Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የወንጌል አገልጋዮች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የኃጢአት ኑዛዜ

    ጤናቸው አንዲመለስላቸው የሚጸልዩ ሰዎች የእሣዚአብሔርን ሕግ መተላለፍ ኃጢዓት መሆኑን ተገንዝበው የኃጢዓት ይቅርታ ማግኘት እንዳለባቸው ይወቁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ «እርስ በርሳችሁ በኃጢዓታችሁ ተናዘዙ፤ ትፈወሱ ዘንድ እያንዳንዱ ስለሌላው ይጸልይ» ሲል : ጸልዩልኝ ብሎ የሚጠይቅ ሰው «ልብህን ልናነብ ወይም የምሥጢር ሥራህን ልናውቅ አንችልም:: ይህን የምታውቁ አሣዚአብሔርና አንተ ብቻ ናችሁ፡፡ ከኃጢዓትህ ከተመለስህ በኃጢዓትህ መናዘዝ የራስህ ፋንታ ነው» የሚል ቁርጥ መልስ ይሰጠው፡፡GWAmh 136.2

    የግል ኃጢዓት አማላጅና አዳኝ እርሱ ብቻ ለሆነው ለክርስቶስ : ‹ማንም ኃጢዓት ቢሰራ ከአብ ዘንድ አማላጅ አለን፣ እርሱም የሱስ ክርስቶስ ጻድቅ::” (1ኛዮሐ. 2፡1) ይላል፡፡ ማንኛውም ኃጢዓት እግዚአብሔርን ስለሚያስቀይም በክርስቶስ በኩል ለርሱ መናዝዝ አለብን፡፡ በግልጽ የተደረገ ኃጢዓት የግልጽ ኑዛዜ ያስፈልገዋል፡፡ ሌላ ሰው በማስቀየም የተፈጸመ ኃጢዓት የተቀየመው ሰው ይቅርታ ለ.ጠየቅ ይገባል፡፡ አንድ የታመመ ሰው ሸካራ ንግግር ተናግሮ የቤተሰብ ጎረቤት ወይም የቤተ ክርስቲያን አባል አስቀይሞ ሌሎችን ሃጢዓት እንዲሠሩ ምክንያት ሆኖ አንደሆን ያስቀየማቸውን ሰዎች ይቅርታ ይጠይቅ፡፡ «በኃጢዓታችን ብንናዘዝ እርሱ የታመነና ጻድቅ ነው ኃጢዓታችንን ይቅር ይለን ዘንድ ከክፉም ሁሉ ያነፃን ዘንድ፡፡ (ዮሐ.1፡9)GWAmh 136.3

    የተጠቀሰው ከተቃና በኋላ የበሽተኛውን መንፈሳዊ ዝንባሌ በመመዘን ልንጸልይለት እንችላለን፡፡ ክርስቶስ እያንዳንዱን ሰው ለብቻ ደሙን እንዳፈሰሰለት በመቁጠር ያውቀዋል፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህን ያህል ጥልቀት ስላለው በሽተኛው በሙሉ በተስፋና በደስታ ሊጸልይ ይችላል፡፡ 15 ዮሐንስ 1:9:GWAmh 136.4

    ምን ይደርስብኝ ብሎ መስጋት ድካምንና በሽታን ያስከትላል፡፡ ፊታቸው ፈታ፤ አካላቸው ነቃ ካለ በሽታንና ሕመምን ድል ይነሳሉ:: «የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደሚፈሩት : (መዝ. 33፡18)GWAmh 137.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents