሦስተኛው መልአክ መልክቶች ሰዓለም ሁሉ፣ ለወገን፣ ለነገድ ለቋንቋና ለሕዝብ ሁሉ ይዳረሱ፡፡ ደሴቶች፣ በአህጉር ሁሉ ጨለማ ሳይ ያብሩ፡፡ ሥራው ሊዘገይ አይገባውም፡፡GWAmh 315.3

    መመሪያ ቃላችን «ምን ጊዜም ወደፊት» የሚል መሆን አለበት፡፡ መንገዳችን ለመጥረግ የሰማይ መላዕክት በፊት ፊታችን ይሄዳሉ፡ ዓለም ሁሉ ብርሃን አስኪበራለት ድረስ ለሩቅ ቦታዎች ያለን ኃላፊነት ከትከሻችን አይወርድም፡፡GWAmh 315.4