Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለአገልግሎት አስፈላጊ ነገሮች መተዛዘን

    እግዚአብሔር ሠራተኞቹን በመተዛዘንና በፍቅር አንዲተሣሠሩ ይፈልጋል፡፡ ሕይወቱን የክርስቶስ ፍቅር የከበበለት ክርስቲያንና ለሕይወት መዓዛ ለመሆን የሚችልን አማኝ፤ ክርስቶስ ጥረቱን ይቀበልለታል፡፡ ክርስትና ሰዎችን እርስ በርሳቸው ያቀራርባል እንጂ በመካከላቸዉ ገደብ አያበጅም፡፡GWAmh 85.2

    እግዚአብሔር ፍጥረትን ሁሉ እንዴት በምህረት ዓይን አንደሚመለከተው ተመልከት (አስተውል)፡፡ የተሳሳተውን ልጁን ይወደዋል፣ እንዲመለስም ይጠባበቀዋል፡፡ አባት የበደለውን ልጁን ያቅፈዋል፡፡ አባቱ የልጁን ድሪቶ (ጨርቅ) ከልጁ አካል ላይ አወልቆ የራሱን ልብስ ያጐናጽፈዋል፡፡ ለንጉሣዊ ቤተሰብነት ምልክት ቀለበት በጣቱ ያጠልቅለታል፡፡ ግን የጠፋውን ልጅ ስንቶች ናቸው በንቀትች ዓይን የሚመለከቱት! አንደፈሪሣዊው «አምላክ ሆይ ተመስገን እንደዚህ ቀራጭ አይደለሁምና” የሚሉ ስንቶች ናቸው፡፡GWAmh 85.3

    አንዳንዶች ከእግዚአብሔር ጋር እንሠራለን ብለው የተሠለፉ ሰዎች አንደፈሪሣዊው፣ ከፈተና ማዕበል ለመውጣት የሚጥረውን ኃጥዕ ከሩቅ ቆመው በግዴለሸነት ይመለክቱታል፡፡GWAmh 86.1

    ክርስቶስ ለነፍሳት እንደሚያዝነው ለወደቁ ወንድሞች ባለመቸገራችን ከእርሱ በጣም እንርቃለን፡፡ ሰውን በሰብዓዊ ደረጃ አለመመልከት ከኃጢዓት ሁሉ የበለጠ ኃጢዓት ነው፡፡ ክርስቶስ ያሳየውን ገርነትና ፍቅር ለሰዎች ሳይገልጡ የእግዚአብሔርን ቅንነት አሳየን ብለው የሚያስቡ አሉ:: ጨካኞችና ፊታቸውን አጥቁረው ሌሎችን የሚመለከቱ ክበድ ያለ ፈተና አለባቸው፡፡ ሰይጣን እንደነዚህ ያሉትን ሰዎች ስለሚታገል የጥላቻና ርህራሄ የጐደላቸው ቃላት ከፈታኙ ኃይል ስር ይጥሉአቸዋል፡፡GWAmh 86.2

    ደግነታችን ጻድቃን መስለው ለሚታዩን ብቻ ሳይሆን እንደ ክርስቶስ ለምስኪኖች፣ ለችግረኞች፣ በትግል ላይ ላሉ ሰዎች፣ በየጊዜው ለሚሳሳቱ፤ ኃጢዓት እየሠሩ ለሚናዘዙ፣ ለተፈተኑና ተስፋ ለቆረጡት ጭምር ማሳየት አለብን፡፡ እንደ ሩህሩሁ ሊቀ-ካህናታችን ለተቸገሩ ነፍሳት የምናስብ መሆን አለብን፡፡GWAmh 86.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents