Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የትክክለኛ መመሪያዎች አስፈላጊነት

    በንግድ መስመር የሚሠሩ ሰዎች ያልተስተካክለ መመሪያ ወይም የተሳሳተ ዘዴ ይዘው አንዳይሰናክሉ መጠንቀቅ አለባቸው፡፡ ታሪካቸው በባቢሎን ቤተመንግሥት እንደነበረው አንደ ዳንኤል ታሪክ ይሁን፡፡ የሠራው ሥራ ሁሉ ለምርመራ ሲቀርብ ምንም ስህተት አልተገኘበትም። የሥራው ታሪክ ፍጽም ባይሆንልንም ሊጠና የሚገባው ትምህርት አለበት፡፡ የሥራ ሰው ማለት ሆነ ተብሎ ለዚያው ሥራ የሠለጠነ መሆ'ን እንደሌለበት ያመሰክታል፡፡ ስለ እግዚአብሔር በሚገባ ያወቀ መሆን አለበት፡፡ ዳንኤል የባቢሎን ጠቅላይ ሚነስትር ሳለ ከሰማይ ብርሃን የሚገለጥለት የእግዚአብሔር ነቢይ ነበር፡፡ ሕይወቱ እያንዳንዱ ክርስቲያን ሠራተኛ እንዴት ሊሆን እንደሚገባ የሚያስረዳ መግለጫ ነው፡፡GWAmh 282.5

    በአሁኑ ዘመን የእግዚአብሔር ሥራ ጥሩ የአስተዳዳሪነት ችሎታ ያላቸው ወንዶችና ሴቶች ያስፈልጉታል፡፡ በየሥራው መስመር ያለውን ፍላጎት በትዕግሥትና በዕውነት የሚመረምሩ፣ የሥራ ፍላጎትና ) ያላቸው፣፤ አፍቃሪና ቸር ልብ ያላቸው፣፤ ቶሎ የማይቆጡ፤ ፍርዳፕዥው አድሏዊ በመንፈስ ቅዱስ ተቀድሰው ያለፍርሃት እጡነተን ዕውነት ሐሰቱን ሐስት ለማለት የሚችሉ፤ ብርቱ የማመዛዘን ግልጽ የማስተዋል ተሰጦ ያላቸው፤ ንጹህና አዛኝ ልብ ያላቸው፣፤፣ «ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ» (ማቴ 23:8) የሚለውን ቃል ከሥራ ላይ አውለው የወደቀውን የሰብዓዊ ዘር ለማንሳት የሚጥሩ ሰዎች በጣም ይፈልጋሉ፡፡GWAmh 283.1

    የተመደቡበትን ዋና ተግባር የሚዘነጉ ወንጌላዊያን ጥቁቶች አይደሉም፡፡ ለወንጌጸ ሥራ የተመደቡ ሰዎች ለምን የኮሚቴ አባሎች ይሆናሉ? ከሥራ ቦታቸው ራቅ ብለው በሚገኙ የስብሰባ ጉባዔዎች አንዲካፈሉ ለምን በየጊዜው ይጠራሉ? የአስተዳደር ጉዳይ ለምን በአስተዳደር ሰዎች አይወሰንም? የወንጌላዊያን ሥራ ይህ አልነበረም፡፡ ገንዝብ ነክ ጉዳዮች ለዚያው የሥራ መስመር በተመደቡ ሰዎች መጠናቀቅ አለበት፤ ወንጌላዌያን ግን ምድባቸው በሌላ ዓይነት ሥራ ነው፡፡GWAmh 283.2

    የገንዘብ ነክ ጉዳዮችን ለመወሰን ወጦንጌላዊያን ኮሚቴዎችን ለመካፈል እዚያም እዚህም መጠራት የለባቸውም፡፡ ብዙ ወንጌላዊያን ባለፈው ጊዜ ይህን ቢያደርጉም እግዚአብኤር ያጫቸው ስራ አልነበረም፡፡ ከመጠን በላይ የሆነ ገንዘብ ነክ ኃላፊነት ተጥሎባቸው ነበር፡፡ ይህን ሥራ ለማጠናቀቅ ሲሞክሩ የወንጌል ሥራ ሳይሠራ ይቀራል፡፡ እግዚአብሔር ይህን ስሙ እንደተዋረደ አድርጎ ይቆጥረዋል፡፡GWAmh 283.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents