Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከክርስቶስ ጋር አንድነት

    ከዋናው ጠባቂ ከክርስቶስ ጋር የተባበረ ዝቅተኛ ጠባቂ ክርስቶስን በቀላሉ ለሰዎች ሊያስተዋውቅ ይችላል፡፡ የዕምነታችን መሠረተ-ትምህርትን ጠንቅቆ ማወቅ ተገቢ ነው፡፡GWAmh 87.1

    ከዚህ የበለጠ ጠቃሚ ነገር ወንጌላዊው በሚያስተምረው ትምህርቱ ራሱ የተጠቀመብት እንዲሆን ነው:: ከክርስቶስ ጋር አንድነት ያለው ወንጌላዊ ለእግዚአብሔር ማገልገል የበለጠ ምኞትና ችሎታ ይኖረዋል፡፡ ዕውቀቱ ይጠልቃል፡፡ ምክንያቱም በፀጋ ማደግ ማለት ቃለ-እግዚአብሔርን በበለጠ ማስተዋል ማለት ነው፡፡ በጌታው እጅ ያለ መሣሪያ መሆኑን ያምንበታል፡፡ ካልተፈተነ በቀር ጉድለቱን ሊያውቅ ስለማይችል ፈተና ይደቀንበታል፡፡ ቢሆንም ጌታን በፍጹም ልቡ ከተማጸነ ፈተናው ሁሉ ያልፋል፡፡GWAmh 87.2

    አንዳንድ ጊዜ ይወድቅ ይሆናል፡፡ ውድቀቱ ግን ምክንያትና በጌታው ላይ የበለጠ እምነት አንዲኖረው መገፋፊያ ይሆናል፡፡ ቢሳሳትም ስህተቱን ላለመድገም ይጥራል፡፡ ፈተናን ለመቋቋም የበሰጠ ብርታት ይኖረዋል፣ ሌሎችም በአራአያነቱ ይጠቀማሉ፡፡GWAmh 87.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents