Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ተችትን መቋቋም

    ወንጌንላዊያኖቻችንና መምህራኖቻችን ለወደቀው ዓለም የእግዚአብሔርን የሚያሳዩ ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በፍቅር በተሞላ ልብ ይነገር፡፡ የተሳሳቱትን ሁሉ ክርስቶስ ባሳየው የዕውነት አቀራረብ መታየት ይገባቸዋል፡፡ ሰዎች በአንድ ጊዜ ባያስተውሉሱሉ አትንቀፏቸው፤ አትፍረዱባቸውም፡፡ የክርስቶስን ፍቅር፤ ገረነትና ጨዋነት ለመግለጥ አእንደተሰለፋችሁ አትርሱ፡፡ የማያምኑና ተቃዋሚዎች አንደሚያጋጥሙን አለመርሳት ነው፡፡GWAmh 244.4

    እውነት ሁል ጊዜ ከተቃውሞና ከጥርጥር ጋር ትታገላለች፡፡ ምንም ጠንካራ ተቃውሞ ቢገጥማችሁ ተቃዋሚዎቻኙሁን አትስደቡ ወይም አትንቀፉ፡፡ ጳውሎስ እንደመሰለው ሁሉ እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ መስሏቸው ይሆናል፡፡ አንደ ላሱት ሰዎች ትዕግሥትና ገርነት ማሳየት አለብን፡፡GWAmh 245.1

    በሕዝብ ተቀባይነት የሌለው ትምህርት ስናስተምር ችግር፣ ክርክርና ፈተና ይገጥመናል ብለን አንፍራ፡፡ የሱስ ስለ እናንተ ሲሰቃይ ጸጥ ማለቱን አስታውሱ፡፡ ሲሰደብና በሀሰት ሲከሰስ እንኳን አላጉረመረመም፤ የተቃውሞ ድምጽ አላሰማም፡፡ ተስፋ የመቁረጥና የብስጭት መንፈስ አይሰማችሁ፡፡ «ስለ ሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ ክፉ አንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙት ነገር በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩ ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኙሮአችሁ መልካም ይሁን፡፡»(1 ጴጥ. 2፡12)GWAmh 245.2

    በስህተት ውስጥ ላሉ ሰዎች ገሮች ሁኑ፡፡ እናንተስ ብትሆኑ በቅርቡ በኃጢዓት ታውራችሁ አልነበረምን? ክርስቶስ ለእናንተ ታጋሽ ስለሆነ እናንተስ ሌሎችን ልትታገሠ አይገባምን? አንድን ሰው በስህተት አቅጣጫ አንዳንመራ የሚቃወሙንን በትህትና እንድንመለከት እግዚአብሔር አስጠንቅቀቆናል፡፡ ሕይዎታችን በክርስቶስ ሕይወት የተጠለለ መሆን ይገባዋል፡፡ ክርስቶስን በግል ማወቅ አለብን፡፡GWAmh 245.3

    ለዓለም ልናስተዋውቀው የምንኘሻኘል ያን ጊዜ ብቻ : «ጌታ ሆይ የሱስ በእኔ ቦታ ቢሆን ኖሮ ይሠራ አንደነበረው እንዳደርግ እርዳኝ» አያልን ዘወትር አእንጸልይ፡፡ የትም የት ብንሆን በመልካም ሥራ አማካይነት ብርሃናትን ለእግዚአብሔር ክበር ይብራ፡፡ የሕይዎታችን ሙሉ ዋና ተግባር ይህ መሆን አለበት፡፡GWAmh 245.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents