Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የመዳኛ መንገዶች (መድኃኒቶች)

    በጸሎት ለመፈወስ የሚፈልጉ ሰዎች ራሳቸው ለማድረግ የሚችሉትን ለመዳን የሚረዳቸውን ነገር ሁሉ መሞከር አለባቸው፡፡ በተፈጥሮ ሕመምንና ስቃይን የሚያስታግሱ ጤናን የሚያስገኙ መድኃኒቶችን መጠቀም የዕምነት ጉድለት አይደለም፡፡ የኑሮን ሕግ ተገንዝበን እንድንሠራበት እግዚአብሔር ኃይል ሰጥቶናል፡፡ የተፈጥሮን ሕግ ሳንቃወም የተሰጠንን ሁሉ ለጤናችን ደህንነት ልናውለው እንችላለን፡፡ በሽተኞች እንዲፈወሱ በምንጸልይበት ጊዜ የቻልነውን ያህል በመርዳት የእግዚብሔር የመዳን ሥራ ተካፋይ በመሆናችን አያመሰገንን መሥራት : ግን ይህን ዕርዳታ ስናደርግ ከፈቃዱ ውጭ ማለት የለብንም፡፡GWAmh 139.1

    መድኃኒት ለመጠቀም የእግዚአብሔር ቃል ፈቃድ አለው፡፡ የእሥራኤል ንጉሥ ሕዝቅያስ ታሞ ሳለ የእግዚአብሔር ነብይ ትሞታለህ የሚል መልዕክት መጣ፡፡ ንጉሥ በእግዚአብሔር ፊት ስላለቀሰ አሥራ አምስት ዓመት የዕድሜ ጭማሪ ይሰጥሃል የሚል የምሥራች ከእግዚአብሔር መጣለት፡፡ ይህን ንጉሥ ለማዳን አንዲት የአግዚአብኤር ቃል ትበቃ ነበር ነገር ግን ልዩ መምሪያ ከእግዚአብሔር ዘንድ መጣለት፡፡ «የበለስ ጥፍ ጥፍ አምጥተው በአባጩ ላይ ይለበጡት እርሱም ይፈወሳል፡፡” (ኢሳ. 38:21) አንድ ጊዜ ክርስቶስ ዓይኑሥውሩን በጭቃ ቀብቶ «ሂድና በሰሊሆም መጥመቂያ ታጠብ ታይምአለህ ሄዶ ታጥቦ ሲመለስ አዬ፡፡ የእውሩ ዓይን በክርስቶስ የፈዋሽነት ኃይል ብቻ ሊድን በቻለ ነበር፡፡- ግን ክርስቶስ የተፈጥሮን መድኃኒት እንድንጠቀምበት ሲያስተምረን ነው፡፡ በሽታችን በ «መድሐኒት» አማካኝነት እንድንረሣ አልፈቀደልንም ነገር ግን ቀላል የተፈጥሮ መድኃኒት መፍቀዱን ከላይ የተዘረዘሩት ማስረጃዎች ያመለክታሉ፡፡GWAmh 139.2

    ለህመምተኛ ጸልየን ምንም ዓይነት ውጤት ባናገኝ በእግዚአብሔር ላይ ያለን አምነት አይዳከም:: መራራ ጽዋ ቢደርስብን ጌታ የመረረውን ማጣፈጥ አንደሚችል አንዘንጋ፡፡ ነገር ግን ከበሽታ ብንድን አዲስ ባገኘነው ኃይል ለጌታችን አዲስ ግዳጅ መፈጸም አንዳለብን አንዘንጋ፡፡ አስር ለምፃሞች ተፈውሰው የሱስን ለማክበርና ለማመስገን ከአሥሩ የተመለሰው አንድ ብቻ ነው፡፡GWAmh 139.3

    ልባቸው በክርስቶስ ምህረት እንዳልተነካው አንደ ዘጠኙ የማናመሰግን አንሁን፡፡ «በጎ ሥጦታ ሁሉ ፍጽም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፡፡ መለወጥም ክእርሱ ዘንድ በመዞርም የተደረገ ጥላ ከእርሱ ዘንድ ከሌላ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ::” (ያዕ. 1፡17)GWAmh 140.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents