Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 7—ለወንጌል ሥራ የሚረዱ ነገሮች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

    ነፍሳትን ለማዳን ከልብ ለመሥራት የሚፈልጉ ወንጌላዊያን ቅዱስ ተመራማሪዎችና ፀሎት አዘውታሪዎች መሆን አለባቸው፡፡- ራሳቸው አንደሚገባ ሳያጠኑ ቃለ-እግዚአብሔርን ማስተማር የሚሞክሩ አንደ ኃጥያት ይቆጠርባቸዋል፡፡ የሚያስተምሩትን እውነት ክብር ከተገነዘቡ በሚገባ ሊዘጋጁ ይገባል፡፡ መግለጫቸው የሚስተዋልና ብርቱ መሆን አለበት፡፡ በምድር ገጽ ከሚገኙት ሰዎች ሁሉ ወንጌላዊያን የሆነ ቃለ-እግዚአብሔርን በበለጠ አውቀው ከሃይማኖታቸው ጋር ማሰተባበር አለባቸው፡፡ የሕይወትን ቃል ጠንቅቆ የማያውቅ ሰው ሰዎችን ወደ ሰማያዊ ቤት ሊያመላክት አይችልም፡፡GWAmh 158.1

    መጽሐፍ ቅዱስ የአምነታችን መሠረተ-ትምህርት ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ቃል የበለጠ ለአእምሮ ስፋትን፣ ለማስተዋል ጥልቀትን፤ ለአካል ብርታትን የሜሰጥ ምንም ነገር የለም፡፡ ሰዎች ቃለ-እግዚአብሔርን በሚገባ ቢከታተሉ ኖሮ ዛሬ በብዙ ሰምች ዘንድ የማይታዩትን የጠባይ ጨዋነት፤ የአእምሮ ማስተዋልን እና የሀሳብ ጽናትን ባገኙ ነበር፡፡GWAmh 158.2

    ብዙ ወንጌላዊያን መጽሐፍ ቅዱስን በሚገባ ስለማያጠኑ የሚፈለገው የዕውቀት ደረጃና የጠባይ አድገት የላቸውም፡፡ ያላቸው የላይ ላይ ዕውቀት በቂ ይመስላቸውና የተደበቀውን መዝገብ በመቆፈር ፈንታ ጊዜያቸውን እንዲሁ ያባክናሉ፡፡ ባለ መዝሙሩ ‹አንተን አንዳልበድል ቃልህን በልቤ ሠወርሁ» (መዝሙር 119፡11) ይላል፡፡ ጳውሎስም ለጢሞቴዎስ ሲጽፍ «መጽሐፍ ሁሉ በእግዚአብሔር መንፈስ ተጻፈች ለማሰተማር፤ ለተግሣፅ፣ ለምክር፣ በጽድቅም ለመምራት ትጠቀማለች፣ እግዚአብሔር ሰው መልካምን ለመሥራት ፍጽም ይሆን ዘንድ» : (2ኛ ጢሞ. 3፡16-17)GWAmh 158.3

    የእግዚአብሔር የሕይወት ሰጭነቱ ኃይል በቃሉ ውስጥ ነው፡፡ ክርስቶስ ሕሙማንን የፈወሰ አጋንንትን ያሰወጣ በቃሉ ነው፡፡ በቃሉ የባሕርን ሞገድ ጸጥ አሰኘ፡፡ ሙታንንም አስነሳ፡፡ ሕዝቡም ቃሉ ኃይል እንዳለው መሰከሩ፡፡ ለብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች የተናገረውን ያንኑ የእግዚአብሔር ቃል ተናገረ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በሙሉ ስለክርሰቶስ ያስተምራል፡፡ ብርታታችንም እርሱ ነው፡፡GWAmh 159.1

    ይህ ቃል ሥራን አይከለክልም፤ ይልቅስ ሥራን ያደፋፍራል፡፡ ሰዎችን በጥርጣሬ ላይ አይተዋቸውም፡፡ በበለጠ ወደ ክርስቶስ አቅርቦ ዋና ሥራቸው ነፍሳትን መመለስ መሆኑን ያስገነዝባቸዋል፡፡ ወደ ሰማይ ቤት እየመራ የሚያደርስ መብራት በአጃችን አለ : ከግምት በላይ ስለሆን የዘለዓለም ሀብት ይናገራል፡፡GWAmh 159.2

    የእግዚአብሔር ቃል የጠባይ መለኪያ ነው፡፡ እግዚአብሔር በቃሉ አማካይነት ለደህንነት የሚበጅን እውነት አስረክቦናል፡፡ ከዚህ የሕይዎት ምንጭ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ሰዎች ቢቀዱለትም፤ ምንጩ፤ ፈጽሞ አያቋርጥም፡፡ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ በቃሉ አማካኝነት እግዚአብሔርን ተመልክተው የእርሱን ዱካ ተከትለዋል፣ እርሱንም መስለዋል፡፡ ነገር ግን ይህ ሁሉ ምርምር ይህን ታላቅ እውነት አላዳከመውም፡፡ ሌሎች በብዙ ሸህ የሚቆጠሩ ምርምሩን ለመቀጠል ተሰልፈዋል፡፡GWAmh 159.3

    ሠራተኛው የክርሰቶስን የሕይወት ታሪክ መመራመር እንደቀጠለ መጠን የበለጠ አስደሳች ትምህርት እየተገነዘበ ያድራል፡፡ ትምህርቱ ፈጽሞ አያቋርጥም፡፡GWAmh 159.4

    ስለ አንደኛው መልአክና ስለ ሁለተኛው መልአክ መልዕክቶች አንናገራለን፡፡ ስለ ሦስተኛው መልአክ መልዕክትም የምናውቀው መስሎ ይሰማናል፡፡ ነገር ግን በትንሸ እውቀታችን ተወስነን ዝም ካልን የበለጠ የአውነት ብርሃን አይገለጥልንም፡፡ የሕይወትን ቃል ለማግኘት የሚፈልግ ሁል ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን መመርመር አለበት፡፡ ይህን ችላ ካለ የተራቡትን ነፍሳት ሊመግብ አይችልም፡፡ ትጉህ፤ ስለ እውነት ለመረዳት በጸሎት ተጠምዶ እውነተኛውን ዕውቀት ከየሱስ የሚሻ ትሁት ተመራማሪ እና ከፍተኛ ዋጋ ይጠብቀዋል፡፡ ለማብራሪያነት የሚጠቀመው የሰዎችን ጽሑፍ ሳይሆን የሕይወትንና የእውነትን ምንጭ ነው፡፡ በቅዱስ ማስተዋል መሪነት እውነቱ ይገለጥለታል፡፡GWAmh 159.5

    እውነት ለሰዎች የሚገለጠው ‹በመንፈሴ ነው እንጂ» በሰብዓዊ ኃይልና ብርታት አይደለም» (1ካ. 4፡6) ይላል እግዚአብሔር፡፡ ሥራውን እንድናደንቅለት የሚያደርገው የተናጋሪው ጠባይ ወይም የንግግሩ ማማር አይደለም፡፡ ጳውሎስ ተክለ፤ ጳውሎስ አጠጣ፤ አንዲያፈራ የሚያደርገው ግን እግዚአብሔር ነው፡፡ ጥረቱን የሚያሳካለት የወንጌላዊው የመጽሐፍ ቅዱስ አውቀትና ፈቃዱን ለመለኮታዊ ፈቃድ ማስገዛቱ ነው፡፡GWAmh 160.1

    የእግዚአብሔርን ቃል የሚቀበል ልብ አንደሚበተን ዕቋሪ ወይም የሚያፈስ አንስራ መሆን የለበትም፡፡ ከተራራ ሥር አንደሚፈለፈልና አግረ መንገዱን የተጠማውን እያረካ፤ የጠወለገውን እያለመለመ እንደሚያልፍ ምንጭ መሆን አለበት፡፡GWAmh 160.2

    መጽሐፍ ቅዱስን በሚገባ ያወቀ ሰው የክርስቶሰ ወኪል የመሆን ማዕረግ ይሰጠዋል፡፡GWAmh 160.3

    የመድኃኒታችን የመምህርነት መንፈስ ለትምህርቱ ግልጽነትን ለጸሉቱ ተደማጭነትን ይሰጠዋል፡፡ ምስክርነቱ ቀላልና የማይስተዋል አይሆንም፡ ሁል ጊዜ አንድ ዓይነት ትምህርት አያቀርብም፡፡ ምክንያቱም በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት አእምሮው እየሰፋ አዲስ ሀሳብ ይፈልቅለታል፡፡ ክርስቶሰ እንዲህ :GWAmh 160.4

    «ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይዎት አለው፡፡ ሕያው አብ አንደላክኝ እኔም ከአብ የተነሣ ሕያው እንደሆንሁ፤ እንዲሁም የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል፡፡ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይዎትም ነው፡፡› ዮሐ. 6፡54፤ 57፣ 63GWAmh 160.5

    የእግዚአብሔር አገልጋዮች ይህን ምሥጢር ሲያስተውሉ የዘለዓለም ሕይዎት ዓላማ በአገልግሎታቸው ውሰጥ ይገኛል፡፡ የተለምዶ ትርጉም የለሸ ስብከት ያቆማል፡፡ የወንጌል መሠረት በአዲስ መንፈስ ይታነፃል ለሁሉ የሚስተዋል የእውነት አገላለጽ ይገኛል፡፡ በዚህ አገልገሎት ለመጠመድ መብት ያገኙ ሰዎች መንፈስ ቅዱስን ከተጠማጠሙ የሚያነቃቃ ኃይል ይቀበላሉ፡፡ የእግዚአብሔር የፍቅር ዕሳት በልቦናቸው ውስጥ ይቀጣጠላል፡፡ መላ ሰውነታቸው የእግዚአብሔርን ቃል ክብርና ሞገስ ለመግለጥ ይነቃቃል፡፡GWAmh 161.1

    ቃለ-እግዚአብሔርን ከክንዱ የማይለይ ወንጌላዊ በተናገረ ቁጥር እውነትን በውበት ያስጌጣታል፡፡ የክርሰቶስ መንፈስ ይሰፍንበትና እግዚአብሔር ሌሎችን ለመርዳት መሣሪያ ያደርገዋል፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ ልቡንና አእምሮውን በተስፋና በድፍረት ይሞላዋል፡፡ ከእርሱ ዘንድ የሚማሩትም እርሱ ያገኘውን በረከት ያገኛሉ፡፡GWAmh 161.2

    በመንፈስ ቅዱስ ውስጥ የእግዚአብሔርን የማያሳስት ምክር እናገኛለን፡፡ ትምህርቱ ተከታይ ካገኘ ለማንኛውም የሥራ ዓይነት ገጣሚ ያደርጋል፣ የእግዚአብሔር ድምፅ በየቀኑ ለነፍሳችን ይናገራል፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ የጨለመውን ማብራት፣ ደንጊያ ልቦችን ማለስለስ፣ አመፀኛን መመለስ፤ ከዓለም ጥፋትም ሰዎችን ማዳን ነው፡፡ የሱስ ለደቀመዛሙርቱ ሲጸልይ «ቃልህ እውነት ናትና በአውነትህ ቀድሳቸው» አለ፡፡ የእግዚአብሔርም ቃል የመንፈስ ነውና ልብን ሰርሥሮ ይቆርጣል፡-: የሚናገረውን ከሥራ ላይ ሳያውል ነፍሳትን ለመመለስ የሚሞክር ተናጋሪ ሰዎችን ያርቃል፤ ለእነዚያ ነፍሳት ጥፋትም ኃላፊነት አለበት፡፡GWAmh 161.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents