Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለ. መንፈሣዊያን ዘበኞች

    የክርስቶስ አገልጋዮች በኋላፊነታቸው ስር ላሉ ሰዎች ጠባቂዎች ናቸው፡፡ ሞያቸው ከዘበኛ ሥራ ጋር ይመሳሰላል፡፡ በድሮ ጊዜ በግንብ ላይ ሆነው የሚጠባበቁ የከተማ ዘበኞች ነበሩ፡፡ ከሩቅ ተመልክተው ጠላት ሲመጣ ያዩ አንደሆን ማስጠንቀቂያ ይሰጣሉ፡፡ የከተማዋ ደህንነት የእነርሱን ታማኝነት ይመለከታል፡፡ በየጊዜው በመጣራት ነቅተው መጠበቃቸውን እርስ በርሳቸው ያረጋግጣሉ፡፡ የደህንነትም ቢሆን ወይም የአደጋ ጩከት አንዱ ሲያሰማ ሌላው እየተቀበለ ከተማውን ያስተጋባል፡፡ ለእያንዳንዱ አገልጋይ እግዚአብሔር እንዲህ ይለዋል፡፡GWAmh 9.1

    «አንተም የሰው ልጅ ሆይ ለአሥራኤል ቤት ዘበኛ አድርጌሃለሁ፣፤ ከአፌ ቃሌን ስማ ከእኔም ዘንድ አስጠንቅቃቸው:: ኃጢዓተኛውን ኃጢዓተኛ ሆይ በአርግጥ ትሞታለህ ባልሁ ጊዜ ኃጢዓተኛውን ከመንገዱ ታስጠነቅቅ ዘንድ ባትናገር ያ ኃጢዓተኛ በኃጢዓቱ ይሞታል ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ፡፡ ነገር ግን ከመንገዱ ይመለስ ዘንድ ኃጢዓተኛውን ብታስጠነቅቀው እርሱ ከመንገዱ ባይመለስ እርሱ በኃጢዓቱ ይሞታል፡፡ አንተ ግን ነፍስህን አድነሃል፡፡»GWAmh 9.2

    ይህ ከባድ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ለቤተ-ክርስቲያን ጠባቂዎችና ለእግዚአብሔር ምሥጢር መጋቢዎች ነው፡፡- ጠላት ሲቃረብ ሕዝቡን ለማስጠንቀቅ በጽዮን አምባ ላይ መቆም አለባቸው፡፡ በአንዳንድ ምክኒያቶች መንፈሣዊ እንቅልፍ ቢጥላቸውና ሕዝቡ አስጠንቃቂ በማጣት አደጋ ላይ ቢወድቅ ደሙ ከአጃቸው ይፈለጋል፡፡GWAmh 9.3

    ጠባቂው ከአምላክ እየተቀበለ ለሕዝቡ ማስጠንቀቂያ ለመስጠት መብትና ግዴታ አለበት፡፡ የእግዚአብሔር ምርጥ ሰዎች በክርስቶስ ደም ሲቀደሱ ዋናው ኃላፊነታቸው ይህ ነው፡፡ 1ኛ ሕዝቅኤል 33፡7-9GWAmh 9.4

    ለሕዝቡ የሕግ ተላላፊነትን መጥፎ ውጤት ማስታወቅ፣ የቤተክርስቲያኗን ፍላጐት ማሟላት አለባቸው፡፡ ምን ጊዜም ቢሆን ኃላፊነታቸውን ችላ ማለት አይገባቸውም፡፡ ሥራቸው ያላቸውን ችሎታ አንዲጠቀሙበት ያስገድዳቸዋል፡፡ ንግግራቸውና መምሪያቸው እርግጠኛነት ያለበት አንጅ በጥርጥር መውጅ የሚወዛወዝ መሆን የለበትም፡፡ ለአበል ወይም ለደመዎዝ ብቻ ብለው ሳይሆን ሥራውን ባይሠሩ ተጠያቂዎች መሆናቸው ተሰምቷቸው መሥራት አለባቸው፡፡GWAmh 9.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents