Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ጊዜ አጠቃቀምን ማሳሳል

    ወንጌላዊያን ለጥናት፣ ለጸሎት ጊዜ መወሰን አለባቸው፡፡ ጥቅሶችን በቃል በማጥናት፣ የትንቢትን ዓ:ጻጳሜዎች በማሰላሰል፣ ክርስቶስን ለደቀመዘሙርቱ ያስተማረውን ትምህርት በማጥናት አእምሮአቸውን በዕውቀት ማበልጸግ አለባቸው፡፡ በአውቶቡስ ስትጓዙ ወይም በባቡር ጣቢያ ስትጠብቁ የምትመለክቱት መጽሐፍ ያኩ፡፡ ትርፍ ጊዜአችሁን ሁሉ መልካም ለመሥራት ተጠቀመብት፡፡ በዚህ መንገድ የፈተና በሮች ሁሉ ይዘጋሉ፡፡GWAmh 179.2

    ብዙዎች ሊሳካላቸው ውድቀት ደርሶባቸዋል፡፡ የሥራውን ከባድነት ስላልተገነዘቡት ነፍሳትን ለመመለስ በሽህ የሚቆጠሩ ዓመታት ያሏቸው አስመስለው በግዴለሽነተ ይማግጣሉ፡፡ የእግዚአብሔር ሥራ የሚፈልገው ተራ ሰባኪዎች ሳይሆን ከልብ የሚሠሩ ትጉና የማይታክቱ ሠራተኞችን ነው፡፡ የሰዎችን የአእምሮ ችሎታ ሊገምት የሚችል እግዚአብሔር ብቻ ነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ሰዎች አእምሮአቸውን በዕውቀት አንዲያበለጽጉ አንጂ በድንቁርና ተቀብረው አንዲቀሩ አልነበረም፡፡GWAmh 179.3

    እያንዳንዱ በዕውቀት የማደግ ኃላፊነት አንዳለበት ይወቅ፡፡ ቢሆንም በዕውቀቱ ከመኩራተትና ከመንጠባረር ይልቅ ለዕውቀት ተጣጥሮ ባገኘው ጥበብ እግዚአብሔርን በማስከበሩ ሊደሰት የገባዋል፡፡ ከዕውቀትና ከጥበብ ምንጭ ክቡር ዕውቀት ሊገበዩ ይችላሉ፡፡GWAmh 179.4

    የክርስቶስ ደቀመዝሙር የሆነ ሰው አእምሮው ሳይሰለች ቨለዓለም ዕውቀትን ይገበያል፡፡ ከዕውነት ወደዕውነት እየተሸጋገረ የተፈጥሮን ሕግ ሲመራመር አስገራሚውን የእግዚአብሔር ፍቅር በበለጠ ያያል፡፡ በዕውቀት ዓይን የክርስቶስን የማይመረመር ፍጽምና፣ ዕውቀትና ጥበብ ይመለከታል፡፡ አእምሮው ሲሰፋ አውቀቱ ሲይዳበር ሕይዎቱ በበርሃን ይመራል፡፡ ከሕይወት ውኃ ምንጭ በብዛት እንደጠጣ መጠን ስለ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊነት ያለሰው አስተሳሰብ በደስታ ይበራለታል፤ የእግዚአበሔርን ጥልቅ ሀሳብ ለማወቅ ያለው ጉጉትም ይጨምራል፡፡GWAmh 180.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents